Jump to content

2019-20 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ

ከውክፔዲያ

የ2019-20 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከባድ እና አጣዳፊ የመተንፈሻ አካላት በሽታ አምጪ በሆነው SARS-CoV-2 ቫይረስ ምክንያት የተከሰተ የኮሮናቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ነው። ወረርሽኙ ለመጀመርያ ጊዜ የተገኘው በቻይና ዉሃን ሁቤ ውስጥ በእ.ኤ.አ. ዲሴምበር 2019 ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት በእ.ኤ.አ. ማርች 11 ቀን 2020 በሽታውን የወረርሽኝ ደረጃ ላይ መድረሱን አወጀ። እስከ መጋቢት እ.ኤ.አ. ማርች 29 ቀን 2020 ድረስ ባለው መረጃ መሠረት ከ670 ሺህ በላይ የኮቪድ-19 ኬዞች በ199 አገራት ውስጥ ተመዝግበዋል። በበሽታው 31,191 ሰዎች ሲሞቱ ወደ 143,840 ገደማ የሚሆኑት ደግሞ አገግመዋል። በወረርሽኙ በዋነኝነት ከተጠቁት አገራት መካከል ቻይናኢጣልያኢራንደቡብ ኮርያ እና ስፔን ይገኙበታል።

ልክ እንደ ኢንፍሉዌንዛ የቫይረሱ ዋነኛ መተላለፊያ መንገድ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሲያስሉ ወይም ሲያስነጥሱ ከሚረጩ ፈሳሾች ነው። በሽታው ተላላፊ ነው ተብሎ የሚወሰደው ሰዎች የበሽታውን ምልክቶች በሚያሳዩበት ወቅት ቢሆንም አንድ አንድ ጊዜ ምልክቱን የማያሳዩ ሰዎች በሽታውን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። አንድ ሰው ለቫይረሱ ከተጋለጠ በኋላ በአማካይ በአምስት ቀን ውስጥ ምልክቶችን ማሳየት ይጀምራል። ነገር ግን ምልክቱ እስኪታይ እስከ ዐሥራ አራት ቀን የሚቆይበት ሁኔታ አለ። የተለመዱት ምልክቶቹ ትኩሳት ፣ ሳል እና የትንፋሽ መቆራረጥ ናቸው። በሽታው ሲባባስ የሣንባ ምች እና የተለያዩ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ሊያስከትል ይችላል። በአሁኑ ጊዜ በሽታው ክትባት ወይም የጸረ-ቫይረስ ህክምና የለውም። በሽታውን ለመከላከል እጅን መታጠብ ፣ ሲያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍን መሸፈን ፣ በሽታው ካለባቸው ሰዎች ራቅ ማለት እናም በሽታው ካለባቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት ከነበረ ራስን ለ14 ቀናት ማግለል ይመከራል።

የበሽታውን መስፋፋት ለመቀነስ የጉዞ ዕገዳዎችን መጣል ፣ ለይቶ ማቆያዎችን ማዘጋጀት ፣ ሠዓት እላፊን መጣል ፣ የተለያዩ ሕዝባዊ ዝግጅቶችን መሠረዝ ወይም ማስተላለፍ እና ብዙ ሰዎች የሚገኙባቸውን ተቋሞችን መዝጋት በዓለም ላይ ከተወሰዱት እርምጃዎች ውስጥ ይጠቀሳሉ።

ይህ ወረርሽኝ ዓለምአቀፋዊ የማኅበራዊ እና የኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን አስከትሏል። የተለያዩ የባሕላዊ እና የስፖርታዊ ዝግጅቶችም ተሠረዘዋል። በመድሃኒት ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ምግብ ረገድ የአቅርቦት እጥረት ይፈጠራል የሚል ፍርሃትንም በሰዎች ውስጥ አሳድሯል። በዚህም ምክንያት በምዕራቡ ዓለም ሰዎች ዕቃዎችን በማግበስበስ እንደ መጸዳጃ ቤት ወረቀት ያሉ መሠረታዊ ዕቃዎች ላይ ከፍተኛ ዕጥረት እንዲፈጠር አድርገዋል።

ሥዕላዊ መግለጫዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የበሽታው ምልክቶች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ምልክት[3] %
ትኩሳት 87.9%
ደረቅ ሳል 67.7%
ድካም 38.1%
አክታ 33.4%
ትንፋሽ ማጠር 18.6%
የጡንቻ ወይም የመገጣጠምያ ህመም 14.8%
የጉሮሮ ህመም 13.9%
ራስ ምታት 13.6%
ብርድ ብርድ ማለት 11.4%
ማቅለሽለሽ ወይም ማስመለስ 5.0%
የአፍንጫ መደፈን 4.8%
ተቅማጥ 3.7%
ደም ማሳል 0.9%
የዓይን መቅላት እና ማበጥ 0.8%
የኮቪድ-19 ምልክቶች
የጀርሞችን ስርጭት ያስቁሙ

በኮቪድ-19 የተጠቁ ሰዎች አንዳንዴ ምንም ምልክት ላያሳዩ ሲችሉ የተቀሩት ደግሞ እንደ ኢንፍሉዊንዛ ዓይነት ምልክቶች የሆኑትን እንደ ድካም ፣ ሳል ፣ ትኩሳት ፣ የትንፋሽ ማጠር እና የጡንቻ ህመሞች ይታዩባቸዋል። የተለመዱት የበሽታ ምልክቶች በቀጣዩ ሰንጠረዥ ውስጥ ተካትተዋል።

በሽታው ሲከፋ ከባድ የሣንባ ምች ፣ የተለያዩ አጣዳፊ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ፣ ከባድ ኢንፌክሽኖችን እንዲሁም ሞትን ሊያስከትል ይችላል። አንዳንድ በበሽታው የተጠቁ ሰዎች ምንም ምልክት ሳያሳዩ ግን በላቦራቶሪ ምርመራ በሽታው ሊገኝባቸው ይችላል። በዚህም ምክንያት ከነዚህ ሰዎች ጋር ቅርብ ንክኪ የነበራቸው ሰዎች የቅርብ ክትትል እንዲደረግላቸው ተመራማሪዎች ይመክራሉ።

የበሽታው ምልክት የመታየት ጊዜ አብዛኛውን ጊዜ አምስት ቀን ቢሆንም ከአንድ ቀን እስከ ዐሥራ አራት ቀን ሊሆንም ይችላል። በአንድ ኬዝ እስከ 27 ቀን የቆየበት ሁኔታም ታይቷል።[4]

መተላለፊያ መንገዶች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ሰው ሲያስነጥስ የሚረጩ ፈሳሾች

የቫይረሱ ቀዳሚ የመተላለፊያ መንገድ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ሲያስሉ ወይም ሲያስነጥሱ ከሚረጩ ፈሳሾች ነው። ፈሳሾቹ ዓየር ላይ ለትንሽ ጊዜ ቢሆንም የሚቆዩት እንደ ብረት ፣ ካርቶን ፣ መስታወት እና ፕላስቲክ ዕቃዎች ላይ ረዘም ላለ ጊዜ ሊቆዩ ይችላሉ። ቫይረሱ ልክ እንደሌሎች ኮሮናቫይረሶች ዓየር ላይ እና አንዳንድ ቁሳቁሶች ላይ እስከ ዘጠኝ ቀን ሊቆይ የሚችልበት ሁኔታዎች አሉ።[5]

ቫይረሱ የሚገኝባቸው አገራት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
የ2019-20 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የአገራት መረጃ የ2019-20 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተከሰተባቸው የአገራት መረጃ (እስከ እ.ኤ.አ. 23 April 2020)[6]
አገር የዛሬ ኬዞች ሕክምና ላይ ያሉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ያሉ ዛሬ የሞቱ አጠቃላይ ኬዞች አጠቃላይ የሞቱ አጠቃላይ ያገገሙ
 አሜሪካ37571735814016258490924768484050
 እስፓንያ463510161777054402130242215789250
 ኢጣልያ0107699238401873272508554543
 ፈረንሣይ097880521801598772134040657
 ጀርመን374423882908191510225334103300
 ዩናይትድ ኪንግደም01150511559013349518100
 ቻይና1095963082798463277207
 ቱርክ0798211814098674237616477
 ፋርስ10301670231059087026548164843
 ሩሲያ477457327230042627735554891
 ብራዚል5911809683182846348293425318
 ቤልጅግ908265079932284279764909800
 ካናዳ024230557040190197413986
 ኔዘርላንድስ887313021050123357294177None
 ስዊዘርላንድ2287087386028496150919900
 ፖርቱጋል3712033220435223538201201
 ህንድ4271673505217976864376
 ፔሩ0116933960192505307027
 ስዊድን7511418451584167552021550
 አየርላንድ066691470166717699233
 ኦስትሪያ772786169121500252211694
 እስራኤል9490671362145921915334
 ሳዑዲ አረቢያ115811884827139301211925
 ጃፓን0102272410119502991424
 ቺሌ057503990112961605386
 ሲንጋፖር1037102702701117812896
 ኤኳዶር090511410108505371262
 ፓኪስታን73582466016108112282337
 ደቡብ ኮሪያ82051552107022408411
 ሜክሲኮ10436947378113105449702627
 ፖላንድ17781711609103464351740
 ሮማንያ38670912363100965272478
 የተባበሩት የዓረብ ግዛቶች5187063148756561637
 ዴንማርክ1612295741080733945384
 ኢንዶኔዥያ35761680127775647960
 ቃጣር6237004720776410750
 ኖርዌይ07117542733818932
 ቤላሩስ06454920728158769
 ዩክሬን578647945137170187504
 ቼክ ሪፐብሊክ4492476271362102002
 ሰርቢያ05955101071141341025
 ፊሊፒንስ27157971166981462722
 አውስትራሊያ1215414516661755045
 ማሌዢያ7119664225603953542
 ዶሚኒካን ሪፐብሊክ0445913505300260581
 ፓናማ17145939734992144255
 ኮሎምቢያ032809804356206870
 ፊንላንድ1552112602342841722000
 ባንግላዴሽ4143951174186127108
 ግብፅ02448003659276935
 ሉክሰምበርግ02863320365480711
 ደቡብ አፍሪካ025153603635651055
 ሞሮኮ912956123537151430
 አርጀንቲና0225712303288159872
 አልጄሪያ0130440029104021204
 ታይላንድ133596112839502430
 ሞልዶቫ020412121277876661
 ግሪክ (አገር)017105502408121577
 ኩዌት1511887551239914498
 ሃንጋሪ116165561142284239390
 ካዛክስታን1161682291225120549
 ባሕሬን71100821209881082
 ክሮኤሽያ311048192198150883
 አይስላንድ0313501785101462
 ኦማን10214013017168307
 ኡዝቤኪስታን012148017167495
 ኢራቅ0402001631831146
 ኤስቶኒያ33135571159245192
 አዘርባጃን30580140154820948
 አርሜኒያ50840100152324659
 ኒው ዚላንድ3370221451161065
 ቦስኒያና ሄርጸጎቪና4587441141354485
 ሊትዌኒያ28961170139838399
 ስሎቬኒያ131076230136679211
 ስሎቫኪያ81102291132515288
 መቄዶንያ41943140130056301
 አፍጋኒስታን50100970122640177
 ኩባ0808160118940341
 ካሜሩን0723330116343397
 ጋና01046401154999
 ቡልጋሪያ57841371108150190
 ሆንግ ኮንግ23339010364699
 ጅቡቲ0789009742183
 ኮት ዲቯር06280095214310
 ቱኒዚያ068132090938190
 ናይጄሪያ06482087328197
 ቆጵሮስ06791507901398
 ላቲቪያ176346077811133
 ጊኒ0591007616164
 አንዶራ037717072337309
 ሊባኖስ652626068822140
 ኮስታ ሪካ0495606816180
 ቦሊቪያ63588336724044
 አልባኒያ292514066327385
 ኒጄር04470066222193
 ኪርጊዝስታን193211116318302
 ቡርኪና ፋሶ01810060939389
 ኡራጓይ020010054912337
 ሆንዱራስ94411015194731
 ሳን ማሪኖ0386404884062
 ፍልስጤም638400480492
 ሴኔጋል37216104796257
 ማልታ1238204453204
 ጆርዳን0113504357315
 ታይዋን1168004276253
 ቡታን4304604205111
 ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ18305003772547
 ጓተማላ26307323421025
 ስሪ ላንካ5221203357107
 ሞሪሸስ059303299261
 ሞንቴኔግሮ1195703165116
 ኬንያ0206203031483
 ቬኔዝዌላ01664029810122
 ማሊ0203002931773
 ሶማሊያ02742028684
 ታንዛኒያ0263702841011
 ቬት ናም044802680224
 ጃማይካ021800252628
 ኤል ሳልቫዶር1317521250867
 ፓራጓይ014210213962
 ፋሮ ደሴቶች29001870178
 Congo016400186616
 ጋቦን014011166224
 ሱዳን22135001621314
 ሩዋንዳ06900153084
 ብሩነይ018201381119
 በርማ41130012759
 ካምቦዲያ012101220110
 ማዳጋስካር06310121058
 ኢትዮጵያ09200116321
 ትሪኒዳድና ቶቤጎ07000115837
 ላይቤሪያ07300101820
 አሩባ03040100268
 ቤርሙዳ05510099539
 ሞናኮ0642094327
 ማልዲቭስ8782094016
 ቶጎ0260088656
 ኢኳቶሪያል ጊኔ076008417
 ቡታን980008211
 ሊክተንስታይን0250081155
 ባርቤዶስ0434076627
 ዛምቢያ0361074335
 Bahamas5491070912
 ጋያና051506779
 ዩጋንዳ0170063046
 ሃይቲ056006242
 ሴየራ ሌዎን055006106
 ሊቢያ0440060115
 ቤኒን0260054127
 ጊኔ-ቢሳው047005003
 ኔፓል238004709
 ማካው0181045027
 ሶርያ033004236
 ሞዛምቢክ033004108
 ኤርትራ033003906
 ሞንጎልያ027003508
 ማላዊ1027103333
 ቻድ025003308
 ስዋዚላንድ022003118
 ዚምባብዌ022002842
 አንጎላ017002526
 አንቲጋ እና ባርቡዳ0111024310
 ምሥራቅ ቲሞር022002301
 ቦትስዋና021002210
 ላዎስ015001904
 ቤሊዝ011101825
 ፊጂ010001808
 ዶመኒካ07001609
 ናሚቢያ09001607
 ግሬናዳ09401506
 ሰይንት ኪትስና ኒቨስ014001501
 ሰይንት ሉሻ000015015
 የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ040014010
 ሰይንት ቪንሰንትና ዘ ግረነዲንዝ010001303
 ቡሩንዲ06001114
 ግሪንላንድ000011011
 ሲሸልስ05001106
 ኒካራጓ01001027
 ጋምቢያ07001012
 ሱሪናም03001016
 ቫቲካን ከተማ0700902
 ፓፑዋ ኒው ጊኒ0800800
 ሞሪታኒያ0000716
 ቡታን0400703
 ሳን ቶሜ እና ፕሪንሲፔ0400400
 ደቡብ ሱዳን0400400
 የመን0100100
  1. The Novel Coronavirus Pneumonia Emergency Response Epidemiology Team. The Epidemiological Characteristics of an Outbreak of 2019 Novel Coronavirus Diseases (COVID-19) – China, 2020. China CDC Weekly, 2020, 2(8): 113–122.
  2. Roser, Max; Ritchie, Hannah; Ortiz-Ospina, Esteban (4 March 2020). "Coronavirus Disease (COVID-19)". Our World in Data. https://ourworldindata.org/coronavirus በ12 March 2020 የተቃኘ.
  3. WHO-China Joint Mission (16–24 February 2020). "Report of the WHO-China Joint Mission on Coronavirus Disease 2019 (COVID-19)". World Health Organization.
  4. "Coronavirus incubation could be as long as 27 days, Chinese provincial government says". Reuters. 22 February 2020. https://www.reuters.com/article/us-china-health-incubation/coronavirus-incubation-could-be-as-long-as-27-days-chinese-provincial-government-says-idUSKCN20G06W.
  5. Kampf, G.; Todt, D.; Pfaender, S.; Steinmann, E. (March 2020). "Persistence of coronaviruses on inanimate surfaces and their inactivation with biocidal agents". The Journal of Hospital Infection 104 (3): 246–251.
  6. "Coronavirus Live Updates". በእ.ኤ.አ. 23 April 2020, 16:08 UTC+03:00 የተወሰደ.