ሰኔ ፳፩
Appearance
ሰኔ ፳፩፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፺፩ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ/(በልግ)ወቅት ፹፮ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፸፭ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፸፬ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፮ ዓ/ም - የ አውስትሪያ እና ሁንጋሪያው ዘውድ አልጋወራሽ፣ አውስትሪያዊው አርች ዱክ ፍራንዝ ፈርዲናንድ በዩጎዝላቪያዊ ነፍሰ ገዳይ እጅ ሰኔ ፲፱ ቀን ፲፱፻፮ ዓ/ም መገደል ነው።የአውስትሪያው ልዑል ‘ፍራንዝ ፈርዲናንድ’ እና ባለቤታቸው የሳራዬቮን ከተማ በመጎብኘት ላይ ሳሉ በነፍሰ ገዳይ እጅ ሕይወታቸውን አጡ። ይኼ ድርጊት የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት መንስዔ እንደነበር በታሪክ ተዘግቧል።
- ፲፱፻፲፩ ዓ/ም - የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ተቀናቃኞች፤ በአንድ በኩል አለማኝያ እና በሌላው ወገን የቃል ኪዳን አገራት የጦርነቱን ፍጻሜ ስምምነት የቨርሳይ ውል በዚህ ዕለት ተፈራረሙ።
- ፲፱፻፶፩ ዓ/ም - የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ካይሮ ላይ በተካሄደ ሥርዓተ-ሢመት በቅብጡ ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ ተቅብተው የፓትርያርክነቱን ዘውድ ደፉ።
- (እንግሊዝኛ) FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |