መርጡለ ማርያም
መርጡለ ማርያም | |
የመርጡለ ማርያም ገዳም | |
ከፍታ | 2750ሜ |
መርጡለ ማርያም በምስራቅ ጎጃም፣ ሞጣ አውራጃ ውስጥ የሚገኝ ጥንታዊ ቤ/ክርስቲያን ሲሆን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተሰራው አክሱም ጺዮን ቀጥሎ የተሰራ ሁለተኛው ቤ/ክርስቲያን ነው።
የሃድያዋ ንግስት እሌኒ ግብጻውያንን በማስመጣት በ1510 የጥንቱ ቤ/ክርስቲያን በግምብ ተሰርቶ እንዲሻሻል አደረገች ። [1] ነገር ግን በ1529-30፣ አጠቃላይ ቤ/ክርስቲያኑ በግራኝ አህመድ እንዲፈርስ ተደረገ። በ1540ወቹ ውስጥ በአጼ ገላውዲወስ አነሳሽነት ቤ/ክርስቲያኑ እንደገና ታነጸ። ነገር ግን በ1560 ወቹ መልሶ በተንቀሳቃሽ የኦሮሞ ቡድኖች ጉዳት ደረሠበት። ለግማሽ ምዕት አመት እንደፈረሰ ቆይቶ በአጼ ሱሰኒዮስ ዘመን ጀስዩቱ ብሩኖ ብሩኒ ንግስት እሌኒ ባሰራቸው ቤ/ክርስቲያን ፍርስራሽ ድንጋይ በመጠቀመም እንደገና ቤ/ክርስቲያኗን እንዳነጸ ጻህፍት ይዘግባሉ [2]
ኢትዮጵያ |
ታሪካዊ ቦታዎች • አክሱም • ላሊበላ • ጎንደር • ነጋሽ • ሐረር • ደብረ-ዳሞ • አዲስ አበባ |
|
-
መርጡለ ማርያም
-
በራፍ- መርጡለ ማርያም
-
መርጡለ ማርያም
-
መስኮት- መርጡለ ማርያም
-
መርጡለ ማርያም