Jump to content

አሞራውያን

ከውክፔዲያ
የ17:18, 29 ዲሴምበር 2017 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

አሞራውያን (ሱመርኛማርቱአካድኛአሙሩግብጽኛአማርዕብራይስጥאמורי /አሞሪ/) በጥንት ከኤፍራጥስ ወንዝ ወደ ምዕራብ የኖረ ሕዝብ ነበረ።

'አሙሩ' በአካድ መንግሥት ዘመን (2075 ክ.በ. ገዳማ)

«የማርቱ አገር» ከሁሉ ጥንታዊ በሆኑት ሱመራዊ ምንጮች ለምሳሌ በኤንመርካርና የአራታ ንጉሥ ወይም በኤብላ ጽላቶች ይጠቀሳል። ለአካድ ነገሥታት ደግሞ 'ማርቱ' በአካድ ዙሪያ ከነበሩት 'አራት ሩቦች' አንዱ ሲሆን ሌሎቹ 3 ሱባርቱ፣ ሱመርና ኤላም ነበሩ። ይህ ስያሜ ወደ ምዕራብ የሆኑት አገራት ሶርያከነዓን ይጠቀልል ነበር። ሉጋልባንዳና የአንዙድ ወፍ በተባለው ትውፊት ዘንድ፣ የኡሩክ መጀመርያ ንጉሥ ኤንመርካር እነሱን ለመከልከል በ፶ኛው ዓመት ግድግዳ በበረሃ አሠራ፣ ይህም ምናልባት 2425 ዓክልበ. ሆነ።

የአካድ ንጉሥ ናራም-ሲን ስሜን ሶርያን 2040 ዓክልበ. ገደማ ወርሮ ዘመተባቸው፤ ልጁም ሻር-ካሊ-ሻሪ እንዲህ አደረገ። በኡር መንግሥት ዘመን በአንዳንድ ሰነድ አሞራውያን እንደ ዘላኖች ይሰደባሉ። ለምሳሌ፦

«ምንምን እህል የማያውቁት ማርቱ.... ምንም ቤት ወይም መንደር የማያውቁት ማርቱ፣ የተራሮች ደደቦች... ለእንጉዳይ የሚቆፈር ማርቱ... (ምድርን ለማረስ) ጉልበቱን የማይበርከክ፣ ጥሬ ሥጋ የሚበላ፣ በሕይወቱ ዘመን ቤት የሌለው፣ ከሞተ በኋላ የማይቀበር ነው»።
«ስንዴና እህል ያዘጋጃሉ፤ አሞራዊ ግን ምን እንዳለበት ሳያውቅ ይበላዋል!»

በኡር መንግሥት ጊዜ፣ አሞራውያን በአገሩ ውስጥ በጣም በመብዛታቸው ምክንያት፣ እንደገና እነሱን ለመከልከል ንጉሶቹ እንደ ሹ-ሲንጤግሮስና ከኤፍራጥስ መኃል አዲስ ታላቅ ግድግዳ ሠርተው ነበር።

የኡር መንግሥት በኤላም እጅ በ1879 ዓክልበ. ገደማ በወደቀበት ጊዜ በመንግሥቱ ውስጥ የኖሩት ብዙ አሞራውያን የራሳቸውን መንግሥታት አቆሙ። «የአሞራውያን መንግሥታት ዘመን» በመስጴጦምያ ታሪክ ከ1879 እስከ 1507 አመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው። ዋናዎቹ አሞራውያን ሥርወ መንግሥታት በማሪ፣ በያምሐድቃትና፣ በአሦር (በአሞራዊው 1 ሻምሺ-አዳድ ገዥነት)፣ በኢሲን፣ በላርሳና በባቢሎን ተነሡ።

ስለ ቋንቋቸው የሴማዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ከመሆኑና ከጥቂት ስሞች በቀር ምንም ዕውቀት አሁን የለንም። በተለይ በማሪ ጽላቶች (1800-1750 ክ.በ. ገዳማ) መካከል የተገኘ የአንዳንድ አሞራዊ ጽሑፍ በአካድኛ ተጻፈ።

'የአሞራውያን ዘመን' መጨረሻ ኬጥያውያን ባቢሎንን በ1507 ክ.በ. ገዳማ (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) ሲያሸንፉት ነበር። ከዚያ ጀምሮ አዳዲስ ወገኖች - በተለይም ካሣውያንሚታኒ - በመስጴጦምያ ተነሡ። ከዚያ በኋላ አሙሩ ሲጠቀስ ማለቱ ስሜን ከነዓን እስከ ቃዴስ ብቻ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን ውስጥ 'አሞራውያን' በከነዓን ምድር የኖረ ሕዝብ ነው። በኦሪት ዘፍጥረት 10፡16 መሠረት የከነዓን ካም ልጆች ናቸው። በብዙ ጥቅሶች 'አሞራውያን' እና 'ከነዓናውያን' የሚሉት ስሞች የሚለዋወጡ ያሕል ናቸው።

ጨው ባሕርና ከዮርዳኖስ ወንዝ ምዕራብ ከሆኑት ተራሮች ጀምሮ እስከ ኬብሮን ድረስ ያለው አገር ከነገለዓድባሳን ጋር ነበራቸው። ኢያሱ እስራኤላውያንን ዮርዳኖስን አሻግሮ ወደ ከነዓን ሳይመራቸው ሙሴ ከአሞራውያን ንጉሦች ከዐግና ከሴዎን ሠራዊት ጋር ታግሎ አሸነፋቸው። እንዲሁም አሞራውያን በግብፅ በተገኙ አማርና ደብዳቤዎች ዘንድ የጢሮስ፤ የሲዶናና የሌሎች ከተሞች ጠላት ሆኑ። በሳሙኤል ዘመን ግን በእስራኤልና በአሞራውያን መካከል ሰላም ነበረ።