Jump to content

ግብፅ

ከውክፔዲያ
የ14:16, 12 ዲሴምበር 2023 ዕትም (ከ78.60.146.70 (ውይይት) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

የግብፅ ዐረብ ሪፐብሊክ
جمهوريّة مصرالعربيّة
ጉሙሪየት ምስር አል-አረቢያህ

የግብፅ ሰንደቅ ዓላማ የግብፅ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር ሀገሬ፣ ሀገሬ፣ ሀገሬ
(አረብኛ) بلادي، بلادي، بلادي
የግብፅመገኛ
የግብፅመገኛ
ግብፅ በአረንጓዴ ቀለም
ዋና ከተማ ካይሮ
ብሔራዊ ቋንቋዎች አረብኛ
መንግሥት
{{{ፕሬዝዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር
 
አብደል ፋታህ አል ሲሲ
ሸሪፍ ኢስማኤልስ
ዋና ቀናት
ሰኔ ፲፩ ቀን ፲፱፻፵፭
(ጁን 18, 1953 እ.ኤ.ኣ.)
 
የነጻነት ቀን ከዩናይትድ ኪንግደም
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
1,002,450 (30ኛ)

0.632
የሕዝብ ብዛት
የ2012 እ.ኤ.አ. ግምት
የ2006 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
 
90 ሚሊዮን (15ኛ)

76,699,427
ገንዘብ የግብፅ ፓውንድ
ሰዓት ክልል UTC +2
የስልክ መግቢያ +20
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን .eg፣ مصر.

ግብፅ ወይም ምጽር፣ ምሥር (አረብኛ مصر ) በሰሜን ምስራቅ ኣፍሪካ የምትገኝ አገር ናት። 77 ሚሊዮን ከሚሆነው ህዝቧ አብዛኛው ከናይል ወንዝ ዳርቻ በአንድ ኪሎሜትር ክልል ውስጥ ይገኛል። የግብፅ አብዛኛው መሬት በሰሃራ በረሃ ክልል ውስጥ ይገኛል። ዋና ከተማዋ ካይሮ ስትሆን ከአፍሪካም ትልቋ ከተማ ናት። ሌላ ትኩረት የሚሰጣት ከተማ አሌክሳንድሪያ (እስክንድርያ) ናት። አሌክሳንድሪያ የአገሪቱ ዋና ወደብ ስትሆን በህዝብ ብዛት ከአገሪቱ ሁለተኛ ናት።

ግብፅ በሰሜን ከሜዴቴራኒያን ባሕር በምሥራቅ ከቀይ ባሕር፤ በደቡብ ከኖብያ፤ በምዕራብ ከምድረ በዳው አገር ይዋሰናል። ነጭ አባይ በግብፅ መካከል ያደርግና ከደቡብ ወደ ምሥራቅ ይሄዳል። የአባይ ወንዝ የሚሞላው በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው። በግብፅ የሚዘንበው አንድ አንድ ጊዜ ብቻ ስለ ሆነ ግብፅ በአባይ ለምቶ ይኖራል።


ግብፅ የመጀመሪያ ቀደምት ስልጣኔ ያላት ሀገር ናት። ከ3000 ዓዓ የተነሳው ጥንታዊ የግብፅ ስልጣኔ፣ በስነ ቅርፅ፣ ኪነጥበብ፣ ምህንድስናና ቴክኖሎጂ የላቀ ሲሆን በቡዙ ስነ ቅሪትና ሳይንሳዊ ምርምር ላይ የዋለ ነው። በተጨማሪም ግብፅ ለሶስት ሺህ አመት በዘውዳዊ ግዛት ስትመራ ነበር። በ3150 ዓዓ ንጉስ ሜኔስ የግብፅ የተዋሀደ ስልጣኔ አስጀመረ። የታላቁ ጊዛው ፒራሚድ በ2600 ዓዓ በአራተኛው የግብዕ ስርወ መንግስት ፈርኦን በነበረው ኩፉ የተገነባ ሲሆን፣ በአለም አንደኛ የሆነ የቱሪስት መስህብነት ያለው ሀውልት ነው። ነገር ግን ይህ ፒራሚድ በወቅቱ የነበሩት የፈርኦኖች ሰይጣንን ማምለኪያ እና መናፍስት የመጥሪያም ሀውልት መሆኑም ይታውቃል። ይህ ሀውልት ለተጓዳኝ የሮማ ወይም የአሁኑ ምዕራብያውያን ስልጣኔ ተረፈ ምርት ሆኖ እያገለገለ ነው። በተጨማሪም የምዕራብያውያን አጋንንታዊ ማምለኪያ ምልክት ሊሆን ችሏል። ኢሉሚናቲ እና አሜሪካ በማህተሟ ላይ በመጠቀም የሚመጣውን ሰይጣናዊው አምባገነናዊው የአለም መንግስት የሚመኙበትን ዘዴ ያሳያል። ግብፅ በጥንት ዘመን የክርስትና ቁንጮ የሆነች ሀገር ነበረች፣ ነገር ግን በ7ተኛው ክፍለ ዘመን እስልምና ሲስፋፋ ወዲያውኑ የእስላም ሀገር ሆናለች። ግብፅ በ1922 ዓም ከእንግሊዝ ቀኝ ግዛት ስትወጣ፣ ከእስራኤል ጋር ብዙ የድንበር ጦርነት አድርጋልች። በ1978 ዓም፣ ግብፅ የጋዛን ግዛት በመተው እስራኤል እንደሀገር እንደሆነች ተገነዘበች። ከዛም በኋላም ግብፅ በብዙ የፓለቲካ አለመረጋጋት አሳልፋለች። ከ2011 ዓም አብዮት ጀምሮ ግብፅ በግማሽ የርዕሰ ብሄር አስተዳደር ትመራለች። የግብፅ ያሁኑ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ ኢል ሲዝ በብዙ ሀያሲያን አምባገነናዊ አመራር እንዳለው ተናግሯል።

ግብፅ የክልል ሀያላን የሆነች ሀገር ናት። የግብፅ ህዝቦች ምንም እንኳን ፈሪሃ እግዚአብሄር ያደረባቸው ሀይማኖተኛ ቢሆኑም፣ ከምዕራብያውያን ጋር በመተባበር አዲሱን አምባገነናዊ የአለም መንግስት ለመመስረት እየነደፉበት ይገኛሉ። በተጨማሪም ግብፅ የሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አጠቃላይ ፓለቲካ ለመቆጣጠርና ሀያልነቷን ለማጠናከር ከአሜሪካ ጋር እየሰራችበት ይገኛል።

ግብፅ በታሪክ ታዋቂ ጥንታዊ ሀይማኖት የነበራት ሲሆን ይህም ሀይማኖት ከጥንቆላና፣ መናፍስትን ከመሳብ ጋር ተያያዥነት አለው። ስለሆነም የግብፅ ሀይማኖት በምዕራብያውያን ዘንድ እጅግ ተወዳጅነት ያገኘ ሆኗል። ፍሪሜሰንሪ የተባለው ሰይጣናዊው ድርጅት የጥንታዊቷን ግብፅ ስልጣኔ በመጠቀም እንደራሱ ጥበብ በማዋል ታላቋን የሮማ (ምዕራብያውያን) ስልጣኔ አስነስቷል። ይህም ለሚያመጡት አምባገነናዊው የሰይጣን መንግስት ለመመስረት ሲባል ነው። ግብፅ የኒው ወርልድ ኦርደር፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአረብ ሊግ አባል ናት።

ጥንታውያን የግብጽ ባለሥልጣኖች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

መጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ከማየ አይኅ ቀጥሎ መጀመሪያ የአፍሪካ ሕዝብ የኖኅ ልጅ የካም ዘሮች ናቸው፤ ይህ አገር ሰናዖር ለሚሉት ቅርብ ስለ ነበር የባብል ግንብ ከተሠራ በኋላ ከዚህ ተነስተው ወደ ግብፅ ወረዱ።

የግብጽ ቀድሞ ዘመን መንግሥት ዋና ጥንታዊ ነው፤ የመሠረተውም ፈርዖን ሜኒስ የተባለው ነው። ጸሓፊው ጊዮርጊስ ስንቄሎስ (፰፻ ዓ.ም. አካባቢ የጻፈው) ይህ ፈርዖን ሜኒስ በዕውነት የካም ልጅ ምጽራይም እንደ ነበረ ገመተ።

ዳሩ ግን አባ አውሳብዮስ በጻፉት ዜና መዋዕል ዘንድ (፫፻፲፯ ዓ.ም. ተጽፎ)፣ የድሮ ግብጻዊው ባለታሪክ ማኔጦን (፫ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.) ስለ ኋለኞቹ ግብጻውያን ሲጽፍ፣ ይኮሩበት የነበረው የታላቁ ጥንት ዘመን ከማየ አይህ አስቀድሞ እንዳለፈ፣ በኋላም በዚያው አገር ዳግመኛ ከሠፈረበት ከካም ልጅ ምጽራይም በውኑ እንደ ተወለዱ ጽፎ ነበር። ተመሳሳይ ታሪክ በእስላም ጸሐፊዎች በግብጻዊው እብን አብድ ኤል-ሀከም እና በፋርሳውያን አል-ታባሪሙሐመድ ቈንዳሚር መጻሕፍት ሲገኝ፣ ፒራሚዶችእስፊንክስ ወዘተ. ሁሉ የተሠሩ ከጥፋት ውኃ በፊት በኖሩት ክፉ ዘሮች ሆኖ፣ ከዚያ በኋላ ግን አገሩ ለካም ተወላጅ ለምጽራይም ('ማሣር' ወይም 'መሥር') ተሠጠ ብለው ጻፉ።

በግሪኩ ጸሐፊ ሄሮዶቶስ ዘንድ፣ የግብፅ ቀድሞ ዘመን የመጀመሪያው ፈርዖን ሜኒስ ነጭ አባይን ከመነሻው ወደ ጎን መለሰና ውሃው ይፈስበት በነበረው ላይ ሜምፊስ የተባለውን ከተማ ቆረቆረ። ታላቅ ንጉሥም ስለ ነበረ ከሞተ በኋላ ሕዝቡ እንደ አምላክ አድርገው አመለኩት። በዘመናዊ አስተሳስብ፣ ይህ ላይኛ ግብጽታችኛ ግብጽ ያዋሐደው መጀመርያው ፈርዖን መታወቂያ ለሥነ ቅርስ ከሚታወቀው ፈርዖን «ናርመር» ከተባለው ጋር አንድ ነው።

ናርመር (ሜኒስ) አገሩን ካዋሐደ አስቀድሞ ሌሎችም ነገሥታት (ለምሳሌ ንጉሥ ጊንጥ) በአገሩ ክፍሎች ብቻ ላይ እንደ ነገሡ ከተገኙት ቅርሶች (የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ ወይም የጊንጥ ዱላ እንደሚያሳይ) ይታወቃል።

የሃይሮግሊፍ ቅርሶችና መዝገቦች ለማንበብ ችሎታው አሁን ስላለ፣ ሜኒስ ከነገሠ በኋላ የግብፅ ታሪክ በጥቂት መጠን ተገልጾአል። መጀመርያው ሥርወ መንግሥታት (፩ኛው እስከ ፮ኛው ድረስ) የቀድሞ ዘመን መንግሥት ይባላሉ። በ፩ኛው ሥርወ መንግሥት ሰባአዊ መስዋዕት በሰፊ ይደረግ ነበርና ከፈርዖኖቹ ጋራ ብዙ ሎሌዎች አብረው ይቀበሩ ነበር። የሔሩ ወገን በሴት ወገን ላይ ይበረታ ነበር። በ፪ኛው ሥርወ መንግሥት የፈርዖኖች መቃብር ከተማ ከላይኛ ግብጽ ወደ ታችኛ ግብጽ (ስሜኑ) ተዛወረ። በኋለኛ 2ኛው ሥርወ መንግሥት ዘመን የሴት ወገን ወኪል ፈርዖን ፐሪብሰን ተነሣና ያንጊዜ ትግሎች እንደ በዙ ይመስላል። በ፫ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያ የሔሩ ወገን ለሥልጣን ተመልሶ፣ ነጨሪኸት የተባለው ፈርዖን የመጀመርያውን ሀረም (ፒራሚድ) አሠራ። ከርሱም በኋላ የተነሡት ታላላቅ ፈርዖኖች በጊዛ ሜዳ ላይ ፒራሚዶቻቸውን እንዲሁም የጊዛ ታላቅ እስፊንክስን ሠሩ። በ፬ኛውም ሥርወ መንግሥት የፈርዖኖች ዝሙት የገዛ እኅቶቻቸውን እስከሚያግቡ ድረስ ደረሰ። በ፭ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ፈርዖኖች በሀረሞቻቸው ውስጥ የሀረም ጽሕፈቶች ያስቀረጹ ጀመር፤ እነኚህ ጽሕፈቶች የሔሩ ተከታዮች ወገን (ወይም «ደቂቃ ሔሩ») በሴት ተከታዮች ወገን ላይ የፈጸሙትን ጨካኝ የጭራቅነት ሥነ ስርዓት ይመሰክራሉ። ይህም አስጨናቂ ሁኔታ በ፮ኛው ሥርወ መንግሥት እየተቀጠለ ፈርዖኖቹ ዓለማቸውን ሁሉ ከነጎረቤቶቻቸውም ጋር በጽናት ይገዙ ነበር።

፮ኛው ሥርወ መንግሥት ከነገሠ በኋላ የግብፅ ታሪክ እጅግ ግልጽ ሆኖ አይታይም። በታሪክ ጸሐፍት እንደ ማኔጦን ዝርዝሮች በኩል፣ ለ፯ኛው-፰ኛው ሥርወ መንግሥታት በርካታ ስሞች ቢመዘገቡም፣ ከጥቂቶቹ ብቻ በስተቀር አንዳችም ሥነ ቅርሳዊ ማስረጃ ከቶ ስላልተገኘላቸው፣ ስሞች ብቻ ቀርተው በእውነት እንደ ኖሩ ወይም ዝም ብለው በማስመስል እንደ ተፈጠሩ አይታወቀም። ከቀድሞውም ዘመን በኋላ በእርግጥኛነት የነገሡት መጀመርያ ፈርዖኖች የግብጽ መካከለኛውን ዘመን መንግሥት የመሠረቱት በስማቸውም ውስጥ «ታ-ዊ» (ሁለቱ አገራት ወይም በዕብራይስጥ ምስራይም) የተባሉት ናቸው።

የግሪክ ጸሐፍት አፈ ታሪክ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በ6ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ኒቶክሪስ የተባለች ሴት የአገሩ ንግሥት እንደ ሆነች የሄሮዶቶስና የማኔጦን ታሪኮች ይነግራሉ። ሄሮዶቶስ እንደሚለው፣ ወንድሙዋን ግብፆች ስለ ገደሉባት እሷም ልትበቀልለት አሰበች። ለዚሁ ጉዳይ ከመሬት ውስጥ አንድ ታላቅ አዳራሽ አሠራች። ከዚያም ታላቅ ግብር አዘጋጅታ የወንድሙዋን ገዳዮች ወደዚሁ ግብር ጠራቻቸው። የተጠሩትም በግብፅ ግዛት የታወቁ ክቡራን ነበሩ። እንዲሁ ሆኖ ሳለ በድንገት ከውጪ በራሳቸው ላይ ውካታና ፍጅት ጩኸትም ተነሳ። የጥፋት ውሃ አዳራሹን ሰብሮ ገባ። ንግሥት ኒቶክሪስ አስቀድማ የወንዙን ውሃ በሚስጥር ወደ አዳራሹ እንዲገባ አድርጋ ነበርና ውሃው በዚያ ታላቅ ግብር ላይ እንዲለቀቅ አደረገች። በዚያም የገቡ ሁሉ ሰጥመው ቀሩ። ይህ የኒቶክሪስ ታሪክ በሄሮዶቶስም ሆነ በማኔጦን ቢገኝም፣ በዘመናዊ ሥነ ቅርስ አስተያየት ለዘመንዋ ምንም ማስረጃ ስላልተገኘ አሁን እንደ አፈ ታሪካዊ ንግሥት ብቻ ትቆጠራለች።

በግሪኮች የታሪክ ጸሐፍት ዘንድ ሌላ ስመ ጥሩ ፈርዖን ሲሶስትሪስ ነበር። ይህ ንጉሥ ዓለምን ለማሸነፍ አስቦ ከግብፅ ሲነሣ የሚሊዮን እኩሌታ የሚሆኑ እግረኛ ወታደሮች፣ ፳፬ ሺህ ፈረሰኞች፤ ፳፯ ሺህ የተሰናዱ ሠረገሎች እንደ ነበሩት ይተረኩ ነበር። ዝና ፈላጊነቱ በክብር ተፈጸመለትና ትልቅ ድል አገኘ። በየሄደበት ስፍራ ሁሉ ከእብነ በረድ የተሠራ ሐውልት አቆመ። የሚመጣው ትውልድ እንዳይረሳው ባቆመው ሐውልት ላይ ጽሕፈት እንዲቀረጽበት አደረገ። በብዝዎቹ ሐውልት ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎአል።

«ንጉሠ ነገሥት ሲሶስትሪስ በጦር ሠራዊቱ ኅይሉ ይህን አገር አሸንፎዋል»

ነገር ግን ዘመናዊ የታሪክ ጸሓፊዎች እንደዚህ አላደረገም ብለው ይጠራጠራሉ። በማኔጦን ነገሥታት ዝርዝር «ሴሶስትሪስ» የሚባል ፈርዖን በ12ኛው ሥርወ መንግሥት በፈርዖን 3 ሰኑስረት (ሰንዎስረት) ፋንታ ይታያል። ስለዚህ የሴሶስትሪስ አፈ ታሪክ ከሰንዎስረት ትዝታ እንደ ተወረደ ይታመናል።

ጵቶልሚዮስና ንግሥት ክሌዎፓትራ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሺሻክ የተባለ የግብፅ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን ስለ ያዛት የሰሎሞን ቤተ መቅደስ በዝብዞ ንዋየ ቅድሳቱን ሁሉ ጠርጉ ወሰደው።

አሚኖፌስ የተባለ ስመ ጥሩ የግብፅ ንጉሥ ነበር፤ ይህም ምናልባት ለስሙ መጥሪያ (ለመታሰቢያው) ብሎ አንድ ትልቅ መቅደስና ምስል ያቆመ ሜምኖን የተባለው ንጉሥ ሳይሆን አይቀርም። የዚህም ፍራሽ እስከ ዛሬ በቴቤስ ይታያል። ያቆመውም የድንጋይ ምስል ፀሓይ ስትወጣ ደስ የሚያሰኝ ቃል ፀሓይ ስትጠልቅ የኅዘን ቃል ያሰማል ይባላል። ዛሬም በዚያ የሚያልፉ መንገደኞች ድምፁን የሚሰሙ ይመስላቸዋል።

፭፻፳፭ ዓመት ከዘመነ ክርስትና በፊት ካምቢሲስ ንጉሠ ፋርስ ግብፅን ድል አድርጎ ነበረና ሳሜኒቱስ የተባለውን የግብፅን ንጉሥ የወይፈን ደም በግድ ስለ አስጠጣው እንደ መርዝ ሆነበትና በዚሁ ጠንቅ ሞተ።

፫፻፴፪ ዓመት ከዘመነ ክርስትና በፊት የመቄዶንያው ንጉሥ ታላቁ እስክንድር ግብፅን ድል አድርጎት ነበር። በዚህ ስፍራ እስክንድሪያ የተባለ አንድ ስመ ጥሩ ከተማ ሠራ። ይህም ከተማ በዓለም ከታወቁት ከተሞች እጅግ ጥሩ ሆኖ የተሠራና መሰል የሌለው አያል መቶ ዓመት የቆየ ቤተ መንግሥት መሆኑ ታውቆዋል። የጥንቱ ሥራው ፈራርሶ ዛሬ የሚታየው እስክንድሪያ ከጥንቱ በጣም ያነሰ ነው።

እስክንድር ሲሞት በዚሁ በእስክንድርያ ተቀበረ። ይኸው ከተማ ስመ ጥሩ በመሆኑ እስከ ዛሬ በግብፅ ዋና የንግድ ሁለተኛ ከተማ ተብሎ ይጠራል።

እስክንድር የሱ ጀኔራል የነበረውን ጵቶልሚዎስን አገሩን እንዲገዛ ሾመው። ከጵቶልሚዎስ ጀምሮ ተወላጆቹ ሁሉ የንጉሥ ዘር ተብለው ሁሉም ጵቶልሚዎስ ተብለዋል። ፪፻፺፬ ዓመት ገዝተዋል። ከነዚህም በመጨረሻ የነገሠው ጵቶልሚዎስ ዲዮናስዮስ ይባላል። በላዮ የገዛ ሚስቱ ተነሥታ ሸፈተችበትና ተዋጋችው። ጵቶልሚዎስ ዲዮናስዮስ በመጨረሻ ድል ሆነና ለማምለጥ የማይሆንበት ቢሆን በነጭ ዐባይ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ሰጠመ። ሚስቱ ክሌዎፓትራ የተባለች የግብፅ ዋና ገዢ ሆነች። አሉ ተብለው ከሚጠሩት ቆነጃጅት አንዲቱ እርስዋ ነበረች። ስጦታዋና ተፈጥሮዋ ከውበትዋ ጋር የተካከሉ ነበሩ። ዳሩ ግን ክፉ ነበረች። ከሠራችው ሁሉ እጅግ የሚያሰቅቀው ነገር ያሥራ አንድ ዓመት ሕፃን የነበረውን የገዛ ወንድምዋን በመርዝ ማስገደልዋ ነው። ምንም ክፋትዋን ዓለም ቢያውቀው እኔ ነኝ ያለ ጀግና የውበት ማጥመጃዋን ሊቃወም የሚችል አልተገኘም። Whole paragraph is POV

ማርክ አንቶኒ የተባለ የሮማ ጀኔራል በግሪክ አገር ፊሊጵ በተባለች አውራጃ ብሩተስንና ካሲውስን ድል ባደረገ ጊዜ ከሜዴቴራኒያን ባሕር በሰሜን ምሥራቅ ወደምትሆን ወደ ሲሲሊያ እንድትመጣ ክሌዎፓትራን አስጠራት። ምክንያቱም ለብሩተስ ረድታ ነበርና ሊቀጣት አስቦ ነበር።

ክሌዎፓትራ ጥሪው እንደ ደረሳት እሺ ብላ በፍጥነት ተነሥታ በተለይ በወርቅ ባጌጠ ታንኳ ገባች። ታንኳው በሽራው ፈንታ ዋጋው የበዛ የከበረ ሐር ነበረው። ታንኳውን በብር መቅዘፊያ የሚቀዝፉት የተወደዱ ቆነጃጅት ነበሩ።

ንግሥት ክሌዎፓትራ ሐር ተጋርዶላት በመርከቡ ተደግፋ ተቀምጣ ነበረች። እንደዚህ ሁና ሲድኑስ በተባለው ወንዝ ተንሳፈፈች። ያለችበትም ታንኳ እጅግ ያማረ ነበር። እርስዋም ራስዋ የተወደደች ነበረች። የሚታየው ሁለመናዋ ሕልም ይመስል ነበር።

ከታንኳው መጋረጃ ነፋስ እየጠቀሰ የሚወስደው ሽቶ እያወደ ክሌዎፓትራ እንደ ተቃረበች ማርክ አንቶኒን አስጠነቀቀው። ከሩቅ ልብ የሚነካ የሙዚቃ ድምፅ ይሰማ ነበር። ቀጥሎ የብር መቅዘፊያው ሲብለጨለጭ ከሩቅ ይታይ ነበር።

ነገር ግን አንቶኒ የግብፆችን ንግሥት በተመለከተ ጊዜ ምንም አላሰበም። ማርክ አንቶኒ ከክሌዎፓትራ እስኪገናኝ ድረስ ክቡር ሰውና ጀግና መሆኑን አሳየ እንጂ ከዚያ በኋላ ግን ፍጹም እንደ ባሪያዋ ሆነ።

ከክሌዎፓትራና ከርሱ ክፉ አካሄድ የተነሣ ኦክታቢዎስ ከተባለ ከሌላ የሮማ ጀኔራል ጋር በግሪክ አገር አክቲውም በተባለች አውራጃ ላይ ተዋግተው አንቶኒ ድል ሆነና በገዛ ሰይፉ ወድቆ ሞተ። ክሌዎፓትራም ኦክታቢዎስ በሕይወትዋ ወደ ሮማ የወሰዳት እንደ ሆነ በሕዝብ መኻከል እንደሚያጋልጣት ተረዳችው።

ስለዚህ ለመታገሥ የማይችል ሲሆንባት ጊዜ በግብፅ አገር አንድ ዐይነት በተናከሰ ጊዜ ሕመሙ የማይሰማ መርዛም እባብ ስላለ ክሌዎፓትራ ከንደዚህ ያለ መርዛም እባብ አንዱን አሲዛ አስመጥታ ሰውነቷን አስነከሰች። ትንሽ ቆይታ ሁለመናዋ ደነዘዘ አበጠ ወዲያው ልቡዋ መምታቱን አቆመ። ውበት የነበራት ክፋዩቱ የግብፅ ንግሥት ክሌዎፓትራ እንደዚህ ሆና ፴ ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት ሞተች።

ተከታይ ታሪክ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከንግሥት ክሌዎፓትራ ሞት በኋላ ግብፅ ለሮማ መንግሥት ተገዛና እስከ ዘመነ ክርስትና ፮፻፵ ዓመት ድረስ የምሥራቅ መንግሥት እየተባለ ለሮማ እንደ ተገዛ ቆየ። ከዚህ በኋላ ሳራሲኖች ድል አደረጉትና እስከ ፮፻ ዓመት ቆየ።

የሳራሲን ገዦች ያሠለጠኗቸው ማምሉኮች የተባሉት የገዛ ዘበኞቻቸው ሳራሲኖችን ከዙፋናቸው ዘርጥጠው አወረዷቸው። ቱርክ መጥቶ ድል እስኪያደርጋቸው ድረስ ማምሉኮች ግብፅን እስከ ፲፯፻፱ ገዝተዋል። ቱርኮችም ግብፅን እስከ ፲፯፻፺፰ ዓመት ገዝተዋል። ከዚህ በኋላ ናፖሊዮን ቦናፓርቲ አርባ ሺህ የሚሆን የጦር ሠራዊት ከፈረንሳይ አገር አምጥቶ፤ ግብፅን ወረረ።

ቱርኮችም ግብፅን ከያዙ ወዲህ ማምሉክ የተባለውን ጭፍራ ወደ ሥራቸው አግብተው ጠብቀውት ነበርና እነዚህ ተስፋ እስኪቆርጡ ድረስ ተከላከሉ። ጦርነቱን የሚዋጉበት ስፍራ በፒራሚዱ አጠገብ ነበር። በዚያ ሲዋጉ ሳሉ እኩሌቶቹ እዚያው ታረዱ። ሌሎቹም እየዘለሉ ወደ ነጭ ዐባይ ወንዝ ባሕር ሰጠሙ። ከዚህ ጦርነነት በኋላ ናፖሊዮን ቶሎ ብሎ ወዲያው ወደ ፈረንሳይ አገር ተመለሰ እንጂ በዚህ አልዘገየም። ሲሄድም ጀኔራል ክሌበር የተባለውን ለፈረንሳይ ጦር ጠቅላይ አድርጎት ሄደ።

ጀኔራል ክሌበር ጀግና ሰው ነበር። ዳሩ ግን ጨካኝ ነበርና ጨካኝነቱ ሕይወቱን እስከ ማጣት አደረሰው።

ይኸው ጨካኙ ጀኔራል አንድ ቀን ሼህ ሳዳ የሚባል አንድ ሽማግሌ እስላም አገኘና ውስጥ እግሩን በከዘራ አስደበደበው። ወዲያው ትንሽ እንደ ቆየ ጀኔራሉ ወደ መስጊድ ገብቶ ሳለ አንድ የተናደደ እስላም ገሠገሠና በጩቤ ቢሽጥበት ያን ጊዜውኑ ሞተ።

በ፲፰፻፩ ዓመት እንግሊዝ ፈርንሳዮችን ከግብፅ ለማስወጣት ከብዙ ጦር ጋራ ሰር ራልፍ አቤሮክሮምቢን ሰደደው። ጀኔራል መኑ የፈረንሳይ ኮማንደር ነበር። አቡኬር ላይ ተዋጉና ሰር ራልፍ አቤሮክሮምቢ ድል አደረገው። ዳሩ ግን እርሱም ራሱ ክፉኛ ቆስሎ ነበር።

በዚያው ዓመት የፈርንሳይ ጦር ተሸነፈና ከግብፅ ወጥቶ በመርከብ ተሳፍሮ ወደ ፈረንሳይ አገር ተመለሰ። ዳሩ ግን ባላገሮቹ ከፊተኞቹ ገዢዎቻቸው ከቱርኮች ይልቅ የፈረንሳይ ጀኔራል ቅን ፍርድ እየፈረደ በመልካም አገዛዝ በደንብና በሕግ ይገዛቸው ነበርና በመሄዱ እጅግ አዝነው ተላቀሱ።

የዛሬው የግብፅ ዋና ከተማ ትልቁ ካይሮ ነው። ቀድሞ ከነበረው ይልቅ የዛሬው በጣም ትንሽ ነው። ነገር ግን ፫፻ ሺህ ሰዎች ይኖሩበታል።

የቤት ሥራ አሠራር ዕውቀትና የድንጋይ መውቀር ብልሀት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከሦስትና ከአራት ሺሕ ዓመት በፊት ብዙ ሚሊዮን ሕዝብ እንደ ነበረ እጅግ ለዐይን ያማሩ ታላላቅና ሰፋፊ የነበሩ የከተሞቻቸው ፍራሽ በመገኘታቸው እንረዳለን። በጥንቱም ሆነ ወይም በዛሬው አስተያየት ስንገምተው እጅግ ደምቆ የሚታይ ከተማ እንደ ቴቤስ ያለ አይገኝም። Huge POV ባለመቶ በር ከተማ ይሉታል። በጦር ጊዜ ከዚህ ከተማ በያንዳንዱ በር የሚወጣው የጦር ሠራዊት እንደሚከተለው ነው። መሣሪያቸው የተሰናዳ ፪፻ ሠረገሎችና ፪ ሺሕ ወታደሮች ናቸው።

ከ፳፬፻ ዓመት በፊት የነበረ ካምቢሲስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ በነበረበት ዘመን ቴቤስ ፈርሶ ነበር። የከተማው ፍራሽ ከነጭ ዐባይ ወንዝ ግራና ቀኝ ፳፯ ማይል ርቀት ተበታትኖ እስከ ዛሬ ይታያል። ከሐውልቱም ያያሎቹ ውፍረት ፲፪ ጫማ (ፊት) ይሆናል።

ከግብፆች ነገሥታት አንደኛው ዙሪያው አርባ አምስት ማይል የሚሆን ትልቅ ጉድጓድ ቆፍራችሁ ወደታች ጥልቅነት ያለው ባሕር ይሁን ብሎ ሕዝቡን አዘዛቸው። አንደኛው ንጉሥ ደግሞ ከመሬት ውስጥ አስቆፍሮ ከዕብነ በረድ የታነጸ ሦስት ሺሕ ጓዳ ያለው አዳራሽ አሠራ። ለዚህም ዘወርዋራ መንገድ ነበረው።

ከፍ ባለው ጓዳ አንዲት የተቀደሰች አዞና ግብፆችም የሚያመልኩዋቸው ሌሎች አራዊት ነበሩ። ከምድር በታች ባለው ጓዳ የግብፃውያን ነገሥታት ዐፅም ተጋድሞአል።

ደግሞ አንደ የሚያስደንቀው ሥራ መሬቱን ወደ ውስጥ ቆፍረው አለቱ ሲወጣ ያንን ወቅረው የድንጋይ ምሰሶ ያደርጉታል። ውስጥ ለውስጥ ጋሌሪ የደርብ መንገድ እያደረጉ ይሠሩታል። በዚህ ውስጥ ከሺሕ ዓመት በፊት የሞተውን ሰው ሬሳ አጋድመውት ይገኛል። ሳይለወጥ ልክ እንደ ተቀበረ ጊዜ ሆኖ ይታያል። ይህንንም ሙሚስ ይሉታል።

የግብፅ ፒራሚድ በነጭ ዐባይ ወንዝ ዳር ይገኛል። ታላቁ ፒራሚድ ከፍታው ፭፻ ጫማ (ፊት) ነው። የግብፅ ፒራሚዶች የተሠሩበትን ዘመን የሠራቸውንም ሰው ማን እንደሆነ ከቶ አይታወቅም። ለመሆኑ ግን ለመቃብራቸውና ለዘለዓለም መታሰቢያ እንዲሆኑዋቸው ጥንታውያን የግብፅ ነገሥታት አሠርተቀቸዋል ይባላል። ነገር ግን ፒራሚዱ ሳይፈርስና ሳይናድ ምንም ብዙ ዘመን ቢቆይ የሠሩት ነገሥታት እነማን እንደ ሆኑ ስማቸው ተረስቷል።

በቴቤስ አጠገብ ባንድ ሜዳ ላይ ወንድና ሴት ሆነው የሰው መልክ የሚመስሉ ሁሉ ታላላቅ ሐውልቶች አሉ፤ ቁመታቸውም ፶ ጫማ (ፊት) ይሆናል።

በግብፆች መኻከል ከሚገኘው ከቀድሞ ሥራ ሁሉ በጣም የሚያስደንቅ ሲፊክስ የሚሉት ነገር ነው። ይኸውም ከታች አካሉ የአንበሳ ሆኖ ከላይ ከራሱ ትልቅ የሴት መልክ ነው። ዛሬ እንደሚታየው ከታች ያለው አካሉ በአሸዋ ውስጥ ተቀብሯል። የላይኛው ክፍል ከምድር በላይ የሚታየው ራሱና አንገቱ ነው። ይኸውም ቁመቱ ፸ ጫማ (ፊት) ነው። የተጠረበው ከአለት ድንጋይ ነው። በሩቁ ለተመለከተው ሰው አፍንጫዋ ደፍጣጣ የሆነች ሴት ከአሸዋ ውስጥ ብቅ ያለች ይመስላል።

በጥንት ቴቤስ አጠገብ ያለው ሉክሶር የተባለው ከተማ ፍራሽ ለተመልካቹ የሚያስደንቅ ሁኖ ያለመጠን ትልቅ ነው። ከመቅደሶቹ አንዱ የጥንት ሥራ ስመ ጥሩ ይመስላል።

ግብፃውያን ይህን የሚያስደንቅ ሥራ ሲሠሩበት በነበሩ ዘመን ከዛሬ ይልቅ የዚያን ጊዜ ብዙ ጥበብ ዐዋቂዎችና የተማሩ ሰዎች እንደነበሩ ይታያል። ጥበባቸውንና ዕውቀታቸው ከፍ ያለ እንደ ነበረ ተመልክተው የሌሎች አገር ሰዎች እንደ አስማተኞች ይገምቱዋቸው ነበር።

ግብፆች ልማደ አገር ከንቱ አምልኮት ነበራቸው። ዋናዩቱም ጣዖታቸው ኢሲስ ትባላለች፤ ባልዋም ኦሲሪስ ይባላል። ምስላቸውን ሠርተው ለነዚህ ይሰግዱላቸዋል። ኢሲስ በጣም የተከበረች ጣዖት ናት፤ ሕዝቡም አያሎች መቅደሶች ሠርተውላታል፤ በዚህም ያመልኩዋታል።