Jump to content

ዳግማዊ ዓፄ ዳዊት

ከውክፔዲያ
(ከሳልሳዊ ዳዊት የተዛወረ)

ዳግማዊ ዓፄ ዳዊት፣ ዙፋን ስም አድባር ሰገድ፣ ከ1708 እስከ 1713 ዓም ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። ከዘመኖች በፊት ነግሠው የነበሩት ዓፄ ልብነ ድንግል ደግሞ በይፋ «ዳግማዊ ዳዊት» ስለ ተሰየሙ፤ ይሄው ንጉሠ ነገሥት እንዲሁም ሣልሳዊ ዓፄ ዳዊት ተብለዋል። የቀዳማዊ ዓፄ ኢያሱና የቁባታቸው የቅድሥተ ክርስቶስ ልጅ ነበሩ።

በሃይማኖት ረገድ በዚሁ ዘመን ሦስት ትልልቅ ድርጊቶች ተከሠቱ። መጀመርያው የአቡነ 10ኛው ማርቆስ ዕረፍት ነበር። ዳዊት ወደ እስክንድሪያ ልከው ከዓመታት በኋላ አዲሱ አቡነ ክርስቶዶሎስ ደረሱላቸው።[1]

ሁለተኛው ድርጊት ሦስት ሮማን ካቶሊክ ካፑቺን ሰባኪዎችና አንድ ልጅ ያለ ፈቃድ ወደ ሀገሩ ሲገቡ ሆነ። አራታቸው ታስረው እንደ ሀረ ጤቆች ተፈረደባቸውና ተገደሉ።[2]

ሦስተኛውም ድርጊት አንድ የኢኦተቤ ሲኖዶስ በጎንደር መካሄዱ ነበር። በዚሁ ጉባኤ ላይ ከኤዎስጣጤዎስ ትምህርት ወገንና ከደብረ ሊባኖስ መኖኩሳት መካከል ክርክር ሆነ። አጼ ዳዊት ለኤዎስጣጤዎስ ወገን ደገፉ፤ ስለዚህ የደብረ ሊባኖስ ወገን አቤቱታ አሰሙ።[3] ዳዊትም ተበሳጭተው አረመኔ የሆኑትን ኦሮሞ ዘበኞቻቸውን ልከው መኖክሶቹን እንዳስገደሏቸው ይባላል።[4]

ከዚሁ ሲኖዶስ ቀጥሎ ታመው ከትንሽ አልፎ አጼ ዳዊት ዓረፉ። ከሎሌዎቹ አንዳንድና አንድ እስላማዊ ሀኪም በመርዝ ሴራ ተፈርደው ተገደሉ።[5]

ከዚህ በተረፈ ዳዊት የዘፈን ወዳጅ እንደ ሆኑ በፋሲል ግቢም ውስጥ የአዝማሪዎች አዳራሽ እንደ ሠሩ ይታወቃል። ከዚህ የተነሣ ቅጽል ስማቸውን ዳዊት አዝማሪ የተቀበሉ ነው። ከጎንደር ሲኖዶስ በፊት ቄሳውንትም ሙዚቃውን ይወድዱ ነበር፣ በኋላም በዚህ እንደ ሰደቧቸው ይባላል።[6]

  1. ^ James Bruce dates the arrival of the new Abuna to 3 November. (Travels to Discover the Source of the Nile (1805 edition), vol. 4 pp. 59, 68.)
  2. ^ E. A. Wallis Budge, A History of Ethiopia: Nubia and Abyssinia, 1928 (Oosterhout, the Netherlands: Anthropological Publications, 1970), pp. 440f.
  3. ^ Donald Crummey, Priests and Politicians, 1972 (Hollywood: Tsehai, 2007), p. 22
  4. ^ Richard P.K. Pankhurst, History of Ethiopian Towns (Wiesbaden: Franz Steiner Verlag, 1982), pp. 146f.
  5. ^ Pankhurst, Ethiopian Towns, p. 147. Paul B. Henze (Layers of Time, p. 104) accepts these reports as the truth.
  6. ^ Donald N. Levine, Wax and Gold: Tradition and Innovation in Ethiopian Culture (Chicago: University Press, 1965), p. 26