Jump to content

የአሦር ነገሥታት ዝርዝር

ከውክፔዲያ
የ22:47, 15 ኦገስት 2018 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

የአሦር ነገሥታት ዝርዝር ከብዙ ቅርሶች ተገኝቷል። ከነዚህ ዋንኛው እራሱ «የአሦር ነገሥታት ዝርዝር» የተባለው ጽሑፍ ነው። ይህ ጽሑፍ ከ3 ቅጂዎች ሲታወቅ፣ ከ2 ሳርጎን አስቀድሞ (ወይም እስከ 730 ዓክልበ. ድረስ) የነገሡትን ነገሥታት ይዘረዝራል። ከ1 ኤሪሹም ጀምሮ ሰነዱ ለያንዳንዱ ንጉሥ የዘመኑን አመታት ቁጥር ይሰጣል። ስለዚህ ዝርዝሩ የተቀናበረው በ2 ሳርጎን ዘመን እንደ ሆነ ይታመናል።

በአሦራዊው መቆጠሪያ፣ እያንዳንዱ አመት በሊሙ (ሹም) ስም ይባል ነበር። ለአንዳንድ ንጉስ ዘመን፣ እነዚህን የአመት ስሞች የሚዘርዝሩ ተጨማሪ ዜና መዋዕሎች ተገኝተዋል። በተለይም በቅርብ ጊዜ (በ1995 ዓ.ም.) በካነሽ ፍርስራሽ (በዛሬው ቱርክ አገር) ከ1 ኤሪሹም እስከ አሹር-ዱጉል ድረስ የነበሩት የአመት ስሞች ተገኝተዋል። የአመት ስም ዝርዝሮች በብዛት ከዋናው የነገሥታት ዝርዝር ጋር ይስማማል። ከሺህ አመት በላይ አሦራውያን የአመቶችን ቁጥር በደንብ ስለ ለዩ፣ እነዚህ ቅርሶች የጥንታዊ ዘመን ታሪክና ዕድሜ መጠን ለማወቅ እጅግ ይረዳናል።

ከ1 ኤሪሹም አስቀድሞ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

[በኤብላ ጽላቶች የ«አባርሳል ውል» ትርጉም የአሦር ንጉሥ ቱዲያ ከሆነ፣ ከቱዲያ በፊት የማሪ ንጉሥ ኢብሉል-ኢል አሦርን ገዛ።]

  • «በድንኳን የኖሩ 17 ነገስታት»፦ ቱዲያ፣ አዳሙ፣ ያንቂ፣ ሳሕላሙ፣ ሐርሐሩ፣ ማንዳሩ፣ ኢምሱ፣ ሃርሱ፣ ዲዳኑ፣ ሃኑ፣ ዙአቡ፣ ኑአቡ፣ አባዙ፣ ቤሉ፣ አዛራህ፣ ኡሽፒያ፣ አፒያሻል።

[ከቱዲያ በኋላና ከኡሽፒያ በፊት ያሉት ስሞች በሌላ ምንጭ ባይታወቁም በአካድ ንጉሥ ማኒሽቱሹ ዘመን የአሦር ሻካናካ (ገዥ ወይም ከንቲባ) አዙዙ ከቅርስ ታውቋል፤ እንዲሁም የአሦር ሻካናካ ኢቲቲ በጋሱር (ኑዚ) ላይ ድል አንዳደረገ ይታወቃል።[1]

  • «አባቶቻቸው የታወቁት 10 ነገሥታት»፦ አፒያሻል የኡሽፒያ ልጅ ነበር፣ ሐሌ የአፒያሻል ልጅ፣ ሳማኒ የሐሌ ልጅ፣ ሐያኒ የሳማኒ ልጅ፣ ኢሉ-መር የሐያኒ ልጅ፣ ያክሜሲ የኢሉ-መር ልጅ፣ ያክሜኒ የያክሜሲ ልጅ፣ ያዝኩር-ኢሉ የያክሜኒ ልጅ፣ ኢላ-ካብካቡ የያዝኩር-ኢሉ ልጅ፣ አሚኑ የኢላካብካቡ ልጅ።
  • «የአመት ስም ቁጥር የማይታወቅላቸው፣ ስሞቻችውም በጡብ የሚገኙ 6 ነገሥታት»፦ ሱሊሊ የአሚኑ ልጅ፣ ኪኪያ፣ አኪያ፣ 1 ፑዙር-አሹርሻሊም-አሁምኢሉሹማ

[የኡር ንጉሥ አማር-ሲን ሻካናካ (አገረ ገዥ) ዛሪቁም ከ፩ ፑዙር-አሹር አስቀድሞ በአሦር እንደ ገዛ ይታሥባል።]

የአሦር ነገሥታት ከ1 ኤሪሹም እስከ አሦር ውድቀት (እስከ 617 ዓክልበ.) ድረስ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  1. ^ እነዚህ «በድንኳን የኖሩት» እስከ ኑአቡ ድረስ ምናልባት የባቢሎን ነገሥታት ወላጆች ደግሞ ነበሩ፤ «ሐሙራቢ ትውልድ» የሚባል ሰነድ የሚከተሉት ተመሳሳይ ስሞች አሉበት፣ ነገር ግን ከአሦራዊ ዝርዝር ተዛብተዋል፦ አራምማዳራ (ሐርሐሩ፣ ማንዳሩ)፤ ቱብቲያሙታ (ቱዲያ፣ አዳሙ)፤ ያምቁአዙሐላማ (ያንቂ፣ ሳሕላሙ)፤ ሄያና (ሃኑ)፤ ናምዙ (ኢምሱ/ሃርሱ)፤ ዲታኑ (ዲዳኑ)፤ ዙማቡ (ዙአቡ)፤ ናምሑ (ኑአቡ)፤ አምናኑ፤ ያሕሩሩም፤ ኢፕቲያሙታ፤ ቡሐዙም፤ ሱማሊካ፤ አሽማዱ፤ አቢያሙታ፤ አቢዲታን፤ ማም-...፤ ሹ-...ኒ-...፤ ዳድ-...፤ ሱሙአቡም (መጀመርያው የባቢሎን ንጉሥ)። J. Finkelstein, 1966, "Genealogy of the Hammurabi Dynasty", Journal of Cuneiform Studies, 20 (3): 95–118