ጥር ፲፬
Appearance
(ከጥር 14 የተዛወረ)
ጥር ፲፬ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፴፬ ኛው ዕለት ሲሆን ፲፱ ኛው የበጋ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፪፻፴፪ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፪፻፴፩ ዕለታት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፲፮ ዓ/ም በቀድሞዋ 'ጎልድ ኮስት' (አሁን ጋና) የአሻንቲ ብሔረሰብ ሠራዊት የእንግሊዝን ሠራዊት በውጊያ አሸንፈው በአፍሪቃአኅጉር፣ የነጭ ቅኝ ገዥ ሠራዊትን በማሸነፍ የመጀመሪያው ብሔረሰብ ሆኑ።።
- ፲፰፻፸፩ ዓ/ም በዛሬዪቷ ደቡብ አፍሪካ በእንግሊዝ ሠራዊት እና በዙሉ ብሔረሰብ መኻል በተካሄደው የ'ኢሳንድልዋና'(Battle of Isandlwana) ውጊያ ዙሉዎች አሸናፊ ሆኑ።
- ፲፱፻፷፪ ዓ/ም የቦይንግ 'ጃምቦ ጄት' በመባል የሚታወቀው ቢ ፯፻፵፯ (Boeing 747) አየር ዠበብ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳፋሪ መንገደኞችን ጭኖ ከኒው ዮርክ ኬኔዲ ዓየር ጣቢያ ተነስቶ ሎንዶን ሂዝሮው ዓየር ጣቢያ አረፈ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም በአገር ውስጥ በረራ ከባህር ዳር ወደ ጎንደር በመብረር ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ DC-3 አየር ዠበብ በአራት የኤርትራ ነጻነት ግንባር አባላት ተጠልፎ ሊቢያ ውስጥ ቤንጋዚ ከተማ አረፈ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የመገናኛ ሚንስትር፣ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን፤ ኡ ታንትን ተክተው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ለመሆን በምርጫው እንደሚሣተፉ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት እጩነታጨውን ይፋ አደረጉ።
- ፲፰፻፺፫ ዓ/ም በታላቋ ብሪታኒያ እና አየርላንድ ንጉዛት ዙፋን ላይ ለ ስድሳ አራት ዓመታት የነገሡት ንግሥት ቪክቶርያ በተወለዱ በ ፹፪ ዓመታቸው አረፉ።
(እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/January_20
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |