Jump to content

ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
መስመር፡ 318፦ መስመር፡ 318፦
*[http://www.pageglimpse.com/geezedit.com] GeezEdit
*[http://www.pageglimpse.com/geezedit.com] GeezEdit
*[http://www.ethiopian-this-week.com/] Ethiopian This Week
*[http://www.ethiopian-this-week.com/] Ethiopian This Week
*[http://www.ethiopian-this-week.com/feeds/posts/default?orderby=updated] Ethiopian Celebrities
*[http://ethiopiancelebrity.blogspot.com/2014_11_01_archive.html]
*[http://factualworld.com/article/List_of_veterinarians] Veterinarians
*[http://luc.devroye.org/fonts-32322.html] Typeface
*[http://factgrabber.com/index.php?q=Ethiopian_American&lcid=ZqHmgSaxB5EHGSbJZJFkmeapZrFkiYaJhsknucbJ5hkm] Ethiopian American
*[https://twitter.com/GeezEdit] Twitter
*[http://www.frequency.com/video/geezedit-typing-by-dr-aberra-molla/151882977/-/5-258] Video
*[http://ethiograph.com/album/displayimage.php?pid=316]
*[http://www.nazret.com/directory/index.php?c=35]
*[https://ia902707.us.archive.org/29/items/December72014p_888/Dec72014p.mp3] Interview Audio
*[https://ia902707.us.archive.org/29/items/December72014p_888/Dec72014p.mp3] Interview Audio
*[http://www.ethiopian-this-week.com/2014/12/part-i-interview-with-founder-of.html] Interview in Amharic
*[http://www.ethiopian-this-week.com/2014/12/part-i-interview-with-founder-of.html] Interview in Amharic
መስመር፡ 324፦ መስመር፡ 333፦
*[http://www.toonfirst.com/new-paid-apps/play-geezedit] Approbatics
*[http://www.toonfirst.com/new-paid-apps/play-geezedit] Approbatics
*[http://www.approbatics.com/] Approbatics
*[http://www.approbatics.com/] Approbatics
*[https://itunes.apple.com/app/id935624754] GeezEdit iPhone 6 App Amharic Typing by Aberra Molla
*[http://ethiopianamericanforum.com/] Ethiopian American Forum, GeezEdit on the App Store on iTunes
*[http://ethiopianamericanforum.com/] Ethiopian American Forum, GeezEdit on the App Store on iTunes
*[http://www.amharicmovies.com/bio/unsung-heroes] Unsung Heroes
*[http://www.amharicmovies.com/bio/unsung-heroes] Unsung Heroes

እትም በ17:24, 22 ዲሴምበር 2014

ዶ/ር ኣበራ ሞላ

ዶ/ር ኣበራ ሞላ መጋቢት ፳፬ ቀን ፲፱፻፵ ዓ.ም. የተወለዱ ኢትዮጵያዊ ናቸው።

ግዕዝ በኮምፕዩተር

ዶ/ር አበራ በኮምፕዩተር ግዕዝ ፊደልን ለመጀመሪያ ጊዜ መጠቀም እንዲቻል ያደረጉ ምሑር ናቸው። ይሀንንም ያደረጉት የዓማርኛውን የጽሕፈት መሣሪያ (ታይፕራይተር) ለሚያውቁት ቀላል እንዲሆን በ“a”፣ “b”፣ “c”፣ “d” ምትክ “ሀ”፣ “ጠ”፣ “ሸ”፣ “ዘ” እና እንግሊዝኛ ለሚያውቁ በ“A”፣ “B”፣ “C”፣ “D” ምትክ “አ”፣ “በ”፣ “ቸ”፣ “ደ” ቀለሞችን በመመደብ ዓይነት ሰላሳ ሰባቱን የግዕዝ ቤት ሆህያት ለ፴፯ የኮምፕዩተር መርገጫዎች ስሞችም በማድረግ ነበር። ስምንቱን የፊደል ቤቶች ወይም እንዚራን ስምንት ፎንቶች ላይ በተኑዋቸው። በእዚህ ዘዴ በእጅ ጽሑፍና ማተሚያ ቤቶች ብቻ ይታተሙ የነበሩት የግዕዝ (Ethiopic) ፊደላት ለመጀመሪያ ጊዜ በኮምፕዩተር ተከተቡ። ሞዴት በመባል የታወቀውን የቃላት ማተሚያ የማይክሮሶፍትን ዶስ በመጠቀም በ፲፱፻፹ ዓ.ም. ኣሜሪካ ውስጥ ለገበያ ኣቀረቡ። ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲከተብ የፈጠሩበትን ዘዴ በዩናይትድ እስቴትስ ፓተንት መጠበቅ ቢችሉም በእዚያን ጊዜ ኢትዮጵያ የፓተንት ሕግ ስላልነበራት የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ሕጉ ሲወጣ ጉዳዩ ይታያል በማለት ስለወሰነ [1] ፓተንት ኣልወጣለትም።

ግዕዝ ድምጻዊ ፊደል ስለሆነ እያንዳንዱን ቀለም እየደረደሩ ማተም ከ፲፱፻ ዓ.ም. ገደማ ጀምሮ ማተሚያ ቤቶች ሊጠቀሙበት ችለዋል። በቀለሞቹ ብዛት የተነሳ ግን የእንግሊዝኛውን የጽሕፈት መሣሪያ ለዓማርኛ እንኳን መጠቀም ኣልተቻለም። ከዳግማዊ ምኒልክ ጀምሮ [2] ብዙ ኢትዮጵያውያን ሊቆች፣ ሚኒስትሮችና ደራስያን የእንግሊዝኛውን የታይፕ መጻፊያ ለዓማርኛ መክተቢያ እንዲያገለግል ወደ ሰማንያ ዓመታት ግድም ሲመራመሩ ቆይተው ባይሳካላቸውም [3] ዶ/ር ኣበራ ትግሎቻቸውን በኮምፕዩተር ኣሳክተዋል። ስለ ዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ምርምሩም የዋቢው ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት አባ ተክለ ማሪያም ሰምሃራይ፣ ክቡር ዶ/ር ሃዲስ ኣለማየሁ፣ ኣቶ ዓለሙ ኃብተ ሚካኤል፣ ኢንጂነር ኣያና ብሩ፣ ዶ/ር ዓለመ ወርቅ፣ ኣለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ክቡር ኣቶ ኣበበ ረታ፣ ክቡር ራስ ዕምሩ ኃይለ ሥላሴ፣ ዶ/ር ሉባክ፣ ኣቶ ዘውዴ ገብረ መድኅን፣ ብላታ መርስኤ ሃዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ፀሓፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ፣ ክቡር ኣቶ ሚሊዮን ነቅንቅ፣ አቶ ስይፉ ፈለቀ፣ ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል፣ ኣቶ ሳሙኤል ተረፈ፣ ሌላ እነ ኮሎኔል ታምራት ይገዙኣለቃ ለማ፡ ኣቶ ብርሃኑ ድንቄብላታ ዘውዴ በላይነህ፣ የኔታ ኣስረስ የኔሰው እና ዶ/ር ፍቅሬ ዮሴፍንም ያጠቃልላል። ይህ ድካማቸው በመጨረሻ ሊሳካ የቻለው ግን ዶክተሩ ምንም ቀለም ሳይቀንሱ ወይም መልካቸውን ሳይቀይሩ የጥንቱንና ትክክለኛ የግዕዝ ቀለሞች [4] በኮምፕዩተር እንዲቀርቡ ስላደረጉ ነው። [5] [6] በተጨማሪም የቢለንጉራጌ እና ሳሆ ምሑራን የቋንቋ ፊደሎቻቸውን እንዲጨምሩላቸው ናሙና ጽሑፎችን ልከውላቸዋል። ከእዚሁ ጋር በማያያዝ እያንዳንዱ ቀለም በሁለት መርገጫዎች እንዲከተብ ኣዲስ የኣከታተብ ዘዴ ፈጥረው ኣዳዲስ የፊደል ገበታዎች ኣቅርበዋል። ለእያንዳንዱ የግዕዝ ቤት ቀለምም እንደ አንግሊዝኛው ቍልፎች የእራሱ ቍልፍና የቍልፍ ስም መድበዋል። በእነዚህ የተነሳ የግዕዝን ፊደል የእንግሊዝኛው ወይም የኣማርኛ የታይፕ መጻፊያ መጻፍ ስላልቻለና ሳይጽፈው ኮምፕዩተር ለመጀመሪያ ጊዜ ደርሶለታል። [7] [8]

የግዕዝን ቀለም (Glyph) በኮምፕዩተር በቀላሉና በቀልጣፋ ዘዴ ማቅረብ ስለቻሉ ሕዝቡ ከማተሚያ ቤቶች በተሻለ ሁኔታ በፊደሉ መሥራት ችሏል። ዘዴውም በዓማርኛ ሳይወሰን ለሁሉም የግዕዝ ቀለሞች መክተቢያና ማተሚያ ከሌሎች የዓለም ፊደላት እኩልና ጎን በሚገባ ሥራ ላይ እየዋለ ነው። [9] ይህ የዓማርኛ ውክፔዲያ ገጽ እንደ ሌሎች ትክክለኛ ገጾች የቀረበውም በግዕዝ የዩኒኮድ መደብ ቀለሞች ነው። ሌላው የትግርኛ ውክፔዲያ ገጽ ነው። የዶ/ር ኣበራ ፈጠራዎች በግዕዝ ሳይወሰኑ ለኣንዳንድ የዓለም ፊደሎች ኣዳዲስ ኣጠቃቀሞችና ፈጠራዎች እየጠቀሙ ናቸው። [10]

የግዕዝ ቀለሞች

ከልጃቸው ብሩክ ጋር የመጀመሪያውን የግዕዝ የእስክሪንና የማተሚያ ቀለሞች ለመሥራት ኣንድ ዓመት ግድም ነበር የወሰደው። የፊደሉም ችሎታ በማደግ መጀመሪያ ፖስትእስክሪፕት ከእዚያም በ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. ትሩታይፕ [11] በኋላም ተንቀሳቃሽ (Embeddable) ሆኗል። ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ የስምንት እንግሊዝኛ ሥፍራዎችን በማስለቀቅ ዓይነት ኣንዱኑ ቦታ በየተራ በመጋራት ነበር። በዩኒኮድ መፈጠር የተነሳ እያንዳንዱ ቀለም የእራሱን ስፍራ ኣግኝቷል። [12] ብዙዎቹ የግዕዝ ቀለሞች በዓለም የፊደላት መደብ ዕውቅና ከኣገኙበት ከ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ወዲህ ግን የዕውቀት ክምችት እንዲስፋፋ እንደመጠቀም ዛሬም ኋላቀር በሆነው የአማርኛ የታይፕ መጻፊያው ዓይነት ቅጥልጥል የአማርኛ ፊደላት እየጻፉ ኢትዮጵያንና እራሳቸውን ወደኋላ እየጎተቱ ያሉትን እየተቃወሙ ነው። [13] ፊደሉንም ለማሟላትና ከሌሎች ፊደላት እኩል እንዲራመዱ በየጊዜው ጽፈዋል። ለምሳሌ ያህል እነ “ሀ”፣ “ሐ”፣ “ኀ”፣ “አ”፣ እና “ዐ” የተሳሳቱ ድምጾች ተሰጣቸው እንጂ በዶ/ር ኣበራ ገለጻ የእየራዕቦቻቸው ሞክሼዎች ስላልሆኑ ለማጥፋት ማዘጋጀት ቀርቶ ድምጾቻቸውን ተረክበው መብታቸው መከበር ኣለበት ነው። ዓማርኛ፣ ቤንችና ጉሙዝ የቋንቋ ዋና ክፍሎች የ"ጨ" ቀለሞች፣ እንዚራንና ዘመዶች ቀለበቶች ሦስት ሳይሆኑ ሁለት ናቸው። የ“ሀ” ትክክለኛ ድምጽ “ኸ” በመሆኑና “ኸ”ም የዓማርኛ ሞክሼ ቀለም ስለሆነ ነው ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝ ሲደረግ የምልክት መርገጫዎች ላይ የፊደል ስም የተሰጠው። የ“አ” ድምጽ በስሕተት “ኧረ” የሚለው ቃል ውስጥ ስንጠቀምበት የነበረ ድምጽ ስለሆነ ለ“ኧ” ስምትንተኛው የ“አ” ቤት ፊደል ድምጹን ዶክተሩ መልሰው ኣስረክበውታል። “ኧረ” መከተብ ያለበት በ“አረ” ነው። ምክንያቱም የስምንተኛው ድምጽ ቀለም የሚሠ'ራው ግዕዙ ወይም ራብዑ ላይ መስመር በመጨመር ስለሆነና የ“አ” ቤት ስምንተኛ ቀለም የማይኖርበት ምክንያት ስለሌለ ነው። ይህ የዓይኑ “ዐ” ባለመስመር “ዓ”ንም ሊመለከት ይችላል። የ“የ”ም ስምንተኛ ድምጽ ቀለም ኣለ። “ጯ” የተሠራው ቀለበት በሌለው “ጨ” ላይ በሚቀጠል ጫማ ነው። ግዕዝ ድምጻዊ ፊደል (Syllabic) ስለሆነ “ሀ” እና “ሃ” ወይም “አ” እና “ኣ” ድምጽ ስለማይጋሩ ነው ዶክተሩ ስማቸውን “ኣበራ” እንጂ “አበራ” በማለት የማይጽፉት። [14] እንዲሁም “ሰረቀ” እና “ሠረቀ” የሚባሉት ቃላት ከግዕዝ የተወረሱ ስለሆኑ ትርጕሞቻቸው ኣንድ ኣይደለም። ለግዕዝ የሚያስፈልጉትን በመጨማመር ከፈጠሯቸው የግዕዝ ምልክቶች መካክል መብት፣ ንግድ፣ ተመዝግቧል፣ ብር፣ ሳንቲም፣ ማጥበቂያ፣ ማላልያና ኣልቦ ኣኃዝ ይገኙበታል። የኮምፕዩተር 42 እንግሊዝኛ ቁጥሮችና ምልክቶች ከግዕዙ ጋር ያቀረቡት ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያድርጉ ለግዕዝ ሥራ እንዲያገለግሉ ወስነው ከግዕዙ ቀለሞች ጋር በተመጣጠነ መልክ መሥራት ስለጀመሩ ኮምፕዩተር ገበታ ላይ ያሉት ኣጠቃቀም የግዕዝም ነው። በእጅ ጽሑፍና ማተሚያ ቤቶች ብቻ ይቀርብ የነበረው የግዕዝ ፊደል በ፲፱፻፹ ገደማ ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ ኣጠቃቀሙ ወደ ኮምፕዩተር ዞሯል። ከእዚያም ወዲህ ፊደሉ የዩኒኮድ የዓለም ፊደላት መደብ ውስጥ ስለገባ እያንዳንዱ ቀለም የእራሱ ስፍራ ኣለው። [15]

የግዕዝ ቁልፎች

ምንም እንኳን ከ“A” እስከ “Z” የኣሉት የኮምፕዩተሩ መርገጫዎች (Keys) ለእንግሊዝኛው ፊደላት ስምና መርገጫ እንዲሆኑ ቢሠሩም ፴፯ቱን መርገጫዎች ለ፴፯ቱ የግዕዝ ቤት ቀለሞች ማለትም ለ“ሀ”፣ “ለ”፣ “ሐ”፣ “መ”፣ “ሠ”፣ “ረ”፣ “ሰ”፣ “ሸ”፣ “ቀ”፣ “ቐ”፣ “በ”፣ “ቨ”፣ “ተ”፣ “ቸ”፣ “ኀ”፣ “ነ”፣ “ኘ”፣ “አ”፣ “ከ’፣ “ኸ”፣ “ወ”፣ “ዐ”፣ “ዘ”፣ “ዠ”፣ “የ”፣ “ደ”፣ “ዸ”፣ “ጀ”፣ “ገ’፣ “ጘ”፣ “ጠ”፣ “ጨ”፣ “ጰ”፣ “ጸ”፣ “ፀ”፣ “ፈ” እና “ፐ” ስምና ቁልፎች እንዲሆኑ ኣድርገዋል። ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲጠቀም ሲፈጥሩ እያንዳንዱ ቀለም የሚከተበው በሁለት መርገጫዎች ነበር። ለሚፈልጉትም የቍልፍ መለጠፊያዎች ነበሩት። እያንዳንዱ የግዕዝ ቀለም ስም የሚከተበው እንደ እንግሊዝኛው ዝቅ (Shift) መርገጫን በመጠቀም ነው። በኣሁኑ ጊዜ እያንዳንዱን ቀለም በኣንድና ሁለት መርገጫዎች መክተብ የሚያስችል ኣብሻ (ABSHA) የሚባል ዘዴ ስለፈጠሩ ዓማርኛውን በእንግሊዝኛ ፎነቲክ እስፔሊንግ እንጽፋለን በማለትና ያም ስላልተሳካ እስከ ኣራት መርገጫዎች መጠቀም እንደማያስፈልግ ተደርሶበታል። [16] ምክንያቱም ዓማርኛው በኣራት ቢከተብም የኣናሳ ቋንቋዎችን በእዚሁ እስፔሊንግ ዘዴ ለመክተብ እስከ ስምንት መርገጫዎችን መጠቀም ስለሚያስፈልግ ነው። [17] [18] en:English-language_spelling_reform ላቲን “ቸ” ቀለምን የሚከትበው በ“CH” ሲሆን “ቸ” ቀለም ቢኖረው ኖሮ ትክክለኛ ኣጠቃቀም ስለሆነ ኣንድ መርገጫ ይሰጠው ነበር።

ዩኒኮድ

ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ የስምንት እንግሊዝኛ ሥፍራዎችን በማስለቀቅ ዓይነት ኣንዱኑ ቦታ በየተራ በመጋራት ነበር። በዩኒኮድ (Unicode) መፈጠር የተነሳ እያንዳንዱ ቀለም የእራሱን ስፍራ ኣግኝቷል። ጥንትም ቢሆን እያንዳንዱ ቀለም የግሉ የሆነ ከ1 እስከ 5600 ቍጥር ኣለው። በተጨማሪም ትክክለኛዎቹና ሁሉም የግዕዝ ቀለሞች ዩኒኮድ የዓለም ፊደላት መደብ እንዲገቡ በማቅረብና በመጻፍ ትልቅ ኣስተዋጽዖ ኣድርገዋል። ይህ ሊሆን የቻለውም የዓለም ፊደላትን ዩኒኮድ የተባለ የፊደላት መደብ ውስጥ ሁሉም የዓለም ቀለሞች ዕውቅና እንዲያገኙ በ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ለተቋቋመ ድርጅት ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ ያደረጉትንና ያቀረቡትን ብዙ መቶዎች ትክክለኛ ቀለሞች [19] [20] በማስጣል ሌሎች ዓማርኛ ፊደል ያልሆነውንና ዓማርኛን የማያስጽፈውን ኢንጂነር ኣያና ብሩ የሠሩትን ዓይነት ቅጥልጥል ፊደል ተሳስተው ዓማርኛና ግዕዝ ነው ብለው ስላቀረቡ ነበር። መቶ ሃያ ስምንት ስፍራዎች ይበቃሉ በማለት ለዩኒኮድ ኣቅርበው የነበረውን በመቃወምና ጽፈው በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. ኣስጥለዋል። [21] ይኽንንም በማድረጋቸውና ኢትዮጵያውያን በፊደላቸውና ቋንቋዎቿቸው በኮምፕዩተር እንዲጠቀሙ ስለፈጠሩ ለግዕዝና ኢትዮጵያ ባለውለታ መሆናቸው ከመጻፉ ሌላ የግዕዝ ኣባት የሚል የቅጽል ስም ተሰጥቷቸዋል። [22] [23] [24] [25] [26] [27] [28] [29] [30] [31] [32] [33] [34] [35] በሁለተኛ ዙር ይህ የፊደል መቀጠል ጥፋት እንደገና ተደግሞ [36] 364 ብቻ ግዕዝ፣ ዓማርኛ፣ ትግርኛና ኦሮሚፋ ቀለሞች ለዩኒኮድ በሌሎች ስለቀረቡ ይኸንንም ተቃውመውና ጽፈው [37] [38] በሦስተኛ ዙር ማሻሻያዎችም ከ55 በላይ የጉራጌ፣ ኣገው/ቢለንና የመሳሰሉት የኣናሳ ቋንቋዎች የግዕዝ ቀለሞች ዕውቅና እንዲያገኙ ቢጽፉምና [39] በትብብር ቢሳካም ሌሎች በጀመሩት ጠንቅ ግዕዝ ኣራት ስፍራዎች ተበትኖ ለዩኒኮድ ቀርቧል። [40] [41] [42] [43] [44] [45] [46] ዶ/ር ኣበራ ለግዕዝ መብት ባይቆሙለት ኖሮ [47] [48] [49] የኣማርኛ መጻፊያው መኪና ኣስቸጋሪ ኣከታተብና ያልተሟላ ቁርጥራጭ ፊደል ተሻሽሎም ቢሆን ስሕተቱ እንደሚቀጥል ጽፈው የዩኒኮድ ፊደል ሆኖ ኢትዮጵያ ከማትወጣበት ዘላቂ ችግር ውስጥ ከመውደቅ ኣትድንም ነበር። [50] [51] በኣሁኑ ጊዜ ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ያገኙትን የቢለንቤንችምኢንሙርሲሱሪትግረትግርኛኣገውኣውንጂኦሮሚፋዓማርኛዲዚዳውሮጉሙዝጉራጌጋሞ ጎፋ እና ግዕዝ ቋንቋዎች የሚጋሯቸውን ቀለሞችና ሌሎች ያጠቃልላል። በፊደሉ ከሚጠቀሙ ቋንቋዎች መካከል ሓረሪ ኣንዱ ነው። መጽሓፍ ቅዱስ ሙሉዉን ወይም በከፊል ከ፲፭፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ በግዕዝ ቀለሞች በማተሚያ ቤቶች ከታተሙባቸው ቋንቋዎች መካከል ሃዲያሲዳሞከምባታኦሮሞወላይታ እና ጌዴኦ ይገኙበታል። [52] [53] የግዕዝ ፊደል ኢትዮጵያዊው ሊቅ ኦነሲሞስ ነሲብ የኦሮሚፋውን መጫፈ ቁልቁሉ በግዕዝ ፊደል ሲጽፉ የፈጠሩትን "ዸ" ቀለምና እንዚራኖቹን ይጨምራል። [54] ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ ያደረጉት ትክክለኛውና ታግለው ከኣጥፊዎች ያቆዩልንና የግዕዝ ቀለሞቻችን የተለያዩ መልኮች እዚህ ኣጓዳኝ [55] ማየት ይቻላል። እንዲህም ሆኖ ደራስያን በሚያውቁት ቀለም ዓማርኛውን የመክተብ መብት ቢኖራቸውም ቀለማቱ በዩኒኮድ ዕውቅና ስላገኙ ፊደል መቀነስ ያስፈልጋል የሚባለው ክርክር ኣትክትሟል።

ግዕዝ ወደ ዩኒኮድ ሲገባ ኣስዋጽዖ ካደረጉት መካከል ዶ/ር ፒ. ማክክሉር፣ ኢ/ር ጆ. ቤከር፣ ኢ/ር ሎይድ ኣንድርሰን፣ ኢ/ር ግሌን ኣዳምስ፣ ዶ/ር በቀለ ሞላ፣ ጌታቸው ሞላ፣ ኢ/ር ፍሰሓ ኣጥላው፣ ኢ/ር ታከለ ኣድነው፣ ኢ/ር ፀሓይ ደመቀ፣ ዶ/ር ይጥና ፍርድይወቅ፣ ኢ/ር ግሩም ከተማ፣ ኢ/ር ቴዎድሮስ ኪዳኔ፣ ዶ/ር ሳሙኤል ክንዴ፣ ኢ/ር ተረፈ ራስወርቅ፣ ኢ/ር ተሻገር ተስፋዬ፣ ኢ/ር ታደሰ ፀጋዬ፡ ኢ/ር ማቲዎስ ወርቁ፣ ኢ/ር ኣባስ ዓለምነህ፣ ኢ/ር ዳንኤል ያዕቆብ፣ ኢ/ር ዮናስ ፍሰሓ፣ ዶ/ር ኣርዓያ ኣምሳሉ፣ ማይክል ኤቨርሰን፣ ኢ/ር ዳዊት ብርሃኑ፣ ኢ/ር ኤፍሬም ተክሌ፣ ኢ/ር እስክንድር ሳህሌ፣ ኢ/ር ዮናኤል ተክሉ እና የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ይገኙበታል።

ግዕዝ ኣረጋገጥ

ዶ/ር ኣበራ ግዕዝን ለመጀመሪያ ጊዜ በኮምፕዩተር እንዲከተብ ሲፈጥሩ እያንዳንዱ ቀለም የትኛው ቍልፍ ላይ መመደብ እንዳለበትም ፈጥረዋል። [56] [57] ከእዚያም ወዲህ ኣመዳደቦቹ እንዳስፈላጊነታቸው በኢትዮወርድ (EthioWord) እና ግዕዝኤዲት (GeezEdit) ተሻሽለው ቀርበዋል።

የመድን ማነስ

ከእዚህ ሌላ በእንስሳት ሕክምና ሙያቸውም በተለይ በኢምዩን ደፊሸንሲ ፓተንቶችና ባበረከቱት Immune Deficiency Patent 4,501,816 [58] 2,127,963 ፈውስ [59] ይታወቃሉ። በኣደረጉት ምርምርና ውጤት ኢምዩን ደፊሸንሲን በማስወገድ [60] በየዓመቱ ሲጠፉ የነበሩትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕይወትን [61] እ.ኤ.ኣ. ከ፲፱፻፸፰ ወዲህ ማትረፍ ተችሏል። ከሰው ልጅ እናቶችና ከኣንዳንድ የጦጣ ዝርያዎች በስተቀር የሌሎች እንስሳት ማህጸኖች ኢምዩኖግሎቡሊን (Immunoglobulin) የሚባለውን የበሽታ መከላከያ ፕሮቲን ለጽንሶቻቸው በእርግዝና ጊዜ ኣያስተላልፉም። ኣጥቢ እንስሳት በእርግዝና ጊዜ በኣካባቢው ለሚገኙት በሽታዎች መከላከያዎች በእንገርነት ያከማቹላቸውና ኣራሶቻቸው እንደተወለዱ ጡት ሲጠቡ የበሽታ መከላከያዎቹ ፕሮቲኖች ሳይለወጡ ከኣንጀት ወደ ደም በመግባት ለጥቂት ሳምንታት ከበሽታዎች ይከላከሉላቸዋል። ኣራሶቹ እንገሩን ሳያገኙ ከቆዩ ግን ወደ ደም መግባታቸውና መከላከያነታቸው ቀርቶ እንደ ተራ ፕሮቲን ምግብ ብቻ ይሆናል። ስለዚህ እንደ ጥጆች ያሉት ሲወለዱ የኤድስ ቫይረስ የበሽታ መከላከያቸውን እንደጨረሰ ሰው ምንም መከላከያ ስለሌላቸውና ኣካባቢው ያሉትን የበሽታ ጀርሞች እየቀማመሱ በተለያዩ በሽታዎች የእራሳቸውን መከላከያ መሥራት እስከሚጀምሩ ድረስ እየተጠቁ ኣብዛኛዎቹ ይሞታሉ። ታክመው የሚድኑትም ኣይጠረቁም። [62] [63] የዶ/ር ኣበራ የድህረ ዶክትራል ምርምር ይኸን ችግር ለመቋቋም መፍትሄ ፍለጋ ጋር የተያያዘ ነበር። [64] [65] ከላይ እንደተገለጸው በዶ/ር ኣበራ ግኝት እስከ 45 በመቶ ለዘመናት ጠንቅ ሆኖ የቆየውን መድኃኒት የሌለውን የእንስሳትን ኤድስ ዓይነት ሁኔታ መቆጣጠርና ማስወገድ ተቻለ። ምርምራቸውን ጨርሰው ያቀረቡትን መፍትሄ ሁሉም ዓውቀውት ቢጠቀሙበት የመድን ማነስ ወደ ዜሮ ከመቶ ግድም ሊወርድ ይችላል። [66] [67] [68] [69] [70] [71] [72] [73] [74] [75] የኣጋጋት ቪድዮዎች እዚህ ኣሉ። [76] [77] [78] [79]

እንገር

ጥጆች ወተት ሲጠቡ ወተቱ ትንሽ ይዘት ያለው ወተት ኣንጀት ውስጥ በቀጥታ ስለሚገባ ወደ ሦስት ሳምንት እድሜ ሞልቷቸው ሳር መቀንጠስ እንከሚጀምሩ ድረስ ጨጓራኣይነበጎ አና ሽንፍላ ሥራቸውን ኣይሠሩም የሚል እምነት በዓለም ስለነበረ ኣልጠባ ያሉትን እስቶማክ ቲዩብ በሚባል ቱቦ መጋትም ኣይጠቅምም የሚባል እምነት ነበር። ምክንያቱም እንቦሳዎች ወተት ሲጠቡ በተፈጥሮ ኢሶፋጂያል ግሩቭ የሚባል የጉሮሮ እጥፋት በኩል ወተቱ በኣቋራጭ ከጉሮሮ ወደ ወተት ኣንጀት ስለሚገባ ነው። በኣፍ በሚገባ የጨጓራ ቱቦ ውስጥ በደቂቃ ጨጓራ ውስጥ የተንቆረቆረ ኣንድ ጋለን ያህል እንገር ወደ ደም እንደሚገባ በምርምር በማረጋገጥ በመድን ማነስ (ፓሲቭ ኢምዩን ደፊሸንሲ / Passive Immune Deficiency) መነሻነት ሲከሰቱ የነበሩ ችግሮች በዶ/ር ኣበራ ለመጀመሪያ ጊዜ ተወግደዋል። [80] [81] [82] [83] ከእዚያም ወዲህ ምርምራቸው በሌሎች ምርምሮች ተረጋግጧል። [84] [85] [86] [87] [88] በእዚህ የተነሳ እንገር (Colostrum) ባለማግኘት ሊሞቱና ሊታመሙ የሚችሉትን እስቶማክ ቲዩብ ወይም ኤሶፋጊያል ቲዩብ በሚባሉ ቱቦዎች በመጠቀም እንገሩን ጥጃው እንደተወለደ በመስጠት ሕይወቱን ማዳን ተችሏል። [89] እንቦሳውም እንገሩን ቶሎ ካላገኘ ጀርሞችም ከሆድ እቃ በቀጥታ ወደ ደም ስለሚገቡ ኣደጋው ስለሚጨምር እንገሩን ጥጃው እንደተወለደ ካላገኘ ወደ ደም መግባቱም ቀስ በቀስ ስለሚቀር ጊዜና የእንገሩ መጠን ወሳኞች ናቸው። የእንቦሳ ጨጓራ እንደሚሠራ ለመጀመሪያ ጊዜ በማረጋገጥ የጥጃውን ትብብር ሳይጠይቅ በምርምራቸው የእንግር መጠንና ጊዜውን ሰው እንዲወስን ሆነ። ስለዚህ ኣልጠባ ያለን ጥጃ ዝም ብሎ መመልከትና መበሳጨት ቀርቶ ወተት ኣንጀት የማይችለውን እንገር ጨጓራ ውስጥ በማስቀመጥ ጥጃው እራሱን እንዲረዳ ኣደረጉ። የዶ/ር ኣበራ የምርምርው ውጤት ትልቅ ፈውስ ሊሆን የቻለው ጊዜ፣ ይዘትና መጠንን በኣንዴ በማካተት ስለገላገለ ነው። የጊዜ ጥቅም ጥጃው እንደተወለደ የተሰጠው ሁሉ ወደ ደሙ ስለሚያስገባ ሲሆን በእዚህ ጊዜም ወደ ደም ሊገቡ የሚችሉትን ጀርሞች ለመቅደምም ነው። ጥጃው ቢጠባም ወተት ኣንጀት በቂ ይዘት ስለሌለው የሚፈለገውን ያህል ሊጠባም ስለማይችል ጨጓራ እንደሚሠራ ስላረጋገጡ ኣንድ ጋለን እንደተወለደ በቱቦው መስጠት ስለቻሉ እንገሩ ውስጥ በቂ የመድን መጠን እንዳለ የሚጣራበት ቀላል የምርመራ ዘዴ ፈጠሩ። በተጨማሪም ሬፍራክቶሜትር የሚባል መሣሪያ የእንገርን መድን መጠን ለመገመት እንደሚጠቅም ጻፉ። [90] ግን ኣንድ ጥጃ በቂ መድን የሚኖረው ኣንድ ጋለን እንገር እንደተወለደ ስላገኘ ብቻ ሳይሆን በቂ ኢምዩኖግሎቡሊን ስላገኘ ስለሆነ እንገሩ ውስጥ በቂ እንዳለ ገበሬው ከላሟ ሳይለይ በኣንድ ደቂቃ እንገሩን መርምሮ የሚያጣራበት የምርመራ ዘዴ ፈጠሩ። የሥጋ ላሞች ግን ስለማይታለቡ ያንኑ የምርመራ ዘዴ የጥጆችን ደም በመውሰድ ገበሬው ሜዳ እንዳለ በኣንድ ደቂቃ ጥጃው በቂ መድን እንዳገኘ እንዲያጣራና ካላገኘ ቱቦውን በመጠቀም ማረም እንደሚቻል ኣቀረቡ።

እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ግን መድን ስለሌለ የግዴታ ይሞታል ማለት ኣለመሆኑንና ሲጠባ የታየ ጥጃ ሁሉ በቂ መድን ኣገኘ ማለት ኣለመሆኑን ነው። ሲጠባ የታየም ይሁን ያልታየ ጥጃ ጊዜ እንዳያልፍበት ደሙን በመመርመር የመድኑ መጠን እንዲጣራበት የእንገር መድን መመርመሪያ ኣዲሱን ዘዴያቸው ለጥጃውም ደም መመርመሪያ እንዲያገለግል ኣደረጉ። ስለ ምርምር፣ ፈጠራዎቻቸውና ኣስተዋጽዖ ከታዋቂ የዓለም የእንስሳት ሓኪሞች ኣንዱ ከመሆናቸውም ሌላ [91] [92] [93] በሽታን መከላከል ሲቻል በማከም ብቻ ስለማያምኑም የኣሜሪካና እንግሊዝ ፓተንቶች (የባለቤትነት መታወቂያ) ኣግኝተዋል። የግኝቶቻቸው ጥቅሞች [94] እዚህ በተጠቃቀሱት የተወሰኑ ኣይደሉም፦ ምሳሌ 4,501,816 ፓተንታቸው የኬሚስትሪ ፓተንቶችን ጠቅሟል። [95] ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስም ያህል የእንገር መድን መጠን ሬፍራክቶሜትር በሚባል መሣሪያ መገመት እንደሚቻል የጻፉትም [96] ከ፴ ዓመታት በኋላ ዋቢ እየሆነና መጥቀሙ ነው። [97] [98] [99]

ሕክምና

የምርምር ግኝታቸውም ጥጆች ሲታመሙም ኣዲስ የመድኃኒት፣ ምግብና ፈሳሽ መስጫ ዘዴ ሆኖ ተገኝቷል። [100] ለምሳሌ ያህል የእንቦሳ ተቅማጥ እንደ ስው ኮለራ (Cholera) ብዙ ጥቃት የሚያደርሰው ከኣካል ውስጥ ውሃ እየተመጠጠ ስለሚያልቅ ስለሆነ ውሃውን ለመተካት ጥጆቹን ሓኮም ቤት መውሰድና ማሳከም ለገበሬው ብዙ ወጪ ነበር። ከዶክተሩ ግኝት በኋላ ግን ትክክለኛውን የጨውና ስኳር መጠን ያለውን ንፁህ ውሃውን በቱቦው ማጠጣት ስለሚቻል ወጪ ቀንሷል። [101] [102] [103] ከእዚያም ወዲህ ጥቅሙ ቢጋነንም [104] የእንገር ንግድ ኣዳዲስ የዓለም ገበሬዎችና ኣምራቾቹ የገቢ ምንጭና የሕክምና ዘዴ ከመሆኑ ሌላ የሰው እናት እንገርና ወተትም ኣጠቃቀምም ተሻሽሏል። [105] [106] [107] የምርምር ውጤታቸውም ጤናማ እንስሳትን ለማሳደግ መራዳትና [108] ሓኪሞችንም ከመጥቀም ሌላ [109] [110] ለሌሎች እንስሳትም ሥራ ላይ ውሏል። ምሳሌ - [111] [112] [113] [114] [115] [116] [117]

ኤድስ

ኤድስ (Acquired Immune Deficiency Syndrome / AIDS / ኣኳየርድ ኢምዩን ደፊሸንሲ ሲይንድሮም) በዓለም ላይ መሰራጨት እንደጀመረ ክትባት እንደማይከላከለው በጊዜው ከሚያውቁት ሳይንቲስቶችና የበሽታ መከላከያ ክትባት ሠሪዎች ኣንዱ በመሆናቸው በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያስከትል ከሚችለው ጉዳት ለመከላከል ሕዝቡን ለማስተማር ባለ ኣራት ገጾች የመጀመሪያው የሆነውን ገለጻ በዓማርኛ ስለ ኤድስ በ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. ተርጕመውና ጽፈው [118] በገዛ ገንዘባቸው እያባዙና እየኣደሉ ቆይተው በኋላም በኢትዮጵያ ሪቪው መጽሔት ኣትመዋል። በእዚያን ጊዜ ስለ ግብረሥጋ ግንኙነትና ኮንዶም የሚጠቅሰውና እንዲሁም የታመሙትን መርዳት ይገባል የሚለው ጽሑፋቸው ከጊዜው ደካማ ኣስተሳሰብ የቀደመ ስለሆነ ተገቢውን ተቀባይነት ሳያገኝ ቸል ተብሎ የታለፈበት ጊዜ ስለነበረ በሽታውን በምርምር የተረጋገጠ ዕውቀትና ትምህርት መከላከል [119] ስላልተቻለ ከፍተኛ ጉዳት ኣድርሷል። ይኸንኑ ጽሑፍ ሕዝቡ እንዲያነብበት GeezEdit Amharic P የሚባል የኮምፕዩተር ፊደላቸውን በ፲፱፻፹፯ ዓ.ም. በነፃ የሰጡት ስጦታ ኣሁንም ኢንተርኔት ላይ ስለኣለ ኣንዳንዶቹ ኣልደረሱበትም እንጂ ደርሰውላቸው ነበር።

ነፃ መክተቢያ

ከቅርብ በረከትም በግዕዝኤዲት ኦንላይን (Free Typing GeezEdit Amharic Online) ዓማርኛ ሕዝቡ በነፃ በዓማርኛ መጻፍና የዓለም ድረገጾችንና የመሳሰሉትን (ኢተርኔት) በዓማርኛ መፈለግ እንዲችል አበርክተዋል። (Amharic) [120]፣ ጉግል በዓማርኛና እንግሊዝኛ፣ [121] [122] ያሁ እና ቢንግ በዓማርኛ መፈለጊያም ይገኙብታል። ቪድዮም አዚህ ኣለ። [123] የድረገጹ ፩ኛ ጥቅም ሌላ መክተቢያና እንደ ማይክሮሶፍት ወርድ [124] ወይም ፔጅስን [125] የመሳሰሉ ፕሮግራሞች (ተጠቃሚው ተመዝግቦ እያንዳንዱን በብዙ ሺህ ብሮች መግዛት ስለማይችል በእራሱ ፊደል መጠቀም እንዳይቸግረው) ኣማራጭ በማበርከት በዊንዶውስ እና ማክ ኮምፕዩተሮች በዓማርኛ ለመጻፍ ነው። ከእዚያ ጽሑፉ ኮፒ ተደርጎ ሌላ ሥፍራ ይለጠፋል። [126] የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች ጽሑፎቻችንንና የመሳሰሉትን ወደ ኢንተርኔት ማስገባትና እነዚህኑ ፈልገን ማግኘት ካልቻልን የሚከተለው ኋላ ቀርነት ቀላል ላይሆን ይችላል። ፪ኛው ኢንተርኔትን በዓማርኛና እንግሊዝኛ ወይም ቀላቅሎ ለመፈለግ በኮምፕዩተር ያገኘነውን ኣዲስ ኣጠቃቀም በሚገባ እንድንጠቀምበት ነው። ይህ ቃላትን ጽሑፍ ውስጥ ለመፈለግና ለመተካትም ይጠቅማል። ሕዝቦች በቀላሉ መጻፍ ስለሚችሉ በሰለጠኑበት የጽሑፍ ኣሠራር እንዲቀጥሉ ሲሆን ፫ኛው ጥቅም ኣንድ የዓማርኛ ጽሑፍ በቀለሙ የተጻፈ መሆኑን ለማረጋገጥና እንዳስፈላጊነቱ ለማረም ነው። በግዕዝ ቀለም ያልተጻፈ ጽሑፍ ኮፒ ተደርጎ ገጹ ላይ ሲለጠፍ ዝብርቅር እንግሊዝኛ ሆኖ ይታያል።

፬ተኛ ጥቅም ኣንዳንድ ምሑራን እንደ “ዝሆን”፣ “ኣኣ”፣ “ክኅሎት”፣ “ድድ” የመሳሰሉትን የዓማርኛ ቃላት የማያስጽፉ ድረገጾችንና የመሳሰሉትን ለመጻፊያ ከማቅረብ እንዲቆጠቡ ነው። ኣንዳንዶቹ “ኵ”ን ኣጥፍተው በ“ክው” እንደ እንግሊዝኛ እስፔሊንግ መክተብና ወጪ መጨመር ቢፈልጉም “ክው” የሚለውን ቃል መጻፍ የማይችሉ ኣሉ። ከእነዚሁ መካከል የእነ “ሐ” እና “ኀ” ቤቶች ቀለሞችን የ“ሀ” ሞክሼዎች ስለሆኑ መቀነስ እየፈለጉ ኣንዳንዶቹ “ትህትና”፣ “ትስስር”፣ “ግግር” እና “ትዝታ” የመሳሰሉትን ቃላት መክተብ ስለማይችሉ ዓማርኛውን በእንግሊዝኛ ለመክተብ ሲባል ቃላቱን ማጥፋት ይፈልጋሉ። ምሳሌ ለብዙ ዓመታት ኣለ። ኣንዳንዶቹ ግዕዝኤዲት በሁለት መርገጫዎች የሚያስከትበውን “ስስ” ቃል የሚከትቡት በሰባት መርገጫዎች ሲሆን “ፄ” ቀለምን ለመክተብ እስፔሊንጉን ማስታወስና ስድስት መርገጫዎች መጠቀም ቢያስፈልግም ሁሉንም የዓማርኛ ፊደላት ባዶ ስፍራ እየጨመሩ እንኳን ኣያስከትቡም። ዓማርኛውን መክተብ ሳይችሉ ሌሎች ቋንቋዎችን የጨመሩ ኣሉ። ፭ተኛው ጥቅም ሞክሼዎችን የማይወዱ ደራስያን ከሚወዷቸው ጋር እያምታቱ በተገኘው እንዳይጠቀሙና በተቀነሰ ፊደል እንዳይጠቀሙም ይራዳል። “ሀ” የ“ሃ” እንዲሁም “አ” የ“ኣ” ሞክሼዎች የሚመስሏቸው ኣሉ። “ኳ” እራሱን የቻለ ሞክሼ የሌለው ቀለም ነውና ጊዜና ስፍራ ማባከን ስለሆነ በ“ኩዋ” ወይም “ክዋ” መዘርዘርም ፊደል ለመቀነስ በታይፕ መጻፊያ ዘመን በኣማራጭነት የቀረበና ያኔም ቢሆን ተቀባይነት ያላገኘ ኣሁንም ቢሆን ጊዜው ያለፈበት ኋላ ቀር ኣስተሳሰብና የማያስፈልግ ግድፈት ነው። የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና “ኳ”ን ሲከትብ የነበረው “ካ” ቀኝ እግር ስር መሥመር በመጨመር በኣሌለና የተሳሳተ ቀለም በመጠቀም ነበር። ፮. በነፃ እየታደሉ በኣሉ የማያዛልቁ ኣከታተቦች ሕዝብ መታለሉ እንዳይቀጥልና እየተነገረውም እነዚያን ለምዶ በኋላ በትክክለኛ ሳይንሳዊ ኣከታተብ መጠቀም ተቸገርኩ እንዳይል ግዕዝኤዲት ይራዳል። በተጨማሪም ዓማርኛውን በቍልፎቹ ብቻ መክተብ ስላልቻሉ ቀለሞቹን ከ“ሀ” እስከ “ፖ” ደርድረው በማውስ ቀስት በመጠቆም እንዲከተቡ ማድረግ ኣያስፈልግም። ፯. ዓማርኛውን በላቲን ቀለሞች መክተብ ኣስፈላጊ ሳይሆን በተገኘው የእንግሊዝኛ እስፔሊንግ እየጻፉ ያሉትን ኣንዳንድ ጉራማይሌ ምሑራን በሚገባ በሚያውቁት ዓማርኛ ፊደልና ቋንቋቸው እንዲጽፉና እንዲያነቡ ያገለግላል። እንግሊዝኛ እስፔሊንግ ከባድ ነገር በመሆኑ ዓማርኛ እንግሊዝኛውን ሊጠቅም ስለሚችል በእንግሊዝኛ ማድበስበስ የለብንም። [127] ግዕዝ ድምጻዊ ፊደል ስለሆነ ለመነበብም ሆነ ለመከተብ እስፔሊንግ ስለማያስፈልገው ሕዝቡ ዓማርኛውን በላቲን እስፔሊንግ እንዲከትብ በብዙ መርገጫዎች ማስቀጥቀጥም ሳይስፋፋ ዓማርኛውን በዓማርኛ ፊደል ለመክተብ ግዕዝኤዲት ይጠቅማል። ምክንያቱም ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና እንዳገኘ እያወቁ ዛሬም በያይነቱ የፊደል ቁርጥራጭ የሚያቀርቡ ኣሉ። የ“ጰ” የዓማርኛ ቁቤ ኣነባበብና ኣከታተብ ካፒታል “ፒ” ("P") ነው ሲባል ተከርሞ [128] [129] [130] በቅርቡ ወደ “ፒ” ("p") እና ነቍጥ (".") ተቀይሯል ይባላል። ቴክኖሎጂውን ለዓማርኛ መፍጠር እንጂ ዓማርኛውን ለቴክኖሎጂው ኣያስፈልግም። ለላቲን ከተሠራ ቴክኖሎጂ ጋር እንዲሄድና በዓማርኛው ኪሳራ ላቲኑን ለማዳበር ሲሞከር የላቲን ተናጋሪዎች ባይናገሩ ባይገርምም የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች በዝምታ እንደማይቀበሉት ዶክተሩ ኣሳይተዋል።

፰. ግዕዝኤዲት የዓማርኛና እንግሊዝኛ መክተቢያ ነው። [131] ፈረንጆች ቋንቋዎቻቸውን በግዕዝ ፊደል እንዲከትቡ ኢትዮጵያውያን ኣልጠየቁም። ኢትዮጵያውያን ቋንቋዎቻቸውን በላቲን ፊደል እንዲከትቡ የሚፈልጉ ፈረንጆችና ኢትዮጵያውያን ግን ኣሉ። ኣንዳንድ ኢትዮጵያውያንም ነገር ስለተማታባቸው ቋንቋዎቹን መቀላቀልም ስለጀመሩ ዓማርኛውንም ሆነ እንግሊዝኛውን በሚገባ የማይናገርና የማይጽፍ ትውልድ እንዳይፈጥሩ ግዕዝኤዲት ይራዳል። [132] ፱. ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህ ዘመናት ከነፃነትዋ ጋር ጠብቃ ያቆየቻቸው ቋንቋዎችዋና የተሟሉት ቀለምዎችዋ ዛሬም በእኩልነት እያንዳንዱ ቀለምዋ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ብቻ እንዲከተብ ተደርጎ ተከባብሮና ተጋብቶ የኖረው ሕዝብ ፍላጎትና እኩልነት በኣብሻ ሥርዓት ቴክኖሎጂ ምሳሌ በግዕዝኤዲት ቀርቧል። የኣንዳንዶቹን ኣንድ ቋንቋ ቀለሞች በኣራት መርገጫዎች የሌላውን በስድስት መክተብ ወይም እንደሌሉ መርሳት የለም። ፲. የምሑራንና ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ሥራና ጥቅም ለኣለ ችግር መፍትሔ መፍጠር ነውና ዶ/ር ኣበራ ለእነዚያ የሚጠቅሙ ሠርተዋል። ኣንዳንድ የግዕዝ ተመራማሪዎች ግን በተሳሳተ ዓላማቸው ፊደሉ ለላቲን ፊደልና ገበታ እንዲስማማ መክተቢያ ሴራ መፍጠር ስለሆነ ግዕዝኤዲት ሳይንሳዊ ዓላማን በመሳት እንዳይቀጥሉ ትክክለኛውን ኣስተሳሰብ ያስገነዝባል። በቅርቡ ኣንድ የፈጠራው ትክክለኛ ኣከታተብ የገባቸው ኢትዮጵያዊ “ዶ/ር አበራ ምሥጋና ይግባውና የአማርኛ ጽሑፍ ትየባ ፍጥነቴ ከእንግሊዝኛው አያንስም” በማለት ጽፈዋል። ፲፩. ግዕዝኤዲት በዓማርኛና እንግሊዝኛ ኣከታተብ ለመማር ይጠቅማል። በዓማርኛ በብዛት የምንጠቀምባቸው ቀለሞች ሳድሳን ስለሆኑ በኣንድ መርገጫ ይከተባሉ። በብዛት ኣጠቃቀም ሁለተኛ የሆኑት ለሁለቱ ዝቅ መርገጫዎች ተመድበዋል። ለግዕዝ ተጠቃሚዎች ኢንተርኔት ላይ በነፃ ለመማርያ የቀረቡ እንግሊዝኛ ኣከታተብ መለማመጃዎችን በመጠቀም ያለኣስተማሪ በፍጥነት መክተብ መማር ይቻላል። "አ"፣ ሰ"፣፣ ደ" እና "ፈ" በግራ እጅ ጣቶች "ጀ"፣ "ከ"፣ "ለ" እና "ጠ" በቀኝ እጅ ጣቶች ይከተባሉ። ምሳሌ [133]

፲፪. ዶ/ር ኣበራ ኮምፕዩተራይዝ ያደረጉትና የታገሉለት ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ስላገኘ የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ቅጥልጥል ፊደል እንዲቀር ቢጻፍም ዓማርኛ ነው ብለው ሲያቀርቡ የነበሩና ዛሬም የሚያቀርቡ ኣሉ። [134] ግዕዝኤዲት የሚሠራው በትክክለኛ የግዕዝ ፊደላት ስለሆነ ልዩነቱን የማያውቁ እንዳይታለሉ ይጠቅማል። ፲፫. የግዕዝና ላቲን ኣከታተብ ግንኙነት የላቸውም። በላቲን “b” እና “o” ሲረገጡ “bo” ይታያሉ። በግዕዝ “bo” ሲርገጡ “ቦ” ቀለምን ሊያስከትቡ ይችላሉ። “bo” ማለት “ቦ” ኣይደለም። እንዲሁም “ቦ” “bo” ኣይደለም። በ”ቦ” ምትክ “bo” እየጻፉ የዓማርኛውን ቀለም ትተው ዓማርኛውን በላቲን ፊደል የሚጽፉ ተጠቃሚዎች ቍጥር እየጨመረ ነው። [135] ይህ የዓማርኛ ቁቤ ስለሆነ ፊደሉንና ቋንቋውን ሊያዳክማቸው ይችላል። [136] [137] [138] ተጨማሪ ምሳሌ ካስፍለገ ኣንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዓማርኛ በላቲን ፊደል እንዲጻፍና በኣጻጻፉም በግዕዝ ፊደል ምትክ በላቲን ፊደል ጽፎ ያቀረበው ጽሑፍ እዚህ [139] ኣለ። ዓማርኛን በላቲን ፊደል መጻፍና ማንበብ በኣንድ በኩል ዓማርኛንና ፊደሉን ማዳከም ሲሆን በሌላ በኩል ደካማና ኣክሳሪ የላቲንን ፊደል በዓማርኛው ፊደል መተካትን ለማስፋፋት ይመስላል። ይኸን ኣጠቃቀም ዶክተሩ ከሚቃወሙባቸው ምክንያቶች መካከል ዓማርኛን በላቲን ቀለሞች መክተብ ከዓማርኛው ቀለሞች የበዙ ቀለሞችን መጠቀምን ስለሚያስከትል ነው። "የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር" የሚለውን ርዕስ በ14 የግዕዝ ቀለሞች ማስፈር ሲቻል "yeityoPya yezemen aqoTaTer" በሚለው 28 መርገጫዎችን በመጠቀም በ24 የላቲን ቀለሞች መተካት ሁለቴ መካሰር ነው። ግዕዝኤዲት የሚከትበውም ከእዚያ በኣነሱ መርገጫዎች ነው። ሙሉ ጽሑፉን በላቲም ፊደል ከመጻፍ ይልቅ በዓማርኛ ፊደል ማስፈር ብዛቱን ወደ 64.7 በመቶ ዝቅ ያደርገዋል። ፲፬. ላቲን ለቀለሞቹ መክተቢያ የማይጠቀምበትን ከግዕዝ መጠየቅ ኣያስፈልግም፦ ምሳሌ በማውስ መክተብ። ምክንያቱም ግዕዝኤዲት ባይኖር ኖሮ ግዕዝ ሌሎች ችግሮች ውስጥ ሊወድቅ ይችል እንደነበረ ከእዚህ በላይ የተዘረዘሩት ሊቀሰቅሱን ይገባል።

ፓተንት እየተጠበቀ ወይም Patent Pending የሚለው ማሳሰቢያ ነፃው ግዕዝኤዲት ላይ ያለውና እዚህም ስለሚሸጠው ዓይነት ገለጻም ውስጥ የተጠቀሰው ሌላ ሰው በተሰጠው ወይንም በተሸጠለት እንዲጠቀም እንጂ ዘዴውን መገልበጥ ትክክል እንዳልሆነና በሕጉ መሠረት እንደሚያስቀጣም ለማስጠንቀቅ ነው። የፈጠራውን እንግሊዝኛ ገለጻ በቍጥሩ US20090179778 [140] ወይም በሚከተለው ማያያዣ http://appft.uspto.gov/netacgi/nph-Parser?Sect1=PTO2&Sect2=HITOFF&p=1&u=%2Fnetahtml%2FPTO%2Fsearch-bool.html&r=1&f=G&l=50&co1=AND&d=PG01&s1=Aberra&s2=Molla&OS=Aberra+AND+Molla&RS=Aberra+AND+Molla ማግኘት ይቻላል። ፈጠራው መጀመሪያ የቀረበውና ያተመው የዩናይት እስቴትስ መንግሥት ስለሆነ ከኢትዮጵያው ቅድሚያ ኣለው።

የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በ፲፱፻፺፪ ወይም Languages of Ethiopia, 1999 የሚል ድረገጽ SIL ያቀረበውን በመተርጎም ከእነካርታው ቀርቦ ነበር። አነዚህም 1 ኣሪ 2 ኣፋር 3 ኣላባ 4 ዓማርኛ 5 ኣንፊሎ 6 ኣኝዋክ 7 ኣርቦሬ 8 ኣርጎባ 9 ኣውንጅ 10 ባይሶ 11 ባምቤሺ 12 ባስኬቶ 14 ቤንች 15 በርታ 17 ቢራሌ 18 ኦሮሞ (ቦረና-ኣርሲ-ጉጂ) 19 ቦሮ 20 ቡርጂ 21 ቡሳ 22 ጫራ 23 ደሳነች 24 ዲሜ 25 ደራሻ 26 ዲዚ 27 ዶርዜ 28 ጉራጌ 29 ጋሞ-ጎፋ-ዳውሮ 30 ጋንዛ 31 ጋዋዳ 32 ጌዴዎ 34 ጉሙዝ 35 ሃዲያ 36 ሃመር ባና 37 ሆዞ 38 ካቻማ-ጋርጁሌ 39 ካሲፖ-ባለሲ 40 ካፊቾ 41 ከምባታ 42 ካሮ 43 ኮሞ 44 ኮንሶ 45 ኩረት 47 ኩንፈል 48 ክዋማ 49 ክዌጉ 50 ሊቢዶ 51 ማጃንግ 52 ማሌ 53 ምኢን 54 ሜሎ 55 መስመስ 56 ሙርሌ 57 ሙርሲ 59 ናዪ 60 ጉራጌ (ሶዶ) 61 ኑአር 62 ንያንጋቶም 63 ኦፑኦ 64 ኦይዳ 65 ቆቱ (ኦሮሞ) 66 ሳሆ 67 ሰዘ 68 ሻቦ 69 ሻካቾ 70 ሼኮ 71 ሲዳሞ 72 ሱማሌ 73 ሱሪ 75 ትግርኛ 76 ፃማይ 77 ኡዱክ 78 ጉራጌ (ምዕራብ) 79 ኦሮሞ (ምዕራብ-መካከለኛ) 80 ኣገው (ምዕራብ) 81 ወላይታ 82 ጫምታንግ 83 የምሳ 84 ዛይ 85 ዛይሴ-ዘርጉላ ናቸው። [142]

ጽሑፎች

ኢትዮጵያንና ጠቅላላ ዕውቀት የሚመለከቱ ጉዳዮች [143] በተለይ Ethiopic.com በየጊዜው የቀረቡ ኣሉ። ለምሳሌ ያህል፣ ስመ እጸዋት፣ [144] [145] [146] የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር፣ [147][148] [149] [150] ስመ በሽታ፣ [151] የግዕዝ ፊደል፣ [152] ስመ ኣኃዝ፣ [153] [154] ስመ አንሰሳት፣ የግዕዝ ስምና ኣኃዝ [155] ስመ ምልክቶች፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች [156] እና ግልጽ ደብዳቤ ለቫቲካን ጳጳስ ቤነዲክት ፲፮ተኛ [157] ምሳሌዎች ናቸው። [158] ሌላ ምሳሌ ለመጥቅስ ያህል የኢትዮጵያ ሚሌንየም መከበር ያለበት መስከረም ፩ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. እንጂ መስከረም ፩ ቀን ፳፻ ዓ.ም. መሆን እንዳሌለበት ኣንድ ድረገጽ ላይ ዶክተሩ ጽፈውና ኣሳምነው የኢትዮጵያ ምክር ቤት ከሰኔ ፩ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. እስከ መስከረም ፩ ቀን ፳፻ ዓ.ም. እንዲከበር የተደነገገው ስሕተት ተደርሶበት ሚሌንየሙ ዓመቱን ሙሉ እንዲከበር ተደርጓል። [159] [160] [161] በተጨማሪም ዶክተሩ በየጊዜው የሞዴትና ኢትዮወርድ መመሪያዎችን ለመክተብና ማቀነባበሪያ ከተጠቀሙባቸውና የሌሎችም ሥራዎች ሌላ ብዙ መጽሓፍት ከ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ጀምሮ ከጻፉባቸው ታዋቂ ደራስያን መካከል ዶ/ር ዓለሙ ቢፍቱ እና ዶ/ር ለይኩን ብርሃኑ ይገኙበታል። ዶ/ር በቀለ ሞላ እና ጌታቸው ሞላ ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ውስጥ ፈጣን ማተሚያ ቤት [162] የመጀመሪያው የሆነውን ግዕዝ ማተሚያ በ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ኣቋቁመው ብዙ መጽሓፍትና ጽሑፍ-ነክ ሥራዎች በሶፍትዌር ታትመዋል።

ግዕዝ ኣከታተብ

ዶክተሩ (Dr. Aberra Molla) ከ564 በላይ የሆኑትን የግዕዝ ዩኒኮድ ቀለሞች ማንኛቸውንም በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ብቻ እንዲከተቡ ለፈጠሩት ቀልጣፋና ግሩም ኣዲስ ዘዴ መረጃ Ethiopic Character Entry ፔንዲንግ ፓተንት (Pending Patent) እዚህ [163] ወይም እዚህ [164] ማንበብ ይቻላል። ኣብሻ (ABSHA) በመባል በታወቀው በእዚህ ኣዲስ የመክተቢያ ዘዴ ወይም ሥርዓት ሕዝቡ በነፃ በአማርኛ መጻፍና የዓለም ድረገጾችንና የመሳሰሉትን (ኢንተርኔት) በአማርኛ መፈለግ እንዲችል http://freetyping.geezedit.com (ፍሪታይፒንግ.ግዕዝኤዲት.ኮም) የሚባል ድረገጽ በ፳፻፪ ዓ.ም. ኣበርክተዋል። ከእዚያም ወዲህ ብዙ መቶ ሺህ ሰዎች ተጠቅመውበታል። በኣብሻ ሥርዓት ብዛቱ ከ፭፻ በላይ ከሆነው የግዕዝ ፊደል፣ ምልክት፣ ኣኃዝና ማዜሚያ ሌላ ኮምፕዩተሩ የሚጠቀምባቸውን የእንግሊዝኛ ቁጥሮችና ምልክቶችን ግዕዝ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ተጠቅሞባቸው መክተቢያዎቹ ተርፈዋል። በኣንድና ሁለት መርገጫዎች የእንግሊዝኛውን ቀለሞች እንዲከትብ የተሠራው የኮምፕዩተር የፊደል ገበታ ግዕዝን ወደ እንግሊዝኛው ዓይነት ኣከታተብ በቀረበ ዘዴ እንዲከትብ ሠርተዋል። በእዚህ ዘዴ ግዕዝ የእንግሊዝኛ እስፔሊንግ ጣጣ ውስጥ ሳይገባ የእንግሊዝኛውን የኮምፕዩተር ገበታ በመጋራት፣ በማዋሃድና ለብቻውም እንዲጠቀም ሆኗል። ይኸንንም ያደረጉት በፓተንት ማመልከቻቸው እንደጠቀሱት ግዕዝን በቀላሉና በቀለጠፈ ዘዴ መክተብ የሚያስችል ዘዴ ስላልነበረ ነው።

ነፃውና የሚሸጠው ግዕዝኤዲት ሶፍትዌር የተሸፈኑት በኣንድ የባለቤትነት መታወቂያ ስለሆነ ማስጠንቀቂያው ለሁለቱም ነው። ፓተንቱ ቢኖርም ባይኖርም ከፈጠሩት ዘዴ የተሻለ በኣሁኑ ጊዜ ስለሌለ ማንኛውምን ቀለም በሁለት መርገጫዎች መክተብም ያስችላል። ለምሳሌ ያህል በፈጠሩት ኣዲስ ዘዴ ኮምፕዩተሩ በኣለው 47 መርገጫዎች የግዕዝ ሳድሳንና ኣኃዞች በኣንድ ኣንድ መርገጫዎች ሲከተቡ ሌሎች ከ500 በላይ የሆኑት የግዕዝ ቀለሞች እያንዳንዳቸው በሁለት መርገጫዎች ይከተባሉ። [165] ስለዚህ በእዚህ ዘዴ መፈጠር የተነሳ ቀለሞችን በሁለትና ከእዚያ በላይ መርገጫዎች በመጠቀም ወይንም የግዕዝን ቀለም ላቲን በማይጠቀምበት ኣዲስና ኋላ ቀር ዘዴ እንደላቲን ቃላት በእስፔሊንግ መክተብ ኣያስፈልግም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዓማርኛውን በኣራት መርገጫዎች የሚያስከትቡ ዘዴዎችንና የኮምፕዩተር ፕሮግራሞች በነፃ በማደል እያዘናጉ በማለማመድ ላይ ያሉም ኣሉ። ይህ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች በኣራት መርገጫዎች ስለማያስከትብና ሊያዛልቅ ስለማይችል ዓማርኛውንም ሆነ እንግሊዝኛውን ሳይጠቅም ሁለቱንም ከሌሎች የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች እንዳያጣላና እንዳያስተዛዝብ ዶክተሩ የፈጠሩት ይራዳል። ግዕዝኤዲት የሚከትበው እንደ እንግሊዝኛው ኣከታተብ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ቢመስልም ከእንግሊዝኛው በተሻለ፣ በረቀቀ፣ ኃይለኛና ኣዲስ ዘዴ ስለሆነ ፊደላችንን በዓለም ላይ ለማስፋፋትና በድምጻዊነቱ ጥቅም ላይ ለማዋል በሚገባ ተዘጋጅቷል። በኣሁኑ ጊዜ ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ያገኙትን የቢለን፣ ቤንች፣ ምኢን፣ ሙርሲ፣ ሱሪ፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ ኣገው፣ ኣውንጂ፣ ኦሮሚፋ፣ ዓማርኛ፣ ዲዚ፣ ዳውሮ፣ ጉሙዝ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ ጎፋ እና ግዕዝ ቋንቋዎች የሚጋሯቸውን ቀለሞችና ሌሎችንም ያስከትባል። ግዕዝኤዲት.ኮም [166] (geezedit.com) [167] የኮሎራዶው ኣብሻ/የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ኩባንያ ሌላ የእሳቸውና ባለቤታቸው ወ/ሮ ሠናይት ከተማ ድረገጽ ነው።

የኣክሱም ሓውልት

ስለ ዶ/ር አበራ ሞላ እና የአክሱም [168] [169] [170] ሐውልት ከጣልያን ማስመለስ ጉዳይ ያውቁ ኖሯል? [171] [172] [173] Aksum [174] Obelisk of Axum [175] ጣልያኖች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከኣክሱም የዘረፉትን የኣክሱም ሓውልት እንዲመልስሱ በ፲፱፻፵ ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት ወስኖ ኢትዮጵያ እና ጣልያናም በጉዳዩ ተስማምተው ነበር። ሓውልቱ እንዲመለስ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ፣ ኮለሌል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም እና ኣቶ መለስ ዜናዊ ጠይቀው ጣልያን ለመመለስ ፈቃደኛ ኣልነበረችም። በኋላም መብረቅ እንደመታው ኣቶ መለስ ዜናዊ ቢጠይቁም ሊያናግሯቸው እንኳን ፈቃድኞች ስላልሆኑና [176] [177] ጣልያኖች ስላልመለሱት የኢትዮጵያ ወዳጆች ሓውልቱ እንዲመለስ የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ግንቦት ፳፭ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. በሮም ንግግራቸው መጠየቃቸው ይታወሳል። [178] የሮም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞም ኣለ። ቀደም ብሎም የኣንዳንድ ታዋቂ የዓለም ሰዎች፣ ኢትዮጵያውያንና የኣክሱም ሕዝብም [179] [180] [181] [182] [183] [184] የጥያቄ ፊርማ ጣልያኖችን ከኣለማስጨነቁም ሌላ [185] ሓውልቱ ከተመለሰ ሥልጣኔን እለቃለሁ የኣሉም የጣልያን ባለሥልጣንም ነበሩ። ላለመመለስ ከቀረቡት ሰበቦች ኣንዱ ሓውልቱ ጣልያን ኣገር ስለቆየ ጣልያናዊ ሆኗል፣ ገንዘብ የለንም፣ ሓውልቱ ስላረጀ ኢትዮጵያ ሲደርስ ይሰባበራል፣ በገንዘቡ ኣክሱም ያለውን ትልቁን የኣክሱም ሓውልት እንትከልበት ነበሩበት። commons:Category:Obelisk_of_Axum [186] [187] [188] ኢትዮጵያም ሓውልቱን ከፈለገች ለጣልያን መክፈል ኣለባት የኣሉም የጣልያን ኣክራሪ እንደነበሩ በኋላም ተደርሶበታል። [189]

ዶ/ር ኣበራም በግላቸው ለዩናይትድ እስቴትስ ፕሬዚደንት፣ ጥቂት ሴነተሮችና የኮንግረስ ወኪሎች እንዲረዱ የጻፉት ደብዳቤ መልስ ሳያገኝ ቀረ። በመጨረሻም ርዝመቱ 79 ጫማዎችና ክብደቱ 160 ቶን የሆነው የኣክሱም ሓውልት ሦስት ቁርጥራጮች ተደርጎ መጋዘን የተቀመጠው [190] የትም ኣይሄድም ተብሎ በማዘናጋት ኣደንዳ ቆየ። [191] ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለስ ኣሜሪካ ኣውሮፕላንና ጣልያን ገንዝብ ከለከሉ የሚለውን የጦቢያ የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. (March 4, 2004) ጽሑፍ [192] የዓዩትና የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክኸርስት በዩናይትድ እስቴትስ መማረር [193] ያላስደሰታቸው ዶ/ር ኣበራ ቅር ስለተሰኙ ሓውልቱን በትናንሹ ኣስቆርጦ ገንዘብ ከዓለም ሕዝብ ላይ በኢንተርኔት ማሰባሰብ እንደሚችሉ ኣዲስ ኣበባ ለሚገኘው የጣልያን ኤምባሲ በኢ.ሜይል የካቲቲ ፳፰ ቀን ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. ካሳወቁ በኋላ [194] ኣጣብቂኝ ውስጥ የገባው የጣልያን መንግሥት ወጪውን ከፍሎ ሓውልቱን እቦታው እንደሚተክለው ገለጸላቸው። በተጨማሪም ሌላ የጣልያን ኤምባሲ ባለሥልጣን የሆኑ ዶክተር ሓውልቱን ለማስጫን ኣውሮፕላን እያፈላለግን ነው ብለው ከጥቂት ቀናት በኋላ ለዶ/ር ኣበራ ኢ.ሜይል ላኩ። ይኸንንም ለሓውልቱ መመለስ ለኣያሌ ዓመታት ሲታገሉ ለነበሩት ፕሮፌሰር ገልጸው ቀደም ብለው ሊረዱዋቸው ስለጀመሩ ይጻጻፉ ስለነበረ ላኩላቸው። ግንኙነት ስላልነበራቸው ለኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ግን ሳያሳውቁ [195] [196] [197] ኣንዳንዶቹን ጽሑፎች ኢትዮፒክ.ኮም ድረገጻቸው ላይ ቢያስቀምጡም ብዙዎቹ ስላላነበቡት ጣልያን ወጪውን ለምን ለመክፈል እንደተስማማች ቢጻፍም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሳይታወቅ የቆየ ይመስላል። [198] [199] [200] ለኢትዮጵያ መንግሥት ግን ጣልያኖች ገንዘቡን እንደሚከፍሉ ያላሳወቁ ይመስላል። [201] በኋላም ሓውልቱ ሲመለስ እንኳን ደስ ያለዎት የሚል የምስጋና ኢ.ሜይል ለፕሮፈሰሩ ላኩ። ኤምባሲውም ዶ/ር ኣበራን ድንጋይ ከምታመላልስ ለረሃብተኛው ሕዝብ በገንዘቡ እህል ግዛበት ያለበትን ኢ.ሜይል ኣስታውሰዋቸው ሓውልቱ ኢትዮጵያ ሲደርሰ ፕሮፌሰሩ ደረሰኝ ብለው ካቀረቡት የእንግሊዝኛ ኢ.ሜይሎች መካከል የዶክተሩ ኣንዱ ነበር። [202] ኣሜሪካኖችም የሓውልቱን ቁርጥራጮች ትክክለኛ መጠን ለማወቅ ተጠይቀው ያወጡትን ወጪና የኣክሱም ኣይሮፕላን ማረፊያ ችሎታ ያጠኑበትን ገንዘብ ጣልያኖች ኣልከፈሉንም ብለዋል። [203] በእዚህ ኣኳኋን በጣልያን ወጪ ሓውልቱ በሩስያ ኣንቶኖቭ ኣይሮፕላን ከጣልያን ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ [204]የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት መኃንዲሶች እርዳታ [205] ኣክሱም ተተክሎ ነሓሴ ፳፱ ቀን ፳፻ ዓ.ም. ተመርቋል። [206] [207] ቪድዮዎችም እዚህ [208] [209] [210] ኣሉ።

ኣፄ ኃይለሥላሴ ሓውልቱን ጣልያኖች ከኣክሱም ሲወስዱትም ከመቃወማቸውም ሌላ ለብዙ ኣሥርት ዓመታት ሓውልቱ እንዲመለስ በሮም የኢትዮጵያ ኣምባሳደሮችና በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ወኪሎች ጠይቀዋል። [211] የኣክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኣክሱም እንዲመለስ በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመን መንግሥት የኢትዮጵያ ምክር ቤት ጠይቆ ነበር። ፕ/ር ፓንክኸርስት ስለ ጉዳዩ ካነሱበትና ሌሎችም በየጊዜው ሲጽፋ ሓውልቱን ለማስመለስ ከ፲፱፹፭ ዓ.ም. ጀምሮ የኣምስት ዓማታት የኣስተዋጽዖ ዝርዝር ውስጥ የሚከተሉት ኣሉብት። [212] [213] የኣዲስ ኣበባ ምክር ቤት፣ [214] የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጥያቄ ፊርማ፣ ልጅ ሚካኤል ዕምሩ፣ ፕ/ር እስቨን ሩበንሰን፣ ፕ/ር ደኒስ ማክ እስሚዝ፣ ኣቡነ ጳውሎስ ፭ተኛ፣ ዶ/ር ሳሊም ኣህመድ ሳሊም፣ ፕ/ር ፓስካል ጄ. ኢምፐራቶ፣ ፕ/ር ፍረደሪክ ጋምስት፣ ፕ/ር ኖርማ ኮምራዳ፣ ራጌሽዋር ሲንግ፣ ባማን ኣሊፍ፣ ዶ/ር ነቪል እስሚዝ፣ ሲይልቭያ ኤይሊንግ፣ ግለንዳ ጃክሰን፣ ኣቶ ገብሩ ኣሥራት፣ ፊታውራሪ ኣመዴ ለማ፣ ፊታውራሪ ኣበባየሁ ኣድማስ፣ ቀኛዝማች ቢያዝን ወንድወሰን፣ ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር፣ ሻለቃ ዻራርቱ ቱሉ፣ ዶ/ር ፈቃዱ ገዳሙ፣ ልዑልሥላሌ ተማሙ፣ ኢንጂነር ታደለ ብጡል፣ ተስፋዬ ዘለለው፣ ሚስስ ዊንዞፕ ቦዝወል፣ ኣንጀሎ ደል ቦካ፣ ዶናልድ ክረሜይ፣ ጆን እስፔንሰር፣ ዴቪድ በክስተን፣ ኣልበርቶ እስባክቺ፣ ሰይድ ሳማታር፣ ቪራጅ ጉፕታ፣ ፕ/ር ሃጋይ አርሊችሪቻርድ ግሪንፊልድ፣ ፒተር ጋረትሰን፣ ዩሪ ኮቢስቻኖቭ፣ ማርያ ራይት፣ ካትሱዮሺ ፋኩይ፣ ጃክ ጎትሌ፣ ፕ/ር ኢማኑኤል ሴሚ፣ ሮጀር ሽናይሰር፣ ፕ/ር ክሪስቶፈር ክላፋም፣ ፕ/ር ፍረድሪክ ሃሊደይ፣ ፖውል ብሪትዝኪ፣ ኣሊ ማዝሩይ፣ ቶማስ ፓከንሃም፣ ኮህን ለጉም፣ ኬረን ዳልተን፣ ሆዜ ጃፊ፣ ፕ/ር ዊሊያም ዲያኪን፣ ዶ/ር ኪርስተን ፒደርሰን፣ ካትርይን ባርድ፣ ዶ/ር ረይደልፍ ሞልቬር፣ ኣይቫን ኣድለር፣ ዊልፍረድ ተሲገር፣ ግራሃም ሃንኮክ፣ ሰር በርናርድ ብሬይን፣ ሉትዝ ቤከር፣ ሮደሪክ ግሪየርሰን፣ ሪታ ማርሌይ፣ ጀርሜን ግሪር፣ ሲሮ ታደኦ፣ ኒኮላ ደማርኮ፣ ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅ፣ ፕ/ር ሥዩም ገብረእግዚኣብሔር፣ ፕ/ር ኣቻምየለህ ደበላ፣ ዶ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ ፕ/ር ኣሸናፊ ከበደ፣ ዶ/ር ካሳሁን ቸኮል፣ ዶ/ር ኣስፋወሰን ኣስራቴ፣ ልጅ ዘውዴ ኃይለማርያም፣ ኣቶ ሳሙኤል ፈረንጅ፣ ሪቻርድ ባልፍ፣ ሃሪ ካህን፣ ዶ/ር ካሳይ በጋሻው፣ ሪታ ፓንክኸርስት፣ ክቡር ደጃዝማች ዘውዴ ገብረሥላሴ፣ ኣርቲስት ኣፈወርቅ ተክሌተክለጻዲቅ መኩሪያ፣ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን፣ ሴጉን ኦሉሶላ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ይገኙበታል።

ሰለ ሓውልቱ ጉዳይ በየጊዜው በመጻፍ ከተራዱትም ውስጥ “ኢትዮፒያን ረቪው” (ኤልያስ ክፍሌ)፣ “ኢትዮፕያን ሬጂስተር” (ግርማ በቀለ)፣ “ኢትዮፕያን ኮመንቴተር”፣ “ኣዲስ ትሪብዩን” እና “ቤዛ” ተጠቅሰዋል። ሓውልቱ እንዲመለስ እስከ ፲፱፻፺ ዓ.ም. እንቅስቃሴውን በመቀጠል ከተዘረዘሩ መካከል የሚከተሉ ኣሉበት። [215] ፕ/ር እንድርያስ እሸቴየኣክሱም ሓውልት ኣስመላሽ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ፣ ኣቶ ኃብተኣብ ባይሩ፣ ፕ/ር ሳሙኤል ኣሰፋ፣ ኣቶ ዳዊት ዮሓንስ፣ የኢትዮጵያ ፓርላማ፣ ፕ/ር ባሕሩ ዘውዴ፣ ማርኮ ቪጎኒ፣ የትግራይ ክልል ፓርላማ፣ ቶኒ ሂኬይ፣ ናፍታለም ኪሮስ፣ እስቲፈን ቤል፣ ኣልበርቶ ኢምፔሪያሊ፣ የሮም ኢትዮጵያውን፣ ጃራ ኃይለማርያም፣ ክቡር ኣቶ ወልደሚካኤል ጫሙ፣ ክቡር ኣቶ ሥዩም መስፍን፣ ፕ/ር ፍራንካቪግሊያ፣ በላይ ግደይ፣ ዶ/ር ተቀዳ ዓለሙ፣ ፕ/ር ኣበበ ከበደ፣ ክቡር ኣቶ ተሾመ ቶጋ፣ ጆርጅዮ ክሮቺ፣ የታዋቂ ኢትዮጵያውያን ፊርማ፣ ፲፬ሺህ ፊርማ የፈረሙ የኣክሱም ሕዝቦችና ብዙ ሺህ ፊርማ ያለው በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያና የጥያቄ ፊርማ (ፔቲሽን)፣ የጥቂት ኣፍሪቃ ኣገሮች ኣምባሳደሮች ደብዳቤዎችና ሌሎችንም ጠቅሷል። ስለ ፊርማውም በማሰማት የቢቢስ ሬድዮና ቴሌቪዥን፣ የካናድ ሬድዮ፣ የእንንግሊዝ፣ የጣልያንና ኣንዳንድ የዓለም ጋዜጣዎች ትኩረት በመስጠት ረድተዋል። ኣንድ ቪድዮም ተሠርቶ ነበር። እዚህ የቀረበው በስም የተጠቀሱትን ብቻ ስለሆነ ወደፊት ማሟላት ይቻላል። ከእዚህ ሁሉ ድካም በኋላ ጣልያኖች ሓውልቱን እንደሚመልሱ ቃል ገብተው በ፲፱፻፺ ዓ.ም. ይመለሳል ተብሎ የጣልያን ፕሬዚደንት ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ይቅርታ ከጠየቁም በኋላ የመመለሱ ጉዳዩ በወሬ ቀረ። [216] እንዲህም ሆኖ ሓውልቱ እንዲመለስ የደገፉ ጣልያኖች ነበሩ። የሓውልቱ መመለስ ጉዳይ ያንሰራራው ጣልያኖች ሓውልቱን ሮም ሲተክሉት ብረት ኣስገቡበት እንጂ ከመብረቅ ስላልተከላከሉለት ግንቦት ፲፯ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. መብረቅ ከመታውና ከላይ በኩል ተሰብሮ ከተጎዳ በኋላ ነበር። [217] [218]

ጣልያኖች የኣድዋን ድል ለመበቀል ከኣክሱም የወሰዱትን ሓውልት ሌላ ትውልድ ኣስመልሷል። [219] [220] [221] [222] ይህ ሲደረግም በየተባበሩት መንግሥታት ስምምነት መሠረት ቅርጿን ለማስመለስ ለዓመታት ስትታገል ኢትዮጵያን የረዳት መንግሥት ኣልነበረም። [223] [224] የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት እንኳን ሓውልቱን መብረቅ ከመታው በኋላ ለኢትዮጵያ ይመለስ ኣላለም።[225] ማንም ኣያስገድደንም ብለው የዓለም ሕዝብ ላይ ሲቀልዱ የነበሩትን ጣልያኖች ኣንድ ሰው ሊያስመልሰውና እንደሚዋረዱ ኣስጠንቅቆ ሓውልቱን ከማስመለስ በስተጀርባ ትምህርትነትም ኣሉት።

የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና

በእንግሊዝኛው እንደሚደረገው ኢትዮጵያውያን ፊደላቸውን በመጻፊያ መኪና መሣሪያ (ታፕራይተር) ለመጠቀም ታግለው ከደረሱበት ዘዴ ፊደላቱን ቆራርጦ መቀጠል የኢ/ር ኣያና ብሩ የ፲፱፻፳፭ ዓ.ም. ገደማ ፈጠራ ሥራ ላይ ውሏል። በእዚህ የተነሳ ኢንጂነሩ ለኢትዮጵያ ባለውለታ ሊቅ ናቸው። ከመቶ በታች መርገጫዎች ያሉት የእንግሊዝኛ የመጻፊያ መሣሪያ ከሁለት መቶ በላይ ለሆኑት የዓማርኛ ቀለሞች እንዲብቃቃ ፊደላቱን ቆራርጦ መቀጠል ኣስፈለገ። “ሀ”፣ “ለ”፣ “ሐ”፣ “መ” እና “ሠ” ኣሉ እንጂ “ሁ”፣ “ሉ”፣ “ሑ”፣ “ሙ” እና “ሡ” ስለሌሉ የመቀነስ ምልክትን የመሰለ “-” ከሌላ መርገጫ በመክተብ “ሀ”፣ “ለ”፣ “ሐ”፣ “መ” እና “ሠ” ጎን በማስቀመጥ ቅጥሎቹ ካዕቦቹን ስለሚመስሉ ተመልካቹ እንዲቀበላቸው ሆነ። ኣንዱን መቀጠያ ብዙ ቀለሞች ሊጋሩት ስለሚችሉ የሁሉም ቀለሞች በኣለመኖር የተነሳ መርገጫዎች መቆጠብ ተቻለ። “ሃ” እና “ማ’ እንጂ “ሂ”፣ “ሚ”፣ “ሄ” እና “ሜ” ስለሌሉ “ሃ” እና “ማ” እግሮች ጎን መስመር ወይም ቀለበት በማስቀመጥ እነዚያን በሚመስሉ ቅጥሎች እንድንጠቀም ሆነ። እነ “ቻ”ን የመሰሉ ቀለሞች ከታችና ከላይ ከሁለት መርገጫዎች “ተ” ላይ በሚቀጠሉ ነገሮች ተሠሩ። ስፍራ ስላነሰ እንደነ “ኳ” ያሉ ቀለሞች “ካ” ስር በተቀመጠ መስመር በሚሠሩ ኣዳዲስ ቀለሞች ተተኩ። የ“ላ”ን ግራ እግር ማሳጠር ስላልተቻለ “ለ” ቀኝ እግር ላይ ከመስመር በታች በወረደ መቀጠያ ረዝሞ ያልተለመደ መልክ ይዞ ቀረበ። በመቀጠል ሊሠሩ ለማይችሉ ቀለሞች የእራሳቸው ስፍራ ሲሰጣቸው ቦታ ስላልበቃ ካልገቡት መካከል የዓማርኛ ኣኃዞች ኣሉበት። ስለዚህ የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና የተመረኮዘውና ኣከታተቡ የተንፏቀቀ ፊደል መቀጠል ላይ ነው። የዓማርኛ ቀለም ግን እያንዳንዱ እራሱን የቻለ ስለሆነ የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ፊደል ዓማርኛ ኣይደለም። [226]

የዓማርኛ ፊደል የመክተቢያ ገበታና ዘዴ ስላልነበሩት ዶክተሩ ፊደሉን ወደ ኮምፕዩተር ሲያስገቡ ዘዴዎቹን ከመፍጠር ሌላ የዓማርኛ የመጻፊያ መኪና ቅጥልጥል ፊደልና ኣከታተቡ ወደ ኮምፕዩተር እንዳይገባ ጽፈዋል። ኣንዳንዶቹም ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው። ፩ኛ. የዓማርኛ ፊደላት ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆኑ ዓማርኛ ያልሆኑ ፊደላት መኖር ዋጋ የለውም። በእንግሊዝኛው የጽሕፈት መኪና በዓማርኛ ለመጠቀም የተሠራው ዘዴ ጊዜው ያለፈበት ቴክኖሎጂ ነው። እንኳን ዓማርኛውን የማይጽፍ የጽሕፈት መኪና በሚገባ እንግሊዝኛውን የሚጽፈው የእንግሊኛ የጽሕፈት መኪና ዋጋ ኣጥቶ ሙዚየም ገብቷል። ፪ኛ. የእንግሊዝኛው የመጻፊያ መኪና የተሠራው ለእያንዳንዱ የላቲን ፊደል መክተቢያና የመርገጫ ስም በመመደብ ሲሆን የዓማርኛው የመጻፊያ መኪና እነዚያን የሉትም። ዶክተሩ ለግዕዙ መክተቢያና የመርገጫ ስም በኮምፕዩተር ፈጥረውለታል። ፫ኛ. የዓማርኛ የመኪና ፊደላት የሚሠሩት ለተወሰነ መጠን ተስተካክለው ወረቅት ላይ እንዲሰፍሩ ነው። በኮምፕዩተር ግን ኣንዱን መጠን መጨመርና መቀነስ ስለሚቻል መጠኑ ሲለወጥ ቅጥሎቹ ይደበቃሉ ወይም ክፍተታቸው ይጨምራል። የገጹ ስፋት ሲጠ'ብ ቅጥሎቹ ብቻቸውን ወደ ኣዲስ መስመር ሊዞሩ ይችላሉ። ቅጥሎቹ ስለሚበጣጠሱ ማሕተምን የመሳሰሉ ነገሮች ኣያሠሩም። ስለዚህ ቅጥልጥል የመኪና ቀለሞች የትክክለኛው ፊደል ተጠጊ እንጂ እራሳቸውን ችለው ሁሉንም ሥራዎች ስለማያሠሩ ኣስፈላጊ ኣይደሉም ብለው ዶክተሩ ጽፈዋል።

፬ኛ. የላቲኑ የመጻፊያ መኪና እያንዳንዱን ቀለም የሚከትበው በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ሲሆን የዓማርኛው መኪና ከእዚያ በላይ መርጫዎችን ይጠይቃል። ስለዚህ ዓማርኛ ሳያስጽፍ ብዙ መርገጫዎችን መነካካት በሚያስፈልግ ዘዴ ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ ከቀረበ ከ፳፯ ዓመታት በኋላ ዛሬም በ፳፻፮ ዓ.ም. መቀጣጠል ጥቅም የለውም። [227] በኣብሻ ሥርዓት የተከተበውን ትክክለኛ ቀለም ለመሰረዝም ኣንድ መርገጫ በቂ ነው። ለኣስቀጣይና ተቀጣይ ግን ኣንድ መሰረዣ በቂ ኣይደለም። ፭ኛ. ወረቀት ላይ ሲሰፍሩም ሆነ የኮምፕዩተር እስክሪን ወይም መዝገብ ኣብዛኛዎቹ የዓማርኛ መኪና ፊደላት ከኣንድ በላይ ስፍራ ይጠይቃሉ። ይህ ወጪ ያስጨምራል። የግዕዝና የላቲን የኮምፕዩተር ፊደላት እያንዳንዳቸው የሚያስፈልጓቸው ኣንድ ስፍራ ብቻ ነው። ፮ኛ. የፊደል ዋና ዓይነቶች ሁለት ናቸው። ኣንደኛው የሁሉም ቀለሞች ስፋት እኩል (Fixed) ሲሆን ሌላው የተለያዩ (Proportonal) ስፋቶች ያለው ነው። በቅጥልጥል የዓማርኛ የመጻፊያ መኪና ቁርጥራጮች ስፋታቸው እኩል የሆኑ ቀለሞች መሥራት ኣይቻልም። በግዕዝና እንግሊዝኛ ቀለሞች ሁለቱንም ዓይነት መሥራት ይቻላል። ፯ኛ. ስፍራ ስላነስ የግዕዝ ኣኃዞች ቀርተው የእንግሊዝኛው ቍጥሮች ብቻ የዓማርኛው ኣኃዛት ሆነው በዓማርኛው የጽሕፈት መኪና ቀርበዋል። ይህ ለግዕዙ ኣኃዞች መዳከም ኣንዱ ምክንያት ሆሏል። ፰ኛ. ለዓማርኛ የጽሕፈት መሣሪያ እንዲስማማ ተብሎ ፊደል መቀነስና መቀንጠስ ተለምዶ ዶክተሩ ሁሉንም ቀለሞች ኮምፕዩተራይዝ ካደረጉ በኋላም መቀነስና መቀንጠስ እንደማያስፈልግ ግንዛቤ ማስጨበጥ ማስቸገሩ ቀጥሏል። ለምሳሌ ያህል “ኳ”ን በ“ኩዋ” ማንበብ የሚፈልጉ ሲኖሩ ፊደሉን ኣጥፍተው በ“ካ” እና መቀጠያው ሲጠቀሙ የከረሙ ስላላዋጣቸው የቆራረጡትን እንደመተው መልሰው በመቀጠል የኣሌለ መልከ-ጥፉ ኣዲስ ቀለም በመጨመር እያስለመዱ ናቸው።

ጥሬ ሥጋ

ዶር ኣበራ ዕድል ባገኙ ቍጥር ችሎታቸውን ለሌሎች ከማስተማርና ስለሚያውቁት ከማስረዳት ኣይቆጠቡም። ለምሳሌ ያህል በቅርቡ ከኣንድ የዋሽንግተን ዲ.ሲ. ሬድዮ ጣቢያ ጋር ስለ ጥሬ ሥጋ ገለጻ ኣድርገው ነበር። ኢትዮጵያውያን ጥሬ ሥጋ ከሚበሉ ሕዝቦች መካከል ስለሆኑ ኣትብሉ ማለት ብቻ ትክክል ስላልሆነ የሚያዋጣው በምርምር የተደገፉ መረጃዎችን ማቅረብ ነው። በኣሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚደረገው ከብት በየቦታው እየታረደ ይበላ ስለነበረ ኣሜሪካ ውስጥ እንዲቀር ተወስኖ በ፲፰፻፺፱ ዓ.ም. ፌዴራል ድንጋጌ የኣልተመረመረና ንጹህ ያልሆነ ሥጋ ለሕዝብ ማቅረብ ክልክል ነው። ሕጉን ኣለማወቅ መከላከያ ኣይደለም። ሥጋው የተመረመረ ለመሆኑ ማሕተሙን ማየት ያስፈልጋል። እንዲህም ሆኖ ኣንድ ሰው የእራሱን እንሰሳት ኣሳድጎና ኣርዶ ሳያስመረምር ቤተሰቡን የማብላት መብት ኣለው።

ጥሬ ሥጋ ጀርሞች ኣሉት። የሚከተሉትንም ማወቅ ጠቃሚ ነው። ፩. ኣንድ እንሰሳ ሲታረድና ቆዳው ሲገፈፍ ጀርሞች በተለያዩ ሁኔታዎች ሥጋው ውጭ ላይ ስለሚቀሩ ያንን ማስወገድ ኣይቻልም። ፪. እንደ ባክቴሪያ ያሉ ጀርሞች በእየ20 ደቂቃዎች ሁለት በመሆን ይራባሉ። ይኸን እርባታ ቅዝቃዜ ያዘገየዋል። ስለዚህ እንሰሳው እንደታረደ ሥጋው ጥቅም ላይ ካልዋለ ሁልጊዜ መፈረጅ (ፍሪግ ውስጥ መቀመጥ) ኣለበት። ለብዙ ጊዜ መቀመጥ ካለበት ሥጋው መፈረዝ (ፍሪዘር መግባት) ኣለበት።

ግዕዝኤዲት ለኣይፎን 6

ግዕዝኤዲት ለኣፕል ኣይፎን 6 (iPhone 6 GeezEdit app) [228] ከኣፕሮባቲክስ (Approbatics) ቀርቦላችኋል። [229] [230] [231] [232] በኣፕል ኣይፓድም (iPad) ያስከትባል። ከኣይፎን 4ኤስ (iPhone 4s) ወዲህ ለተሠሩትም ኣዲሱን የኣይኦኤስ 8 (iOS 8) ሥርዓት በማስገባት ማሻሻል (Upgrade) በዓማርኛው መጠቀም ያስችላል። GeezEdit (Amharic Typing) ከኣፕ ቁስ (App Store) ወይም ኣይቲዩንስ ወደ ኣይፎን 6 የእጅ ስልካችን ስናስገባ "Allow Full Access" የሚለው ከፊደል ገበታዎች ኃይል ጋር ያሉትን ልዩ ጥቅሞች ለመጠቀም የሚያስፈልግ ስለሆነ ለጊዜው መዝለል ይቻላል። እንዲህም ሆኖ ኣፕል አንጂ የኢትዮጵያ ኮምፕዩጥሮችና ሶፍትዌር የገዥዎችን ክሬዲት ካርድና ኣድራሻ ኣያውቅም። ይህ ለኣዲሱ የኣፕል የእጅ ስልክ የተለያዩ ቁሳቁሶች ውስጥ እንዲሠራ የቀረበው ቁስ ኣከታተብ የባለቤትነት መብቱ ለዶክተሩ ሊሰጥ እየተጠበቀ ባለው ዘዴ ለዊዶውስና ማክ ኮምፕሩዩተሮች መክተቢያ በነፃ ከተሰጠውና ከሚሸጠው ግዕዝኤዲት ጋር ኣንድ ዓይነት ነው። ለተወስነ ጊዜ ዋጋው ዶላር ፩.፱፱ (1.99) ነው። ቁሱ ተወዳጁን የግዕዝኤዲት ዩኒኮድ የዓማርኛውን ፊደል ይጨምራል። የግዕዝ ፊደል ያላቸው የኣንድሮይድ ስልኮችም ከኣይፎን የተላከላቸውን ማስነበብ ይችላሉ። የፊደል ገበታው ለጊዜው ለዓማርኛ ብቻ ቢሆንም ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች ማለትም [233][234][235] እና [236] ከኣንድ ገበታ እንዲያስከትብ የተሠራ ነው። እያሻሻልነውና የሌሎች ቋንቋዎቻችንን መክተቢያዎች እንደኣስፈላጊነታቸው ወደፊት እንከፍታቸዋለን።

ዓማርኛ ከዓለም ቋንቋዎች መደብ እንዲገባ ኣፕል ገበታችንን እንድናስገባ ስለወሰነ እናመሰግናለን። የግዕዝኤዲት ቁስ የተለያዩ የኣይፎን 6 የእጅ ስልክ ፕሮግራሞች ውስጥ እንድንሠራ ኣዲስ ችሎታ ኣስገኝቶልናል። በኣሁኑ ጊዜ ኣንዳንድ ድረገጾችና ጽሑፎች ግን ላይነበቡ የሚችሉት በሌሎች ምክንያቶች ሲሆን ችግር የሌላቸው ድረገጾች ምሳሌ እዚህ [237] ኣለ። ለምሳሌ ያህል እንደነፃው የግዕዝኤዲት ገጻችን [238] ያሉት ገጾች በኮምፕዩተር የሚነበቡት በኣዶቢ ፍላሽ ስለሆነና የኣፕል ኣይፎን ፍላሽን ስለማያስገባ ድረገጹ ባይነበብ ችግሩ የግዕዝኤዲት ኣይደለም። ወጪና ጊዜ ያስጨምራል እንጂ ለኣንዳንዳቹም ተግዳሮት መፍቻ ዘዴዎች ኣሉ። ኣንዳንድ ፕሮግራሞችም በእንግሊዝኛ እንጂ በዩኒኮድ ፊደላት የመጠቀም ኃይል ገና የላቸውም። ለተጨማሪ መረጃ የግዕዝኤዲት ፌስብክ ገጻችንን መከታተል ይጠቅማል። ኣጓዳኙም እዚህ [239] ኣለ።

በኣይፓድ ግዕዝኤዲትን የምትጠቀሙትም ለጊዜው እንግሊዝኛውን በኣንደኛ ቋንቋነት ትታችሁ አማርኛውን ሁለተኛ ኣድርጉት።

ከእዚህ በፊት መጻፊያ ኣጥታችሁ በእንግሊዝኛ ፊደል ዓማርኛውን ስትጽፉ የነበራችሁትን ግዕዝኤዲት ገላግሏል። ከእንግዲህ ወዲያ ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስት መርገጫዎች መክተብና ቴክኖሎጂን በሚ'ገባና ሳይንሳዊ ባልሆነ ዘዴ መጠቀም ኣስፈላጊ ኣይደለም።

ግዕዝ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም.
ኣንገነጠልም፣ ፲፱፻፹፯ ዓ.ም.
የኣክሱም ሓውልት፣ ፳፻፩ ዓ.ም.
ኢምዩን ደፊሸንሲ ፈውስ ፲፱፻፷፱ ዓ.ም.
ኣንዳንዶቹን ከ፲፱፻፹ ዓ.ም. ጀምሮ
መድን መመርመሪያ፣ ፲፱፻፸፰ ዓ.ም.
የሞዴት ፊደል ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. Ethiopian Review, 1991
አቡጊዳ ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. Ethiopian Review, 1991

የውጭ መያያዣዎች

  • [240] Computers & Software. Retrieved on 2007-09-15.
  • [241] ግዕዝ በኮምፕዩተር በአበራ ሞላ Amharic ፲፱፻፹፫ ዓ.ም
  • [242] ግዕዝ በኮምፕዩተር
  • [243] Ethiopic Computerization by Dr. Aberra. Ethiopian Review, 1991
  • [244] Ethiopic Computerization by Dr. Aberra
  • [245] Dr. Aberra Molla
  • [246] ኤድስ በ፲፱፻፹፫ ዓ.ም.
  • [247] GeezEdit ad in Ethiomedia
  • [248] Ethiopian Review, 1991. AIDS ኤድስ በዶ/ር ኣበራ ሞላ ፲፱፻፹፫ ዓ.ም.
  • [249] Advances Made by Ethiopians in the Computer Technology (1991) ግዕዝና ኮምፕዩተር በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም.
  • [250]
  • [251] Millennium
  • [252]
  • እናስተዋውቅዎ
  • የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር
  • [253] The Ethiopic Calendar
  • [254] The Ethiopic Calendar
  • [255] ዶ/ር ኣበራ ሞላ
  • [256] Plant Names ስመ እጸዋት
  • [257] Plant Names ስመ እጸዋት
  • [258] World Heritage Encyclopedia - Teff ጤፍ
  • [259] Scientists
  • የኢትዮጵያ እጽዋት ዓማርኛ ዊኪ
  • Rabies የውሻ እብደት፣ 1974
  • [260] ስመ በሽታ
  • [261] Disease Names in Amharic
  • [262] የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ፲፱፻፺፪ Languages, 1999
  • [263] የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በዶ/ር ኣበራ ሞላ
  • [264] Ethiopian of the Millennium Nominee by Seifu Abdi ሰይፉ ኣብዲ
  • [265] ሚሌንየም
  • [266] ግዕዝኤዲት ኦንላይን ዓማርኛ GeezEdit Online Amharic
  • ኮምፕዩተር
  • [267] ማስታወሻ፣ ሮዝ መጽሔት
  • [268] AMHARIC BECOMES OFFICIAL D.C. GOVERNMENT LANGUAGE
  • [269]
  • [270] GeezEdit
  • [271] Ethiopic.com ዶ/ር ኣበራ ሞላ
  • [272] ያሁ እና ቢንግ በዓማርኛ መፈለጊያ
  • [273] Yahoo and Bing
  • [274] The Amharic Typewriter የአማርኛ የጽሕፈት መኪና
  • ግዕዝኤዲት ዜናዊ መግለጫ
  • ግዕዝኤዲት ዜናዊ መግለጫ
  • [275] Google in Amharic ጉግል በዓማርኛ
  • [276] ግዕዝ ስምና ኣኃዝ Ethiopic Names and Numbers
  • Academic Dictionaries and Aberra Molla (From English Wikipedia)
  • [277] Bionity, Aberra Molla ኣበራ ሞላ]
  • Scientists Dr. Molla
  • ዓማርኛ በጉግል ኣፈላለግ How to Google in Amharic plus English
  • [278] Dr. A. Molla
  • [279] Scientists የኢትዮጵያ ሳይንቲስቶች
  • [280] The Aksum Obelisk
  • [281] The Axum Obelisk
  • [282]የአክሱም ሐውልት
  • [283] The Ethiopic Calendar የግዕዝ ቀለንጦስ
  • [284] The Ethiopic Alphabet የግዕዝ ፊደል
  • [285] ግዕዝኤዲት
  • [286] The Ethiopic Millennium ሚሌንየም
  • [287] Ethiopic Zero የግዕዝ ኣልቦ
  • [288] Ethiopic Numeral Names
  • [289] ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እውቀት መለዋወጫ መረብ
  • [290] GeezEdit ግዕዝኤዲት
  • [291] በነፃው ግዕዝኤዲት ዓማርኛ ኣከታተብ፣ አማርኛ
  • [292] Amharic Typing በነፃው ግዕዝኤዲት አማርኛ ኣከታተብ፣ እንግሊዝኛ
  • [293] የኣክሱም ሓውልት
  • [294] Axum Obelisk Revisited, Global Alliance for Justice: The Ethiopian Cause
  • [295] Aksum Obelisk Revisited
  • Ethiopian Scientists የኢትዮጵያ ሳይንቲስቶች
  • en:List_of_Ethiopians, s.v. Scientists
  • [296] ኢምዩንደፊሸንሲ የኣሜሪካ ፓተንት
  • [297] 4,501,816 ኢምዩንደፊሸንሲ የኣሜሪካ ፓተንት
  • [298] ModEth Ethiopian Word Processor Copyright, ሞዴት የኢትዮጵያ ቃላት ማተሚያ ኮፒ መብት
  • [299] የኢትዮጵያ ፓተንት ማመልከቻ፣ ግዕዝ በኮምፕዩተር ፲፱፻፹፪ ዓ.ም.
  • [300] የኣሜሪካ ፓተንት ፔንዲንግ፣ ግዕዝ በኮምፕዩተር
  • [301] Kingdom Patent 2127963 የእንግሊዝ ፓተንት
  • [302] Sebat Biet Guragie ሰባት ቤት ጉራጌ
  • [303] Amharic Search አማርኛ አፈላለግ
  • [304] Cell Phone Typing in Amharic የእጅ ስልክ
  • [305] የእጅ ስልክ
  • [306] Ethiopian eResources
  • [307] ኑግ
  • [http://am.wiktionary.org/wiki/sorghum0 Sorghum ማሽላ
  • [308] Ethiopian Millenium
  • [309] Ethiopic Invention የግዕዝ ኣከታተብ ኣዲስ ፈጠራ።
  • ግዕዝኤዲት GeezEdit]
  • [310] ከዶከተር አበራ ሞላ ጋር በኮሎራዶ የተደረገ ውይይት ክፍል ፩ ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. 1992 እ.ኤ.ኣ.። Dr. Aberra Molla's Interview on ECTV, 1992
  • [311] ከዶከተር አበራ ሞላ ጋር በኮሎራዶ የተደረገ ውይይት ክፍል ፩ ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. 1992 እ.ኤ.ኣ.። Dr. Aberra Molla Interview on ECTV, 1992, Part 1
  • [312] ከዶክተር አበራ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ሙሉ ክፍል ያድምጡ በቪ.ኦ.ኤ. መለስካቸው አመሀ፣ 26.09.2012
  • [313] An Open Letter to His Holiness Pope Benedict XVI, By Dr. Aberra Molla, 11/28/12 ግልጽ ደብዳቤ ለቫቲካን ጳጳስ
  • [314] Ethiopic Character Entry, pending patents
  • [315] ግዕዝኤዲት ቪዲዮ ፳፻፭ ዓ.ም.፣ Dr. Aberra Molla - interview on ETV, 9/26/2012
  • [316] ስለ ግዕዝ ቴክኖሎጂ ከዶቸ ቨለ ሬድዮ ተክሌ የኋላእሸት ጋር የዶ/ር ኣበራ ቃለ ምልልስ (መጋቢት ፳፭ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)
  • [317] Acquired Hypogammaglobulinemia ፈውስ ፈጠራ
  • [318] US Patent 8381119 B2, Aberra Molla Patent Citation ሺና
  • [319] Encyclopedia of Time, Calendar, Ethiopian
  • [320] List of Veterinarians ታዋቂ የዓለም የእንስሳት ሐኪሞች
  • [321] Heroes and Heroines, Inside Ethiopia የኢንሳይድ ኢትዮጵያ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን
  • [322] Scientists የኢትዮጵያ ሳይንቲስቶች
  • [323] Addis Abeba University
  • [324] Cell Phones የእጅ ስልክ
  • [325] GeezEdit Facebook ግዕዝኤዲት ፌስቡክ
  • [326] Engraving Portal's Font Designers List የዓለም ፊደል ሠሪዎች
  • [327]
  • [328] Abyssinia Forever
  • [329] Subi 2000
  • [330] Plant Genetic Resources of Ethiopia - archive today
  • [331]
  • [332] Wikipedia Amharic Language
  • [333] Dr. Aberra Molla interview on ETV
  • [334] Engineer Ayana Birru ኢንጅነር ኣያና ብሩ
  • [335] Ethiopia by Nebiyu Asfaw ነቢዩ ኣስፋው
  • [336] Ethiopian Numbers
  • ግዕዝ
  • [337] ዓማርኛ
  • አማርኛ
  • ትግርኛ
  • [338] ኣገው / ቢለን
  • [339] The Ethiopic Alphabet - Dagmawbelelte.com ዳግማዊ በለጠ
  • [340] ቪድዮ
  • [341] Ethiopian Alphabet ሀሁ ቪድዮ
  • [342] Useful Links
  • [343] Ancient Calendars of the Holy Bible
  • [344] Calendar Research
  • [345] Ethiopian Computers & Software
  • [346] African Fonts
  • [347] Africans Scientific Legacy
  • [348] Addis Abeba University
  • [349] History of writing
  • [350] ኢትዮጵያ Ethiopia
  • [351]
  • [352] ሞዴት
  • [353] ኢትዮወርድ
  • [354] JAH Witness
  • [355] 365 Days
  • [356] ግዕዝኤዲት ቪድዮ
  • [357] አማርኛ ኣከታተብ በዶ/ር ኣበራ ሞላ
  • [358] GeezEdit Amharic Typing by Dr. Aberra Molla
  • [359] ምስጋና Testimonials
  • [360] ምስጋና Testimonials
  • [361] African Scientific Legacy
  • [http://mapyourinfo.com/wiki/am.wikipedia.org/%E1%8A%A3%E1%89%A0%E1%88%AB%20%
  • [362]
  • [363]
  • [364] Amharic Movies
  • [365] A RASTA_LOJ Proposal
  • [366] የዶ/ር ኣበራ ሞላ ውክፔዲያ ገጽ ኣንባቢ ብዛት
  • [367] የውክፔድያ ጽሁፎች ከረጅሙ ተደርድረው
  • [368] ያሁኑ
  • [369] Encyclopedia of Time: Science, Philosophy, Theology, & Culture
  • [370]የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር
  • [371] የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር
  • [372] Aberra Molla Wikidoc
  • [373] ግዕዝኤዲት ኣከታተብ በዶ/ር ኣበራ ሞላ GeezEdit Typing by Dr. Aberra Molla
  • [374]History
  • [375] Ethiopian Millennium – An African Occasion.
  • [376] The Ethiopic Calendar - Docstoc
  • [377] Africa Speaks and Rastafari Speaks
  • [378] በበፍቃዱ...
  • [379] SeeEthiopia.com
  • [380]
  • [381] Video
  • [382] አክሱም Ethiopian Travel Advisor
  • [383] Ethio Circle ኢትዮ ሰርክል
  • [384] ጋሻው ገብረኣብ Gashaw Gebreab
  • [385] Ethiopic Numeral Names
  • [386] ስመ ኣኃዝ
  • [387] የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር
  • [388]
  • [389] Aethiopian alphabet and wheel
  • [390]
  • [391] 3,350 B.C.
  • [392] Terrefe Ras-Work
  • [393]
  • [394]
  • [395]
  • [396] Twitter Tseday ትዊተር ፀዳይ
  • [397] Veterinarians
  • [398] Ethiopian People
  • [399] Colorado State Alumni
  • [400] CSU Alumni
  • [401] 1947 Births
  • [402] Ethiopian Computers & Software - 1982-2008...
  • [403]
  • [404] Dr. Aberra Molla
  • [405]
  • [406]
  • [407] Ethio Circle Professionals
  • [408] An Ethiopian Journal
  • [409] Patent Citation
  • [410] Ethiopian Inventions
  • [411] Ethio Circle
  • [412] Mathematics
  • [413] Adera
  • [414] Amharic Typing GeezEdit
  • [415] GeezEdit Online
  • [416] E-bookspdf.org
  • [417] Google Books
  • [418] Cybrmstr
  • [419] GeezEdit Video
  • [420] An Ethiopian Journal
  • [421] GeezEdit
  • [422] Ethiopian This Week
  • [423] Ethiopian Celebrities
  • [424]
  • [425] Veterinarians
  • [426] Typeface
  • [427] Ethiopian American
  • [428] Twitter
  • [429] Video
  • [430]
  • [431]
  • [432] Interview Audio
  • [433] Interview in Amharic
  • [434] History of Mathematics in Africa AMUCHMA 25 Years
  • [435] Most Viewed Titles
  • [436] Approbatics
  • [437] Approbatics
  • [438] GeezEdit iPhone 6 App Amharic Typing by Aberra Molla
  • [439] Ethiopian American Forum, GeezEdit on the App Store on iTunes
  • [440] Unsung Heroes
  • [441] Ethiopian Scientists
  • [442] GeezEdit Facebook ግዕዝኤዲት ፌስቡክ
  • [443] geezedit.com links
  • [444] የኢትዮጵያ ሙዚቃ ፎቶዎች Ethiopian DJ Photos
  • [445] FPosts.com ምስጋና፣ ዶክተር ኣበራ (አበራ) ሞላ በኮምፕዩተር ግዕዝ ፊደልን ለመጀመሪያ ጊዜ መጠቀም እንዲቻል ስለኣደረጉ።
  • [446] የኢትዮጵያ ሙዚቃ Ethiopian Music
  • [447] Ethiopian DJ ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ !!! Thanks to Dr. Aberra Molla for computerizing Ethiopic
  • [448]
  • [449] Ethiopic Character Entry US 20090179778 A1 by Dr. Aberra Molla, cited by six patents (2010-20014)
  • [https://itunes.apple.com/us/app/geezedit/id935624754?mt=8 iPhone 6 GeezEdit App link
  • መጋቢት ፳፬
  • ደብረ ብርሃን
  • ስለ ነፃው ግዕዝኤዲት GeezEdit Video ቪድዮ በዶ/ር ኣበራ ሞላ፣ የኮምፕዩተር ጥገና ባለሙያ እልፍነሽ ኃይለመስቀል እና የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ዮርዳኖስ ኣዳነ፣ ኣሸናፊ ዘለቀ እና ኤፍሬም ፀጋየ ጋር
  • [450] Dr. Aberra Molla. PERSON OF THE YEAR 2013, Ethiopian American Forum
  • [451] Aberra Molla ግዕዝኤዲት አማርኛ ለአይፎንና አይፓድ GeezEdit Amharic Typing in Apple.com iTunes
  • [452] ግዕዝኤዲት ለኣይፎን 4s, 5 and 6 GeezEdit Amharic Typing in iOS 8 system, and for iPad
  • [453] ግዕዝኤዲት ለኣይፎን 6 GeezEdit Amharic Typing in iOS 8 system, for iPhone 6 and iPad