ሚያዝያ ፳
Appearance
ሚያዝያ ፳፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፳፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፴፮ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፴፭ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - የኢጣልያ የፋሺስት መሪ የነበረው ቤኒቶ ሙሶሊኒ ከነውሽማው ክላራ ፔታቺ ጋር በቀበሌ ታጣቂዎች ተይዞ በኮሎኔል ካሌሪዶ ከተረሸነ በኋላ አደባባይ ላይ ቁልቁል ተሰቀለ።
- ፲፱፻፶፱ ዓ/ም - ጥቁር አሜሪካዊው ቡጢኛ ሙሐመድ አሊ ወደአገሪቱ ጦር ሠራዊት ገብቶ የማገልገል ግዴታውን እንዲወጣ ቢጠየቅም አሻፈረኝ አለ። የዚያኑ ዕለት የዓለም ቻምፒዮናነቱን ማዕረግ በኒው ዮርክ የአትሌቲክ ባለ ሥልጣን ተገፈፈ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የአገራቸውን አርበኞች የመሩትና ከነጻነት በኋላም የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ሆነው ለ አሥራ አንድ ዓመታት ያገለገሉት ሻርል ደጎል በፈቃድቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ።
- ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - በስዊድን፤ ፊንላንድ እና ኖርዌይ የሚገኙ የኑክሊዬር ምርመራ ማዕከላት ያልተለመደ የራዲዮ-አክቲቭ በከላ በምድር ጠፈር ላይ እንዳገኙ ባስታወቁ በሁለተኛው ቀን የሶቪዬት ኅብረት ባለ ሥልጣናት ቸርኖቢል የሚባለው የኑክሊዬር የመብራት ኃይል ማምረቻ አደጋ እንደደረሰበት ይፋ አደረጉ።
- ፲፱፻፲፮ ዓ/ም - የዛምቢያ የመጀመሪያ ፕሬዚደንት የነበሩት ኬኔዝ ካውንዳ ተወለዱ።
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - የቀድሞው የኢራቅ ፕሬዚደንት ሳዳም ሁሴን አብደል ማጂድ አል ቲክሪቲ በዚህ ዕለት አል አውጃ በሚባል ሥፍራ ተወለዱ።
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 Annual Report from Ethiopia for 1960
- (እንግሊዝኛ) http://www.thepeoplehistory.com/april27th.html
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/April_28
- (እንግሊዝኛ) http://news.bbc.co.uk/onthisday/hi/dates/stories/april/28/newsid_3564000/3564529.stm
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |