Jump to content

ይግባ ጽዮን

ከውክፔዲያ
(ከቀዳማዊ ሰለሞን የተዛወረ)

==

ዓፄ ይግባ ጽዮን
ይግባ ጽዮን አዳልን ወግቶ ዘይላን ሲቆጣጠር
ይግባ ጽዮን አዳልን ወግቶ ዘይላን ሲቆጣጠር
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ግዛት ከ1285- 1294 እ.ኤ.አ.
ተከታይ ዓፄ ሰይፈ አርድ ፬ኛ
ሥርወ-መንግሥት ሰሎሞን
አባት ይኩኖ አምላክ
የሞቱት 1294 እ.ኤ.አ.
ሀይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና

==


ዓፄ ይግባ ጽዮን በዘውድ ስማቸው ቀዳማዊ ሰለሞን ከ1285 - 1294 (እ.ኤ.አ) ሲነግሱ ከአባታቸው ይኩኖ አምላክ ጋር ከንግስናቸው በፊት አገሪቱን አብረው አስተዳድረዋል።

የዘመኑ ተጓዥ ማርኮ ፖሎ እንደጻፈ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በዚህ ንጉስ ዘመን የነበረው ታዋቂው የአውሮጳ ተጓዥ ማርኮ ፖሎ ስለአጠቃላይ የኢትዮጵያ ግዛትና በተለይ ንጉሱ በአዳል ላይ ያደረገውን ውጊያ በ1290 ባሳተመው መጽሃፉ ላይ ጠቅሷል[1]

እንደሰማሁት፣ በ1288 የሃበሻው ንጉስ ወደ እየሩሳሌም በመሄድ የኢየሱስ ክርስቶስን መቃብር ለመሳለም ፈልጎ የሱ መኮንኖች ይህ የሚያስከትለውን ችግር በተለይ የእስልምና ተከታይ መንግስታት በአካባቢ መብዛትን ግምት ውስጥ በማስገባት በሱ ምትክ በሃይማኖተኛነቱ ይደነቅ የነበረ ጳጳስ እንዲሄድ አድርጎ ይህ ጳጳስ እየሩሳሌም በመሄድ ስለት አስገብቷል። ጳጳሱ ሲመለስ ግን አዳል ውስጥ ተማርኮ የአዳሉ መሪ ጳጳሱ እስልምና እንዲቀበል ቢመክረው እምቢ በማለቱ ጳጳሱ እንዲገረዝ [እንዲሰለብ?] አደረገ። ከዚያም ጳጳሱ ወደ አገሩ ከተመለሰ በኋላ የተደረገበትን ግፍ ለንጉሱ ነገረው። ንጉሱም ወዲያው ፈረሱን አስጭኖ ከሰራዊቱ ጋር አዳልን ለማጥፋት ዘመተ። የአዳሉም ልዑል የአቢሲኒያ ጦር እንደዘመተበት በሰማ ጊዜ ሁለት ባለ ብዙ ሰራዊት እስልምና ተከታይ ንጉሶች ከእንዲረዱት ጥሪ አደረገ። ነገር ግን የሃበሻው ንጉስ ስላሸነፋቸው የኤደንን [አዳል?] ዋና ከተማ [ዘይላ?] በመቆጣጠር ከተማይቱን በዘበዘ። ይህም ለጳጳሱ የተደረገበትን ጉዳት ለመበቀል ነበር።

የእስልምና መስፋፋት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በዚህ ድል ምክንያት ሰላም በመገኘቱ የእስልምና ተከታይ የሆኑ ነጋዴወች ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያውን ውስጠኛውን ክፍል ዘልቀው ለመግባትና ለመነገድ ክፍተት አገኙ፣ በብዛትም በአገሪቷ ለመሰራጨት ቻሉ። [2] ይህ በዚ እንዳለ እስልምና በሃድያሶማሊያሐረርይፋት እና ዳህላክ ደሴቶች ከዚህ ንጉስ ዘመን በፊት ስር የሰደደ ቢሆንም፣ በአፋርአርሲሲዳሞ መሰበክና መስፋፋት የጀመረው በዚህ ዘመን ነበር። አርጎባም በእስልምና ስር የወደቀው በዚህ ዘመን ነው። የወላስማ ሥርወ መንግሥትይፋት የተነሳው በ1285 በዚህ ጊዜ ነው፤ ቀስ ብሎም አዳዲሶቹን ክፍለ ሃገሮች፦ ፈተገርን፣ ዳዋሮን እና ባሌን በተጽዕኖው ስር ለማስገባት ቻለ።[3]ትግራይ] ውስጥ የእስልምና ተከታዮች መሰባሰቢያ የሆነው ነጋሽ እየጎለመሰ ሄደ።

የመንግስት ሽግግር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በጥንቱ የኢትዮጵያ ነገስታት የነበረው ቋሚ ችግር፣ ስልጣንን የማወርስ ችግር ነበር። ይግባ ጺዮን 5 ወንድ ልጆች ነበሯቸው ግን ከ5ቱ የትኛው እንዲነግስ መወሰን ስላልቻሉ እያንዳንዱ ልጅ ለአንድ አመት እንዲነግስ እንዳረጉ ታሪክ ጻህፍት ይዘግባሉ [4]

  1. ^ Marco Polo, Travels, book 3, chapter 35.
  2. ^ Hubert Jules Deschamps, (eds.). General History of Black Africa to Madagascar and its islands Volume I: Beginnings to 1800. p. 398, PUF Paris (1970)
  3. ^ Hubert Jules Deschamps
  4. ^ ታደሰ ታምራት, Church and State in Ethiopia (1270 - 1527) (Oxford: Clarendon Press, 1972), p. 72