ግሪክ (አገር)

ከውክፔዲያ

Ελληνική Δημοκρατία
የግሪክ ዲሞክራሲ

የግሪክ ሰንደቅ ዓላማ የግሪክ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር Ύμνος εις την Ελευθερίαν

የግሪክመገኛ
የግሪክመገኛ
ዋና ከተማ አቴና
ብሔራዊ ቋንቋዎች ግሪክ
መንግሥት
ፕሬዝዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር
ፓርለሜንታዊ ሪፐብሊክ
ካሮሎስ ፓፑሊያስ
ኮስታስ ካራማንሊስ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
131,990 (95ኛ)
የሕዝብ ብዛት
የ2015 እ.ኤ.አ. ግምት
 
10,955,000 (80ኛ)
ገንዘብ ዩሮ (€)
ሰዓት ክልል UTC +2
የስልክ መግቢያ +30
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .gr
.ελ


መልከዐምድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ግሪክ ወደ ሜዴቴሪኒያን ባሕር የተዘረጋ አንድ ትንሽ አገር ነው። ከምሥራቅ ወደ ትንሽ እስያ፤ ከምዕራብ ወደ ኢጣሊያ አገር ከሁለቱም ወገን ርቀቱ ትክክል ነው። ግሪክ በሰሜን ወገን ከመቄዶንያ ይዋሰናል። ግሪክ ኣብዛኛው በባሕር የታጠረ ነው።

በደቡብና በምሥራቅ ወገን አያሌ ደሴቶች አሉ። ከእነርሱም በአያሌዎቹ መንደሮችና ከተሞች ተሠርተውባቸዋል። አንዱ አንቲፖሮስ ይባላል። በእዚህም ስፍራ ያለው ታላቅ ያጌጠ ዋሻ የታወቀ ስመ ጥሩ ነው። እኩሌቶቹም የግሪክ ደሴቶች ከባሕር ወደ ውጪ እየተወረወሩ የወጡ ይመስላሉ። እኩሌቶቹም ከጥንት ጀምረው ይታዩ የነበሩት ያሉበት አይታወቅም ጠፍተዋል። ይህ እንግዳ ነገር እንዲህ እንዲሆን ያደረገው ከባሕር በታች የተነሳው እሳተ ገሞራ ነው።

በደቡብ ግሪክ ወገን ባሉት ደሴቶች አየሩ በአሜሪካ እንዳለው እንደ ቨርጂኒያ ግዛት አየር ቀላል ነው። በዚህ አገር ብዙ አይነት ፍሬ ሁሉ ሞልቶዋል። በሰሜን በኩል ደግሞ አየሩ ቅዝቃዜ ያለበት ነው።

በየጠረፉ የመርከብ መቋሚያዎች ወደቦች ይገኛሉ። ብዙዎቹ የአገሩ ሰዎችም መርከበኞች ናቸው። በደኑም ፓይን (ጥድ) የተባለው ጠንካራ ዛፍ ይገኛል። በላይኛው አውራጃ ኦክ የተባለው ዛፍ ይገኛል። ወደታች ባለው ክፍልም ቸስትነትዋልነት የሚባሉት ዕንጨቶች ይገኛሉ።

በዚህ ስፍራ የሚገኘው ዋናው ነገር ደረቅ ፍራፍሬ፣ ዘቢብጥጥሐር ጠጉርሩዝትንባሆበቆሎ ነው። የእጅ ሥራ ጥቂት ነው። በቤት የተለመደ ሥራ እንደ ጥጥ እንደ ጠጉር እንደ ሐር የመሰለ ነገር ነው። ቀለም ማግባት ወይም መቀባት በጣም የተለመደ ከሆነ ብዙ ጊዜው ሆነው።

ከዛፎች ፍሬ ዋነኛው ወይራ ሲሆን በብዛት ይተከላል። ወይን፣ በኽረ? ሎሚበለስ፣ አልሞንድ (ለውዝ)፣ ተምርሴትሮን፣ ፓሜግራኔት (ሮማን)፣ ኩሬንትም ይበቅላሉ።