ጥቅምት ፲፪
Appearance
(ከጥቅምት 12 የተዛወረ)
ጥቅምት ፲፪
ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፵፪ኛው እና የመፀው ፲፮ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፳፬ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፳፫ ዕለታት ይቀራሉ።
- ፲፯፻፺ ዓ/ም - በፓሪስ ከተማ፣ ሦስት ሺህ ሁለት መቶ ጫማ ሽቅበት ላይ አንድሬ-ዣክ ጋርኔራን የተባለ ሰው በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመዝለያ ጥላ (parachute) ዘለለ።
- ፲፰፻፵ ዓ/ም - ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ የሸዋን ንጉዛት ወርሰው በዙፋኑ ተቀመጡ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በኩባ ደሴት ላይ የሶቪዬት ሕብረት የኑክሊየር መሣሪያዎች ማስቀመጧን በስለላ መረጃዎች ካረጋገጡ በኋላ፤ በደሴቷ ዙሪያ በአየርም ሆነ በባሕር ላይ የእንቅስቃሴ እገዳ ትእዛዝ አስተላለፉ።
- ፲፱፻፳፫ ዓ/ም - የቴአትር ደራሲ፥ ጋዜጠኛና የቀድሞው የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ሊቀ መንበር ማሞ ውድነህ በዚህ ዕለት በዋግ አውራጃ ዐምደ ወርቅ ከተማ ተወለዱ።
- ^ መስፍን አረጋ (ዲባቶ)፤ ሰገላዊ አማርኛ፤ ፳፻ ዓ.ም
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |