Jump to content

ናሚቢያ

ከውክፔዲያ

የናሚቢያ ሪፑብሊክ
Republic of Namibia

የናሚቢያ ሰንደቅ ዓላማ የናሚቢያ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር "Namibia, Land of the Brave"

የናሚቢያመገኛ
የናሚቢያመገኛ
ዋና ከተማ ዊንድሁክ
ብሔራዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛአፍሪካንስ
መንግሥት
{{{
ፕሬዝዳንት
ምክትል ፕሬዝዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር
 
ሓገ ገይንጎብ
ኒኪ ዒያምቦ
ሳራ ኩጎንጌልዋ
ዋና ቀናት
መጋቢት 12 ቀን 1982
March 21, 1990 እ.ኤ.አ.
 
የነፃነት ቀን
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
825,418 (33ኛ)
የሕዝብ ብዛት
የ2011 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
 
2,113,077
ገንዘብ የናሚቢያ ዶላር
ሰዓት ክልል UTC +1
የስልክ መግቢያ +264
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን .na


ናሚቢያ በደቡብ-ምዕራብ አፍሪቃ የምትገኝ ሀገር ናት። በምዕራብ በአትላንቲክ ውቅያኖስ፣ በስሜን በአንጎላና በዛምቢያ፣ በምስራቅ በቦትስዋና፣ በደቡብም በደቡብ አፍሪቃ ትካለላለች። በ1982 አመተ ምኅረት ነጻነትዋን ከደቡብ አፍሪቃ ስላገኘች በጣም አዲስ አገር ነች። ዋና ከተማዋ ዊንድሁክ ነው።

የናሚቢያ በረኅ አውራጃ ከጥንት ጀምሮ በሳን (ቡሽማን)፣ በዳማራና በናማቋ ሕዝቦች ተሰፈረ። በ14ኛው መቶ ዘመን፣ የባንቱ ወገኖች ባስፋፉ ጊዜ አገሩን ሠፈሩ። ክልሉ ግን ከ19ኛው መቶ ዘመን በፊት በአውሮጳውያን አልተዘለቀም። በዚያን ጊዜ ጀርመን ደቡብ-ምዕራብ አፍሪቃ ተብላ አገሪቱ የጀርመን ቅኝ ግዛት ሆነች። ዳሩ ግን ዋልቪስ በይ የተባለው ትንሽ ወደብ ብቻ የእንግሊዝ ግዛት ነበር።