ተረት ሰ
Appearance
- ሰለሞን ሳባን ውሀ ባያስጠማት ኖሮ የሱ ጥም ባልበረደ ነበር
- ሰውን ፈላጊ በምርጫ ይሽነፋል
- ሰማይ አትረስ ንጉስ አትክሰስ
- ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ
- ሰባት አመት ባይማሩ ሰባ አመት ይደንቁሩ
- ሰነፍ ሴት ያገባ በሬው በሰኔ ገደል የገባ
- ሰነፍ በዓል ያበዛል
- ሰነፍ ቢመክሩት ውሀ ቢወቅጡት
- ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል
- ሰነፍ ገበሬ ክረምት በጋው በጋው ክረምቱ
- ሰኔ መቃጠሪያ ህዳር መገናኛ
- ሰኔ ሰላሳ የለውም ካሳ
- ሰኔና ሰኞ
- ሰኔን በዘራዘር ሃምሌን በጎመን ዘር
- ሰካራም ቤት አይሰራም
- ሰካራም ዋስ አያጣም
- ሰው መሳይ በሸንጎ
- ሰው በዋለበት ውሀ በወረደበት
- ሰው ቢማር ቄስ እንጂ መላክ አይሆንም
- ሰው ባለው ይሰለፋል
- ሰውን ማመን ቀብድ ተቀብሎ ነው
- ሰውን ሰው ናቀው የራሱን ሳያውቀው
- ሰውን ሰው ያሰኘው እቁብ ነው
- ሰውን ሲወዱ ከነንፍጡ እና ልጋጉ
- ሰውን ሲያማ ለእኔ ብለህ ስማ
- ሰው አለብልሀቱ ገደል መግባቱ አለጉልበቱ ውሀ መግባቱ
- ሰው አለወንዙ ብዙ ነው መዘዙ
- ሰው እንደ እውቀቱ ነው
- ሰው ከሞተ የለ ንስሀ ከፈሰሰ አይታፈስ ውሀ
- ሰውየው ውሀ ሲወስደው እኔም ወደ ቆላ እወርዳለሁ ብዬ ነበር አለ
- ሰው ያመነ ውሀ የዘገነ
- ሰው ያስገድላል አባይ ውሀ ያስጮሀል ድንጋይ
- ሰው ያለስራው የተሰረቀ አህያ ይነዳል
- ሰው ጥራ ቢሉት መራራን ጠራት
- ሰው ጥራ ቢሉት እራሱ መጣ
- ሰዶ ማሳደድ ቢሻህ ዶሮህን ለቆቅ ለውጥ
- ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ
- ሲሉ ስምታ ዶሮ ሞተች ዋና ገብታ
- ሲመክሩት ያልሰማ ሲያጮሉት ይሰማ
- ሲመች ያማት ተዝካር ይወጣል ሳይመች ያባት ይቀራል
- ሲሞቱ ብታይ አንቀላፋች
- ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል
- ሲሮጡ የፈቱት ሲቀመጡ ለማስተካከል ቀላል ነው
- ሲሮጥ የመጣን አህያ አጥብቀህ ጫነው
- ሲሰርቀኝ ያየሁትን ቢጨምርልኝ አላምነውም
- ሲስሟት ትታ ሲስቧት
- ሲስሟት እንቢ ብላ ሲጎትቷት
- ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል
- ሲበሉ አድርሰኝ ሲጣሉ አርቀኝ
- ሲበሉ አድርሱኝ ሲጣሉ መልሱኝ
- ሲቃ የቀስቀስው ነቅቶ አይተኛም
- ሲታጠቡ እስከ ክንድ ሲታረቁ ከሆድ
- ሲቸኩሉ የታጠቁት ለወሲብ አይመችም
- ሲቸግር ጤፍ ብድር
- ሲያውቀኝ ናቀኝ
- ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል
- ሲያደርጉ አይታ ዶሮም ጡት መያዣ ገዛች
- ሲጠሩት ወዴት ሲልኩት አቤት
- ሲጠባ ያደገ ጥጃ ቢይዙት ያጓራል
- ሲገደገድ ያልበጀው ሲወቀር እሳት ፈጀው
- ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ጸሎት
- ሳትወልድ ብላ
- ሳያሽ የበላ ዝንጀሮ ሲስል ያድራል
- ሳያውቁ የቆረጡት አበባ የፈለጉት ቀን ይደርቃል
- ሳያጣሩ ወሬ ሳይገሉ ጎፈሬ
- ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በቅርቡ
- ሳይሰሙ ወሬ ሳይገሉ ጎፈሬ
- ሳይቃጠል በቅጠል
- ሳይተርፋት አበድራ ሳትቀበል ሞተች
- ሳይቸግር ጤፍ ብድር
- ሳይቸግር ጤፍ ብድር መከበር በከንፈር
- ሳይቸግር ጤፍ ብድር በስተርጅና ሙሽርና
- ሳይከካ ተቦካ
- ሳይደግስ አይጣላም
- ሳይጠሩት አቤት የሰይጣን ጎረቤት
- ሳይጠሩት ወይ ባይ ሳይሰጡት ተቀባይ
- ሴቱ ሲበዛ ጎመን ጠነዛ
- ሴትና ዶሮ ዱር ከሄዱ ቤታቸውን ይክዳሉ
- ሴት ከወንድ እህል ከሆድ
- ሴት ለቤት ወፍጮ ለዱቄት
- ሴትና መሬት የማይችሉት የለም
- ሴት ማገዶ ሲቸግራት ምሰሶ ትነቅላለች
- ሴት ሲበዛ ልማት ይፋጠናል
- ሴት ሲበዛ ወንዶች ይፈራሉ
- ሴት በማጀት ወንድ በችሎት
- ሴት በጳጳስ ኳደሬ በንጉስ
- ሴት ብታውቅ በወንድ ያልቅ
- ሴት ሲያፏጩላት ያረሱላት ይመስላታል
- ሴት ታውቅ በወንድ ያልቅ
- ሴት አማት የመረዘው ኮሶ ያነዘዘው
- ሴት አግብተው ሴት ቢወልዱ የት አለ ንግዱ
- ሴት ከወንድ እህል ከሆድ
- ሴት ከጠላች በቅሎ ከበላች አመል አወጣች
- ሴት ካላበለች ባልዋን ትወልዳለች
- ሴት ካልወለደች ቋንጣ አትጠብስም
- ሴት ካልዋሸች ባልዋን ትወዳለች
- ሴትና መሬት የማይችሉት የለም
- ሴት የወደደ ጉም የዘገነ
- ሴት ያመጣው ጠብ አይበርድም
- ሴት ይወዷል ማጀት ያንጎዳጉዷል
- ሴትና ቄስ ቀስ
- ሴትና በቅሎ እንደገሪዋ ነው
- ሴትና አህያ በዱላ
- ሴትና አህያ ዱላ ይወዳል
- ሴትና ድመት ወደ ሞቀበት
- ሴትና ዶሮ ሳይጣላ አይውልም
- ሴትና ድስት ወደ ማጀት
- ሴትና ዶሮ ሳያብድ አይውልም
- ሴትና ፈረስ እንደኩሬ ውሀ እያደር ማነስ
- ሴትና ፈረስ የስጡትን ይቀምስ
- ሴትን ያመነ ጉም የዘገነ
- ሴት የላከው ምልክቱን አይረሳም
- ሴት የላከው ሞት አስፈራራው
- ሴት የላከው ሞት አይፈራም
- ሴት የላከው በር አያንኳኳም
- ሴት የላከው አልቃይዳን አይፈራም
- ሴት የላከው ጅብ አይፈራም
- ሴት የላከው ፓርላማ ይገባል
- ሴትየዋ እንደፈራሁት ተቀደደብኝ አለች
- ስለ ጨሰ አይነድም ስለዳመነ አይዘንብም
- ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎም ስልቻ
- ስምህ ማነው ላገር አይመች ማን አወጣልህ ጎረቤቶች
- ስምሽ ማነው ሲሏት ቂጤ ትልቅ ነው አለች
- ስምን መላክ ያወጣዋል
- ስም ከመቃብር በላይ ይቆማል
- ስም ያለው ሞኝ ነው
- ስም ይወጣል ከቤት ይሄዳል ጎረቤት
- ስም ይወጣል ከቤት ይከተላል ጎረቤት
- ስራ ለሰሪው ምርጫ ለመራጭ
- ስራ ለሰሪው እሾህ ላጣሪው
- ስራ ከመፍታት ምርጫ መወዳደር
- ስራ ከምፈታ ልጄን ላፋታ
- ስራ ያጣ መለኩሴ አደገኛ ቦዘኔ ተባለ
- ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል
- ስራ ያጣ መነኩሴ "አደገኛ ቦዘኔ" ተብሎ ታሰረ
- ስራ ያጣ መነኩሴ የምርጫ ቅስቀሳ ጀመረ
- ስራ ያጣ ቄስ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል
- ስብ ሊያርዱ ጉፋያ ይነዱ
- ስትወልድ የምትበላውን በርግዝናዋ ጨረስችው
- ስትግደረደሪ ጾምሽን እንዳታድሪ
- ስደትና አግዳሚ ሁሉንም እኩል ያረጋል
- ስጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ አንድ አለ
- ስጋው ያሳማ እንኳን ለበላው ለሰማው ገማ
- ስጋው ያሳማ ከበላው የሰማው ገማ
- ሶስቴ ከመፍሳት አንዴ መቅዘን