ለቂቅ ሐሳብ ከውስብስብ ነገሮች ወይንም ሐሳቦች ላይ በ
አዕምሮ ተነጥሎና ተላቆ የተወሰደ ሐሳብ ማለት ነው።
በተጨባጩ ዓለም፣ የነገሮች ጸባዮች ምንጊዜም ተደባልቀው እንጅ ተለያይተው አይገኙም። ነገር ግን አዕምሮ እነዚህን ጸባዮች ከተደባለቁበት ተፈጥሮ አላቆና ነጣጥሎ መገንዘብ ይችላል። ለምሳሌ አንድን
ሎሚ ፣ ሎሚ የሚያስብሉት ፡ የብዙ ጸባዮቹ ተደባለቀው አንድ ላይ መገኘት ነው። ይሁንና አዕምሮ የዚህን ፍሬ ድብልብልነት፣ ቢጫነት፣ የሽታ ዓይነት፣ ክብደት፣ ቁጥር ብዛት ወዘተ... ነጣጥሎ ና ከሎሚው አላቆ መገንዘብ ይችላል። ይሁንና እያንዳንዳቸው ለቂቅ ሐሳቦች፣ በአለም ላይ ለብቻቸው አይገኙም፤ ማለት ቢጫነት፣ ወይንም ድቡልቡልነት ለብቻው በተጨባጩ ዓለም
ህልውና የላቸውም።