ቤኒን
République du Bénin |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: L'Aube Nouvelle |
||||||
ቤኒን በቀይ ቀለም
|
||||||
ዋና ከተማ | ፖርቶ ኖቮ፣ ኮቶኑ | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ፈረንሳይኛ | |||||
መንግሥት {{{ፕሬዝዳንት |
ፓትሪስ ታሎን |
|||||
ዋና ቀናት ሐምሌ ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. (August 1, 1960 እ.ኤ.አ.) |
ነጻነት ከፈረንሳይ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
114,763[1] (100ኛ) 0.4 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት የ2013 እ.ኤ.አ. ቆጠራ |
10,653,654[2] (84ኛ) 10,008,749 |
|||||
ገንዘብ | ምዕራብ አፍሪካዊ CFA ፍራንክ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +1 | |||||
የስልክ መግቢያ | +229 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .bj |
ቤኒን ወይም በይፋ የቤኒን ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። ከምዕራብ ቶጎን፣ ከምሥራቅ ናይጄሪያን እና ከሰሜን ቡርኪና ፋሶና ኒጄርን ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ ፖርቶ ኖቮ ሲሆን የመንግሥቷ መቀመጫ ግን ኮቶኑ ከተማ ናት። የቤኒን የቆዳ ስፋት ወደ 110,000 ካሬ ኪ.ሜ. ሲሆን የሕዝቧ ብዛት ደግሞ ወደ 9.05 ሚሊዮን ይገመታል።
የቤኒን ይፋ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን እንደ ፎንና ዮሩባ የመሳሰሉት የሀገሪቷ ባህላዊ ቋንቋዎች ሰፊ ተናጋሪ አላቸው። የሮማ ካቶሊክ ክርስትና ብዙ ተከታዮች ሲኖሩት እስላሞች፣ ፕሮቴስታኖችና የቩዱ ተከታዮችም ይገኛሉ። ቤኒን የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ሕብረት እናም ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ናት።
ከ17ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን እ.ኤ.አ. የሀገሪቱ መሬት በዳሆሚ መንግሥት ነበር የሚመራው። በ17ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የአትላንቲክ የባሪያ ንግድ በአካባቢው ሰፍቶ ስለነበር ቦታው የባሪያ ጠረፍ ይባል ነበር። በ1892 እ.ኤ.አ. ፈረንሳይ አካባቢውን በመቆጣጠር የፈረንሳይ ዳሆሚ ብላ ሰየመችው። በ1960 እ.ኤ.አ. ዳሆሚ ነፃነቷን በማግኘት ለ፲፪ ዓመታት በዴሞክራሲያዊ መንግሥት ተመርታለች።
ከ1972 እስከ 1990 እ.ኤ.አ. ሀገሪቷ በማርክሲስት ሌኒኒስት አቋም የቤኒን ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ተብላ ተሰመች። በዚህ ጊዜ በሀገሪቷ የኢኮኖሚ ውድቀት ተከስቶ ነበር። በ1991 እ.ኤ.አ. የቤኒን ሪፐብሊክ ተመሠረተ።
ቤኒን ወደ ውጭ የሚልከው ዋንኛ ምርት ጥጥ ሲሆን ከዚህ በላይ ካሸው ለውዝ (Anacardium occidentale)፣ ኮኮነት፣ ዓሳ፣ እንጨት ወደ ውጭ ይላካሉ። ፔትሮሊየምና ወርቅም ይላካሉ። ባለፉት ዓመታት ውስጥ ቤኒን ለተግባራዊ ሳይንስ ምርመራ ጥናት አንጋፋ ማዕከል ሆናለች።
በደቡብ ቤኒን ባሕላዊ አበሳሰል፣ በተለይ የበቆሎ ዳቦ በኦቾሎኒ ወጥ ወይም በቲማቲም ወጥ ይጠቀማል። አሳ እና ዶሮ ከሁሉ ተራ ሥጋዎች ናቸው፣ በሬ፣ ፍየልና የጫካ አይጥ ደግሞ ይበላሉ። በስሜን ቤኒን ባሕላዊ አበሳሰል፣ በተለይ ኮቴሃሬ በበቆሎው ፈንታ ይጠቀማል። ቤሬ ወይም አሳማ በጥብስ ወይም በወጣወጥ፣ ፎርማጆ፣ ኩስኩስ፣ ሩዝ፣ ባቄላ፣ ፍራፍሬ በሰፊው ይጠቀማሉ።
እግር ኳስ ከሁሉ የሚወድ እስፖርት ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ቤስቦል ወደ ቤኒን ገብቷል።
- ^ (PDF) Demographic Yearbook – Table 3: Population by sex, rate of population increase, surface area and density. United Nations Statistics Division. 2012. http://unstats.un.org/unsd/demographic/products/dyb/dyb2012/Table03.pdf በ3 September 2017 የተቃኘ. http://unstats.un.org/unsd/demographic/products/dyb/dyb2012.htm
- ^ http://www.insae-bj.org/Migration.html?file=files/stats-demographiques/STATISTIQUES%20DEMOGRAPHIQUES.xlsx
|