አባል:Daniel (usurped)~amwiki
Appearance
ተረቶቹ በቅደም ተከተል ሲቀመጡ
- ሀሜተኛ ነው ከዳተኛ
- ሀሜተኛ ያፍራል ሀስተኛ ይረታል
- ሀሜተኛ ያፍራል እውነተኛ ይረታል
- ሀሜት አይቀር ከድሀም ቤት
- ሀሜትና ጅራት በስተኋላ ነው
- ሀምሌ ቢያባራ በጋ ይመስላል
- ሀምሌና ሙሽራ ሳይገለጡ ነው
- ሀምሌን በብጣሪ ነሀሴን በእንጥርጣሪ
- ሀምሳ ሎሚ ለሀምሳ ሰው ጌጡ ለአንድ ሰው ሸክሙ
- ሀረጉን ሲስቡት ዛፉ ይወዛወዛል
- ሀረጉን ሳብ ዛፉ እንዲሳሳብ
- ሀረግ ለመዳፍ አልጋ ለምንጣፍ
- ሀሰተኛ ምስክር ጉልበት ይሰብር
- ሀሰተኛን ሲረቱ በወንድም በእህቱ
- ሀሰተኛ ሲናገር ይታወቃል ስሱ ሲበላ ይታነቃል
- ሀሰተኛ ሲናገር ይታወቃል በሶ ሲበሉት ያንቃል
- ሀሰተኛ በቃሉ ስደተኛ በቅሉ ሀሰተኛ በቃሉ ስደተኛ በቅሉ ይታወቃሉ
- ሀሰተኛ ብርቱ ወንጀለኛ
- ሀሰተኛ ያወራውን ፈረሰኛ አይመልሰውም
- ሀሰት ስለበዛ እውነት ሆነ ዋዛ
- ሀሰት ቢናገሩ ውቃቢ ይርቃል
- ሀሰትና ስንቅ እያደረ ያልቅ
- ሀሰት አያቀላ እውነት አያደላ
- ሀሰት አያድንም መራቆት መልክ አያሳምርም
- ሀስት እያደር ይቀላል እውነት እያደር ይበራል ሀስት እያደር ይቀላል እውነትና ውሀ እያደር ይጠራል
- ሀሰት ነገር ክፉ ገሀነም እሳት ትርፉ
- ሀሳቡ ጥልቅ ነገሩ ጥብቅ
- ሀሳብህን ጨርቅ ያድርገው
- ሀሳብና መንገድ ማለቂያ የለውም
- ሀሳብ ከውለታ አይቆጠርም
- ሀሳብ ከፊት አይፈታ ሙት አይመታ
- ሀሳብ ያገናኛል ፍራት ያሸኛኛል
- ሀሳብ ያገናኛል ፍርሀት ያሸኛኛል
- ሀ ሳይሉ ጥፈት ውል ሳይዙ ሙግት
- ሀ ባሉ ተዝካር በሉ
- ሀ ባሉ ደሞዝ በሉ
- ሀብታም ለሀብታም ይጠቃቀሱ ድሀ ለድሀ ይለቃቀሱ ሀብታም ለሰጠ የድሀ ሙርጥ አበጠ
- ሀብታም ለሰጠ የድሀ ሙርጥ ያብጣል
- ሀብታም ለሰጠ ደሀ ምንጭሩ አበጠ
- ሀብታም ለሰጠው ደሀ ይንቀጠቀጣል
- ሀብታም ሊሰጥ የደሀ ቂጥ ያብጥ ሀብታም ሊሰጥ የደሀው ሙርጥ ያብጣል
- ሀብታም ሊሰጥ ደሀ ምርጥ ያወጣል
- ሀብታም ሲወድቅ ከሰገነት ድሀ ሲወድቅ ከመሬት
- ሀብታም በመመጽወቱ ድሀ በጸሎቱ
- ሀብታም በከብቱ ድሀ በጉልበቱ
- ሀብታም በወርቁ ድሀ በጨርቁ
- ሀብታም በገንዘቡ ድሀ በጥበቡ እርስ በርስ ይቃረቡ ሀብታም በገንዘቡ ይኮራል ድሀ በጥበቡ ይከበራል
- ሀብታም በገንዘቡ ይኮራል ድሀ በጥበቡ ይከብራል ሀብታም ቢሰጥ አበደረ እንጂ አልሰጠም
- ሀብታም ቢያብር ድህነትን ያጠፋል
- ብታም ነው መባል ያኮራል ድሀ ነው መባል ያሳፍራል ሀብታም እንደሚበላለት ድሀ እንደሚከናወንለት
- ሀብታም ያለ ድሀ አይኮራም ድሀ ያለ ሀብታም አይበላም ሀብታም ገንዘቡን ያስባል ድሀ ቀኑን ይቆጥራል
- ሀብት እና እውቀት አይገኝ (ም ) አንድነት
- ሀብት የጠዋት ጤዛ ነው
- ሀኪም ሲበዛ በሽተኛው ይሞታል
- ሀኪም የያዘው ነፍስ ባያድር ይውላል
- ሀኪሞች እስኪመካከሩ በሽተኛው ይሞታል
- ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ
- ሀዘንና ደስታ ጎን ለጎን ናቸው
- ሀዘንን የፈራ በደስታ የተጣራ
- ሀይለኛ ውሀ አሻቅቦ ይፈሳል
- ሀይለኛ ዱቄት ከነፋስ ይጣላል
- ሀይማኖቱ ከጅማት ጉልበቱ ከብረት የጠና
- ሀይማኖት ከግብር ጸሎት ከፍቅር
- ሀይማኖት ያለ ፍቅር ጸሎት ያለ ግብር
- ሀይማኖት የሌለው ሰው ልጓም የሌለው ፈረስ ነው ሀጢአት ለሰሪው ምህረት ለአክባሪው
- ሀጢአት ሲደጋገም ጽድቅ ይመስላል
- ሀጢአት ሳያበዙ በጊዜ ይጓዙ
- ሀጢአት በንስሀ በደል በካሳ
- ሀጢአት በንስሀ እድፍ በውሀ
- ሀፍረት ያከሳል ያመነምናል
- ሁለተኛ ደሞ ለዘበኛ ! አሉ ሁለተኛ ግፌ ጫንቃዬን ተገርፌ ልብሴን መገፈፌ
- ሁለተኛ ግፍ ልብሴን ይገፍ ጀርባዬን ይገርፍ
- ሁለተኛ ጥፋት ቆሞ ማንቀላፋት ሁለተኛ ጥፋት ከገበያ ማንቀላፋት
- ሁለተኛ ጥፋት ከገበያ ቆሞ ማንቀላፋት
- ሁለቱን የተመኘ አንዱንም አላገኝ
- ሁለቱን የተመኘ አንድም አላገኘ
- ሁለቱን ወንበዴ በአንድ ዘዴ
- ሁለቴ ሰላምታ አንዱ ለነገር ነው
- ሁለት ሆነው የተናገሩት በመሬት የቀበሩት
- ሁለት ሞት መጣ ቢለው አንዱን ግባ በለው አለ
- ሁለት ሞግዚት ያለው ህጻን ያለጥርጥር በእሳት ይቃጠላል ሁለት ቁና ሰጥቼ አንድ ጥንቅል
- ሁለት ባላ ትከል አንዱ ሲስበር ባንዱ ተንጠልጠል
- ሁለት ባላ ትከል አንዱ ሲነቀል ካንዱ ተንጠልጠል ሁለት ብልጥ ኑግ አያደቅ
- ሁለት አይወዱም ከመነኮሱ አይወልዱም
- ሁለት አይወዱ ከመነኩሴ አይወልዱ
- ሁለት አይወዱ ከመነኮሱ አይወልዱ
- ሁለት አገር አራሽ ለባልንጀራው አውራሽ
- ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ አይወጡም
- ሁለት እግር አለኝ ብሎ እሁለት ዛፍ አይወጣም
- ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም
- ሁለት አፎች ባይናከሱ ይናቀሱ
- ሁለት ወፎች ባይናከሱ ይናቀሱ
- ሁለት የተመኘ አንድም አላገኘ
- ሁለት የወደደ አንዱን ሳያገኝ ሄደ
- ሁለት ጉድጓድ ያላት አይጥ አትሞትም
- ሁለት ጊዜ ተናገርህ ከፋህ
- ሁለት ጊዜ በላህ ተፋህ
- ሁለት ጊዜ ተናግረህ ከፋህ
- ሁለት ጊዜ በላህ ተፋህ
- ሁለት ጊዜ ነው የዶሮ ልደት አንዱ በእንቁላል አንዱ በጫጩት
- ሁለት ጊዜ ይፈርዱ ጉድ ይወልዱ
- ሁለት ጥፉ ካገር ይጥፉ
- ሁሉ ሄዶ ተበተነ እህና እኔ ቀረነ አለ እያዘነ
- ሁሉ ሄደ ተበተነ እህና እኔ ቀረነ አለ ያዘነ
- ሁሉ ሆነ ቃልቻ ማን ይሸከም ስልቻ
- ሁሉም ሰው መምሰሉ ባይታይ አመሉ
- ሁሉም ሸክሙን ፍቅርም ያዥውን
- ሁሉም በየዘመድህ ቢሉት አክንባሎ ጋጥ ገባ
- ሁሉም አካል ነው ግን እንደአይን አይሆንም
- ሁሉም ከኋላው ያገኘዋል እንደስራው
- ሁሉም ከልኩ አያልፍም
- ሁሉም ወንፈሉን ፈታይም ድውሩን
- ሁሉም ያልፋል እውነት ብቻ ይተርፋል
- ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ
- ሁሉ ቢናገር ማን ይሰማል
- ሁሉ አማረኝን ገበያ አታውጣት
- ሁሉ አረሰ ማን ይሸምት
- ሁሉ የሚገኝ ከእሱ የሚገኝ የለም ያለእርሱ
- ሁሉን ለእኔ አትበል
- ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል
- ሁሉን አውቆ አሳውን እሾህ ከስጋው ለይቶ
- ሁሉ ያልፋል እስኪያልፍ ያለፋል
- ሁሉም ያልፋል ግን እስኪያልፍ ያለፋል
- ሁሉ ያልፋል እውነት ብቻ ይተርፋል
- ሁሉም በየዘርህ ቢሉት አከንባሎ ጋጣ ገባ
- ሁሉም ያልፋል የሚኮርጅም ቢሆን
- ሁሉ አማረሽን ዲስኮ (disco) አታውጧት
- ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት
- ሁል ጊዜ ባሬራ ትበያለሽ ወይ አንዳንድ ጊዜ እንኳ ወጥ አትይሞይ
- ሁል ጊዜ ከመደንገጥ አንድ ጊዜ መሸጥ
- ሂዳ ጉበት ቢነሷት ታናሽ ታላቅ ስደዱልኝ አለች
- ሂዳ ጉበት የነሷት ታናሽ ታላቅ ስደዱልኝ አለች
- ሂዳ ጉበት ይነሷታል ታናሽ ታላቅ ላኩልኝ አለች
- ሂድ አትበለው እንዲሄድ አድርገው
- ሂድ አትበለው እንደሚሄድ አርገው
- ሂድ ካገር ኑር ካገር
- ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም
- ህልም አለ ተብሎ ሳይተኛ አይታደርም
- ህመሙ ቀርቶ ሞቱን በሰጠኝ
- ህመሙ ቀርቶ ሞቱን በተወኝ
- ህመሙን የሸሸገ መድሀኒት የለውም
- ህመሙን የደበቀ መድሀኒቱም አልታወቀ
- ህመሙን የደበቀ መድሀኒት የለውም
- ህዳር መማረሪያ ሰኔ መቃጠሪያ
- ህያዋን ለነገስታት ሙታን ለካህናት ይገብራሉ
- ህግ ይኖራል ተተክሎ ስርአት ይኖራል ተዛውሮ
- ሆሆሆ ስቄ ልሙት አለ ሰውየው
- ሆቴል ቢያብር ገንዘብ ያስገኛል
- ሆደ ሰፊ ነገር አሳላፊ
- ሆደ ሰፊ ይሻላል ከአኩራፊ
- ሆዱ ሲሞላ ፍቅሩ ሌላ
- ሆዱ ሲጎድል ሰው ያጋድል
- ሆዱ ናረት ሙያው ከጅረት
- ሆዱን የወደደ ማእረጉን የጠላ
- ሆዱን የወደደ ማእረጉን ይጠላል
- ሆዱን ያለ ሆዱን ተወጋ
- ሆዱ ወድዶ አፉ ክዶ ክፉ ለምዶ
- ሆዱ ፈሪ እግሩ ዳተኛ አዳም ሲዋጋ እርሱ ይተኛ
- ሆዳም ሰው እንብርት የለውም
- ሆዳም ቢሸከም የበላ ይመስለዋል
- ሆዳም ቢፈተፍት የጠገበ ይመስለዋል
- ሆዳም ፍቅር አያውቅም
- ሆዴ በጀርባዬ ቢሆን ገፍቶ ገደል በጣለኝ
- ሆዴ ኑር በዘዴ
- ሆዴን በልቶኝ ጎኔን ቢያኩኝ አይገባኝ
- ሆዴ አታጣላኝ ከዘመዴ
- ሆድህና ልጅህ አይጥሉህ
- ሆድህን ጎመን ሙላው ጀርባህን ለጠላት አታሳየው
- ሆዴ ሆዴ የሚለውን ጌታ ያየዋል አይኔ አይኔ የሚለውን ሰው ያየዋል
- ሆድ ሆዴን የምትል ወፍ አለች ምናለች
- ሆድ ለማታ በልቶ ለጠዋት
- ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው
- ሆድ ለባሰው ቢላዋ አታውሰው
- ሆድ ለተተባሰው ማጭድ አታውሰው
- ሆድ ሲሞላ ራስ ባዶ ይቀራል
- ሆድ ሲያር ጥርስ ይስቃል
- ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ
- ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ጠዋት
- ሆድ ባዶን ይጠላል
- ሆድ ባዶ ይጠላል
- ሆድ ከሁዳድ ይስፋል
- ሆድ ካገር ይስፋል
- ሆድ እንዳሳዩት ነው
- ሆድና ግንባር አይሸሸጉም
- ሆድና ግንባር አይሸሸግም
- ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት ዳገት ላይ ይለግማል ሆድን በጎመን ቢደልሉት ይለግማል ጉልበት
- ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል
- ሆድ ወዶ አፍ ክዶ ክፉ ለምዶ
- ሆድ ዘመድ ሳይወድ አፍ እህል ሳይለምድ
- ሆድ የኔ ነው ሲሉት ቁርጠት ሆኖ ይገድላል
- ሆድ የሸሸገውን ብቅል ያወጣዋል
- ሆድ ያበላውን ያመሰገናል
- ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል
ተረትና መሳሌ ላይ ይቀጠላል።