Jump to content

ኦሲሪስ አፒስ

ከውክፔዲያ
(ከዩፒተር ኦሲሪስ የተዛወረ)

ሃሞን ዩፒተር ኦሊምፑስ ኦሲሪስ (አፒስ) የጣልያናዊ መኖኩሴ አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ1490 ዓ.ም. ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ የካሜሴኑስሬያ ልጅ ሲሆን እነርሱ በሊብያ በገዙበት ወቅት ተወለደ (2279 ዓክልበ. ግድም)። የሃሞን ልጅ ዲዮኒሶስ ግን የአባቱን ቂም በቅሎ በ2271 ዓክልበ. ካሜሴኑስን ወደ ግብጽ አባረረው፤ ልጁንም አፒስን የግብጽ ንጉሥ አደረገው። በ2261 ዓክልበ. ካምና ሬያ እኅቱን ዩኖ ኢሲስ ወለዱ፤ ይቺም የአፒስ ሚስት ሆነች። በ2211 ዓክልበ. ግድም አፒስና ዩኖ ወደ ከነዓን ሄደው የስንዴ ምርት አስተማሩ። ከ2180 ዓክልበ. ግድም በኋላ ወደ ግብጽ ተመልሰው የማረሻ ጥቅም አስተማሩ። በኋላ አፒስ እጅግ ረጅም እድሜ እየኖረ በአውሮጳ እየተጓዘ ግብርናን እያስተማረ አገሮችን ተገዥ አደረጋቸው። በ2057 ዓክልበ. ግድም በጥራክያ አገር ሊኩርጉስን ገደለው። በ2034 ዓክልበ. ግድም የአፒስ ልጅ ማከዶንኤማጥያ ገዛ፤ ስለዚህ አገሩ በስሙ መቄዶን ይጠራ ጀመር። በ2019 ዓክልበ. የኦሲሪስ ሰፈሮች እስከ ዳኑብ ወንዝ በደረሱበት ጊዜ፣ ጣልያኖቹ በጊጋንቴስ አምባገነኖች ዕጅ ተጨቆነው ለአፒስ እርዳታ ጠየቁ፤ አፒስም ለ10 ዓመት ጣልያንን ለራሱ ያዘ። በ2009 ዓክልበ. ግድም አፒስ ወደ አገሩ ግብጽ ተመለሰና በዚያ ስለ ጉዞዎቹ የመዘገቡ ዓምዶችን አስቀረጸ። ሆኖም ወንድሙ ቲፎን ያንጊዜ አፒስን ገደለው፤ መንግሥቱን ቃመ። ቲፎንም በፈንታው በቅርብ ጊዜ ውስጥ በሄርኩሌስ ሊብዩስ ኦሲሪስ ተገደለ፤ ይህም ሄርኩሌስ ወዲያው ወደ ጣልያን ዘመቻ ሄደ።

የአፒስ ዘመን ደግሞ በሲክዮንና በአርጎስ ጥንታዊ ነገሥታት ዝርዝሮች ቢታይም፣ በሲክዮን ዜና መዋዕል አከታተላቸው ትንሽ ተዛብቷል። በነዚህ ከተሞች አፒስ ከ2059 እስከ 2034 ድረስ እንደ ነገሠ ይመስላል። ፔሎፖኔሶስ ከዚያ እስከ ፔሎፕስ ዘመን ድረስ በርሱ ስም «አፒያ» እንደ ሆነ ይባላል። እንዲሁም በግሪክ ልማድ ዘንድ አፒስ በኋላ ወደ ግብጽ ሄዶ በዚያ ንገሠና እንደ አምላክ ሴራፒስ፣ ኦሲሪስ፣ ሃሞን ዩፒተር ወይም ሞንቱ ተቆጠረ። በተቃራኒ ምንጭ ግን (በአፖሎዶሮስ የተባለው ቢብሊዮጤኬ) አፒስ በቴልቂንጤልክሲዮን ተገደለ። ከትውፊቶቹ ብዛት የተነሣ ደግሞ ብዙ ልዩ ልዩ አፒሶች እንደ ነበሩ አንዳንዴ ይቆጠራል።

ዲዮዶሮስ ስለዚሁ ኦሲሪስ ኢንዲህ ይላል፦ ኦሲሪስ የወይን፣ የስንዴና የገብስ ጥቅም አገኘ፣ ግብጽንም ካስተዳደረ በኋላ አገሩን ለንግስቱ ኢሲስና በአገረ ገዥነት ለሄርኩሌስ ሊብዩስ፣ ለቡሲሪስና ለአንታዮስ ለቅቆ ከሥራዊት ጋር ወደየ አገሩ ዞረ፣ የእርሻ ጥቅም በማስተማር ሕዝቦችን ተገዥ አደረጋቸው። በኢትዮጵያ ጭፍረኞች (ወይም ሳቲሮች የተባሉ) አመጡለት፣ ከዚያ እነዚህና ዘጠኙ ሙሳያውያን (ሴት ዘፋኞች) ከኦሲሪስ ጋር ተጓዙ። እርሻ ካስተማራቸው በኋላ አንዳንድ ከተማ ሠራ ደግሞ በአባይ ላይ ገደብ ሠራና አገረ ገዥ ለቅቆ ወደ አረቢያ ተሻገረ። እስከ ሕንድ ድረስ የእስያ አገራት ሁሉ ጎበኘ። ከዚያ ወደ አውሮፓ ከአሁኑ ቱርክ አገር ተሻገረ። የጥራክያ ንጉስ ሊኩርጉስ ተቃውሞት ኦሲሪስ ገደለውና አለቃውን ማሮን አገረ ገዥ አደረገው። ይህ ማሮን ማሮኔያ የተባለ ከተማ በጥራክያ ሠራ። ልጁን ማከዶን በመቄዶንያ ገዥነት ለቀቀው፤ አቲካንም ለትሪፕቶለሞስ ሰጠው። እንዲህ ኦሲሪስ እንኳን እስከ እስተር (ዳኑብ) ወንዝ መነሻ ድረስ ደረሰ። ወደ አገሩ ግብጽ በተመለሰበት ጊዜ ግን ወንድሙ አለቃው ቲፎን ገደለው። የኦሲሪስ ልጅ ሄርኩሌስ ግን ቂሙን በቅሎ ቲፎንን ገደለው።

ቀዳሚው
ሌውኪፖስ
የአፒያ (ሲክዮን) ንጉሥ
2059-2034 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
መሣፖስ
ቀዳሚው
ፎሮኔዎስ
የአፒያ (አርጎስ) ንጉሥ
2059-2034 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
አርጉስ
ቀዳሚው
ዔናቂ ሉኪ (ኣምባገነኖች)
የራዜና (ጣልያን) ንጉሥ
2019-2009 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሌስትሪጎን