መግቢያ ሐተታ
መግቢያ ሐተታ
ውክፔዲያ የተሟላ፣ ትክክለኛ እና፡ ነጻ መዝገበ ዕውቀትን በብዙ ቋንቋዎች የሚያቀርብ የትብብር ሥራ ውጤት ነው። ይህ የአማርኛው ውክፔዲያ ጥር 18 ቀን 1996 ዓመተ ምሕረት (27 January 2004 እ.ኤ.አ.) የተጀመረ ሲሆን አሁን 15,376፡ ጽሑፎችን፡ አካቶ ይዟል።
ውክፔዲያ የጋራ ነው። ማንም ሰው ለዚህ መዝገበ ዕውቀት ኣስተዋጽዖ ሊያደርግ ይችላል። አባልነት ለመግባት «መግቢያ» የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ። ጽሑፍ ለማቅረብ ወይም በአርትዖት ሥራ ለመሳተፍ ከላይ መልመጃ የሚለውን አፅቅ ይጫኑ። ለጊዜው ጥያቄ ካለወት እኒህን ነባር አባላት ፈቃደ፣ እልፍዓለም፣ ቡልጌው፣ አንዋርንና Hጌትነትን ይጠይቁ። ሆኖም ማኅበረሠቡ የተዘጋ አይመስላችሁ፤ ምንጊዜም አዳዲስ ቋሚ አቅራቢዎች ለመጨምር እየፈለግን ነው። ከዚህም ጭምር ማንም ቋሚ አቅራቢዎች ከጥቂት ልምምድ በኋላ ለመጋቢነት ሊታጩ በቀላሉ ይቻላል!
|
ታሪክ፡በዛሬው፡ዕለት።
ታሪክ፡በዛሬው፡ዕለት።
ታኅሣሥ ፲፬
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም - የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት በራስ ዕምሩ ኃይለ ሥላሴ በቡመራው የኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ የመርዝ ጢስ ረጩ፡፡
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የጃፓን አልጋወራሽ (አሁን ንጉሠ ነገሥት) አኪሂቶ እና ባለቤታቸው ልዕልት (አሁን እቴጌ) ሚቺኮ በኢትዮጵያ የአራት ቀናት ጉብኝታቸውን በዛሬው ዕለት ጀመሩ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት የብሔራዊ ዓመት በዓላት በአገሪቱ ታሪክ ዘገባ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓቢይ እስላማዊ በዓላትን እንደሚያካትቱ አውጀ።
- ፲፱፻፺፰ ዓ/ም - የሱዳን ሠራዊት በአድሬ ላይ ባካሄደው ጥቃት የመቶ ሰዎች ሕይወት ካለፈ በኋላ የቻድ መንግሥት በሱዳን ላይ ጦርነት አወጀ።
|
|
የዕለቱ፡ምርጥ፡ምስልና፡አዳዲስ፡ጽሑፎች።
የዕለቱ፡ምርጥ፡ምስልና፡አዳዲስ፡ጽሑፎች።
መጨረሻ የቀረቡ 3 ትኩስ መጣጥፎች
|
ምስል - ከኢትዮጵያ
ምስል - ከኢትዮጵያ
ይህን ያውቁ ኖሯል?
ይህን ያውቁ ኖሯል?
- የሰው ልጅ ፀጉር ዘለላ ሳይበጠስ እስከ 3 ኪሎግራም ማንጠልጠል ይችላል።
- ሴቶች ከወንዶች ሁልት እጥፍ ጊዜ ዓይናቸው ተከፍቶ ይከደናል።
- የሰው ልጅ ሳይንገዳገድ ለመቆም 300 ጡንቻወችን አንድ ላይ ማሰራት አለበት።
- በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ቲያትር ቤት የሃገር ፍቅር ቴአትር ሲሆን የተመሰረተው በ1927 የሃገር ፍቅር ማህበር በሚል ስም ነበር።
- ለመጀመሪያ ጊዜ በምንሊክ መልክ ታትመው የወጡት ገንዘቦች ስራ ላይ የዋሉት በ1886 ዓ/ም ነበር።
|
[[|]]
|
የመደቦች ዝርዝር
የመደቦች ዝርዝር
የዕለቱ ፅሑፍ
የዕለቱ ፅሑፍ
ቢግ ማክ የሃምበርገር ዓይነት ሲሆን በፈጣን ምግብ ቤቱ ማክዶናልድስ የሚሸጥ ነው። ሃምበርገሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው በ1960 ዓ.ም. በአሜሪካኑ ጅም ዴልጋቲ ነበር። ሁለት የተፈጨ የበሬ ስጋ ክቦችን፣ ሰላጣ ቅጠል፣ ዓይብ፣ ሽንኩርት፣ ፒክልስ እና ሶስት የሰሊጥ ጠፍጣፋ ዳቦዎችን ከማዋዣ የቢግ ማክ ሶስ (መረቅ) ጋር ይይዛል።
ቢግ ማክ በኣሁኑ ዘመን በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተዎዳጅነትን በማግኘቱ ዘ ኢኮኖሚስት የተሰኘው የሥነ ንዋይ ጋዜጣ በያመቱ ቢግ ማክ ኤንዴክስ የተባለ መረጃ ያትማል። ቢግ ማክ በያገሩ የሚሸጥበትን ዋጋ በማዎዳደር፣ የየአገሩን የኑሮ ውድነት ለማነጻጻር ይጠቀምበታል። |
|
[[|]]
ይጠይቁ፣ ይሳተፉ !!!
ይጠይቁ፣ ይሳተፉ !!!
ስለ ምን ለማወቅ ይፈልጉ ነበር?በዚህ ያቅርቡ።ቀልዶችን እዚህ ላይ ይጨምሩ!
can't see the Amharic font?
Click here to download the Amharic Unicode. |
|
|