Jump to content

ገብረ መስቀል ላሊበላ

ከውክፔዲያ
(ከዓፄ ላሊበላ የተዛወረ)
== 

ዓፄ ገብረ መስቀል ላሊበላ
የአጼ ላሊበላ ምስል
የአጼ ላሊበላ ምስል
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ግዛት ከ፩ሺ፻፸፫-፩ሺ፪፻፲፫ እ.ኢ.አ.
ቀዳሚ ቅዱስ ሐርቤ
ተከታይ ዓፄ ነዓኩቶ ላሊበላ
ባለቤት መስቀል ክብረ
ልጆች ይትባረክ
ሙሉ ስም ላይለበላይ
ሥርወ-መንግሥት ዛግዌ
አባት ጃን ስዩም
ሀይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ክርስትና

==

የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት
ከዓለም አስደናቂ ሥራዎች አንዱ
ከዓለም አስደናቂ ሥራዎች አንዱ
ከፍልፍል ድንጋይ የተሠሩ
ደቡብ ምሥራቅ ቤተ መርቆሬዎስ
ሰሜን ቤተ መስቀል
ሰሜን ምሥራቅ ቤተ መድኃኔ ዓለም
ሰሜን ቤተ ሚካኤል
ሰሜን ቤተ ማርያም
ምሥራቅ ቤተ አማኑኤል
ደቡብ ምሥራቅ ቤተ አባ ሊባኖስ
ደቡብ ምሥራቅ ቤተ ደናግል
ደቡብ ምሥራቅ ቤተ ገብርኤል ወሩፋኤል
ደቡብ ምዕራብ ቤተ ጊዮርጊስ
ሰሜን ቤተ ጎለጎታ
ቤተልሔም



ዓፄ ገብረመስቀል ላሊበላ ከ1181 እስከ 1221ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩ ሲሆን በዓለም ደረጃ ታዋቂ የሆኑቱን የአለት ውቅር የሆኑትን የላሊበላ አብያተ ቤተ ክርስቲያን ሕንጻወች በማስገንባት ይታወቃሉ [1] .[2]ላሊበላ በትክክለኛ አጻጻፍ ላል-ይበላል ሲሆን ቃሉ በጥንቱ አገውኛ ‹‹ ማር ይበላል ማለት ነው›› «ንቦች ሳይቀሩ ንጉስነቱን እውቅና ሰጡ» ማለትም ነው።

ንጉስ ላሊበላ፣ ቡግና ውስጥ በሮሃ ወይንም አደፋ እንደተወለዱ ትውፊት አለ። ህጻኑን «ላሊበላ» ያለቸው እናቱ ስትሆን ይህም ምክንያቱ ህጻን እያለ ንቦች ከበውት በማየቷ ለወደፊቱ የኢትዮጵያ ንግሠ ነገሥት ለመሆኑ ምልክት ይሆናል ብላ በመተንበዮዋ ነበር። ከትውፊት አንጻር የወደፊቱ ንጉስ ከአጎቱ ታታዲም እና ከራሱ ወንድም ንጉስ ሐርቤ ጋር ባለ መስማማቱ ለስደት ተዳረገ። በመሃከሉ ግማሽ እህቱም ልትገለው መርዝ አጠጥታው ነበር። ከዚህ ሁሉ ፈተና በኋላ በራሱ በወንድሙ በንጉሱ ሐርቤ ዘመን ንጉስ ለመሆነ ስለበቃ፣ ወደ ስልጣን የወጣው በጦርነት እንደነበር ታሪክ አጥኝው ታደሰ ታምራት ይናገራል [3]

ኢየሩሳሌምመስሊሞች በ1187ዓ.ም. ሲያዝ፣ ላሊበላ በአይነ ህሊናው እየሩሳሌምን እንደተመለከተና አዲስ እየሩሳሌምን በኢትዮጵያ ለመገንባት ፍላጎት እንዳደረበት በታሪክ ይጠቀሳል። ስለሆነም ለዚህ ተግባር አሁን ላሊበላ የሚባለውን ድንቅ የአለት ፍልፍል ከተማ ለማሰራት ተሰማራ። ከላሊበላ አቅድ አንጻር ይህ አዲሱ ከተማ ኢየሩሳሌምን መምሰል ስላለበት ብዙ ቦታዎቹ ከዚህ አቅድ አንጻር ተሰይመዋል። ለምሳሌ በአካባቢው የሚፈሰው ወንዝ ዮርዳኖስ ወንዝ በመባል ይታወቃል። አዲሱ ከተማ ሮሃ፣ ከ12ኛው እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ በመሆን አገልግሏል።

ዓፄ ላሊበላ ያስገነባው የሮሃ ከተማና የአለት ውቅር ቤተከርስቲያኖቹ

ላሊበላ እኒህን11አብያተ ክርስቲያናት እንዴት እንዳስገነባ ዝርዝር መረጃ የለም። በኋላ የተጻፈው ገድለ ላሊበላ እንደሚለው ቤተ ክርስቲያኖቹ በመላዕክት እርዳታ ብቻ ላሊበላ ከአለት እንደፈለፍላቸው ያሰፍራል [4]

ተጨማሪ ንባብ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • (ፈረንሳይኛ) J. Perruchon. Vie de Lalibala, roi d'éthiopie: texte éthiopien et traduction française. Paris 1892. (Online version in Gallica website at the "Bibliothèque National Française")
  1. ^ Taddesse Tamrat, Church and State in Ethiopia (Oxford: Clarendon Press, 1972), p. 56n.
  2. ^ Getachew Mekonnen Hasen, Wollo, Yager Dibab (Addis Ababa: Nigd Matemiya Bet, 1992), p. 22.
  3. ^ Taddesse Tamrat, p. 61.
  4. ^ Richard K.P. Pankhurst in his The Ethiopian Royal Chronicles (Addis Ababa: Oxford University Press), 1967