መርጡለ ማርያም

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
መርጡለ ማርያም
Mertulemariam.jpg
የመርጡለ ማርያም አቅድ
ከፍታ 2750ሜ
መርጡለ ማርያም is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
መርጡለ ማርያም

10°49′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°16′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


መርጡለ ማርያም በምስራቅ ጎጃም፣ ሞጣ አውራጃ ውስጥ የሚገኝ ጥንታዊ ቤ/ክርስቲያን ሲሆን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተሰራው አክሱም ጺዮን ቀጥሎ የተሰራ ሁለተኛው ቤ/ክርስቲያን ነው። የሃድያዋ ንግስት እሌኒ ግብጻውያንን በማስመጣት በ1510 የጥንቱ ቤ/ክርስቲያን በግምብ ተሰርቶ እንዲሻሻል አደረገች ። [1] ነገር ግን በ1529-30፣ አጠቃላይ ቤ/ክርስቲያኑ በግራኝ አህመድ እንዲፈርስ ተደረገ። በ1540ወቹ ውስጥ በአጼ ገላውዲወስ አነሳሽነት ቤ/ክርስቲያኑ እንደገና ታነጸ። ነገር ግን በ1560 ወቹ መልሶ በተንቀሳቃሽ የኦሮሞ ቡድኖች ጉዳት ደረሠበት። ለግማሽ ምዕት አመት እንደፈረሰ ቆይቶ በአጼ ሱሰኒዮስ ዘመን ጀስዩቱ ብሩኖ ብሩኒ ንግስት እሌኒ ባሰራቸው ቤ/ክርስቲያን ፍርስራሽ ድንጋይ በመጠቀመም እንደገና ቤ/ክርስቲያኗን እንዳነጸ ጻህፍት ይዘግባሉ [2]

ታሪካዊ ክስተቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ንግስት እሌኒ በመርጡለ ማሪያም እንደተቀበረች ይነገራል።
  • በ1604 ሱሰኒዮስ በመርጡለ ማርያም የዙፋን አክሊል እንደደፋ በታሪክ ተመዝግቧል።


ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Guida, consoziazione turisticta Italiano, Milano, 1938, p398
  2. ^ Cheesman, "lake Tana and the Blue Nile" p269