ደቡብ ኦሤትያ-አላኒያ
Appearance
ደቡብ ኦሤትያ-አላኒያ (ኢሮንኛ፦ /ኹሣር ኢርስቶን-አሎንስቶን/) በከፊል ተቀባይነት ያገኘ አገር ነው። ነጻነቱን በ1983 ዓ.ም. ያዋጀ ምንም ቢሆን፣ ጂዮርጂያ ግን ይግባኝ አለው።
ከተባበሩት መንግሥታት የሚከተሉት አገራት ደቡብ ኦሤትያን ተቀባይነት ሰጥተዋል፦ ሩስያ፣ ኒካራጓ (በ2000 ዓ.ም.) ፤ ቬኔዝዌላ (2001 ዓ.ም.)፣ ናውሩ (2002 ዓ.ም.)፣ ሶርያ (2010 ዓ.ም.)
በከፊል ተቀባይነት ካገኙት ሌሎች አገሮች፣ አብካዝያ፣ ትራንስኒስትሪያ እና አርጻኽ (የቀድሞው ናጎርኖ-ካራባቅ) ደቡብ ኦሤትያን እርስ በርስ ይቀበላሉ። ምዕራባዊ ሣህራ ደግሞ ደቡብ ኦሠትያን ተቀብሏል።
በተጨማሪ ቱቫሉ ከ2003 እስከ 2006 ዓ.ም. ድረስ ይቀበለው ነበር።
የተረፉት መንግሥታት የጂዮርጂያ ግዛት እንዲሆን የጂዮርጂያን ይግባኝ ተቀባዮች ናቸው።
በመጋቢት 2009 ዓም ከተደረገው ሕዝቡ ውሳኔ ቀጥሎ የሀገሩ ስም በይፋ ከ «ደቡብ-ኦሤትያ» ወደ «ደቡብ-ኦሤትያ-አላኒያ» ተቀየረ። የአገሩ ሕዝብ ከታሪካዊ አላኖች ብሔር እንደ ተወለደ ይታመናል፤ ታሪካዊውም አላኒያ ከ890-1230 ዓም ያሕል በአካባቢው የቆየ መንግሥት ነበረ።
|