Jump to content

መቀሌ

ከውክፔዲያ
(ከመቀለ የተዛወረ)
መቐለ
ከተማ
ሓኽፈን ጎዳና (መቐለ)
አገር  ኢትዮጵያ
ክልል ትግራይ ክልል
ዞን መቐለ ልዩ ዞን
ከፍታ 2,084 ሜ.
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 169,207
መቐለ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
መቐለ

13°29′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°28′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

መቐለ (አማርኛ፦ መቀሌ) የትግራይ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከአዲስ አበባ 783 ኪ.ሜ. ወደ ሰሜን ትገኛለች። ከ300,000 አስከ 350,000 የሚገመት የሕዝብ ብዛት ስላላት ከሰሜን ኢትዮጵያ ትልቋ ከተማ ያደርጋታል። መቐለ ለ አጼ ዮሐንስ ፬ኛ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ በመሆን በ19ኛው ክፈለ ዘመን ነው የተመሠረተችው። መቐለ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ከተሞች በንግድና ትምህርታዊ ማዕከላዊነትዋ ትታወቃለች። በታላቁ አፍሪካዊ ጄነራል ራስ አሉላ አባ ነጋ የተሰየመ ዓለም አቀፋዊ አየረ ማረፊያ አላት። በተጨማሪም እንደነ መስፍን ኢንዱስትርያል፣ መሰቦ ሲሚንቶ፤ ሌሎች ፋብሪካዎችና መቐለ ዩኒቨርሲቲ የመሳሰሉ ትላልቅ ተቋማት በከተማዋ ይገኛሉ።